The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ሕወሓቶችና የአጋር ድርጅት አመራሮች እየተናከሱ ነው

በአባይጸሃዬ የሚመራው የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ያቀረበውን ጥናት ሃይለማሪያም ደሳለኝ ውድቅ ማደረጉ በመካከላቸው ያለው ክፍፍልና አለመግባባት የደረሰበትን ጡዘት ደረጃ ያመለክታል ተብሎአል።
የህወሃት ቁንጮ የነበረው መለስ ዘናዊ በሞት ከተለየ ወዲህ በህዝባዊ ወያኔ ሃሪነት ትግራይና በአባል ድርጅቶቹ አመራሮች
መካከል አለመግባባትና ክፍፍል መንገሱ ላለፉት አራት አመታት ውስጥ ለውስጥ ሲናፈስ ከቆየ በኋላ ሃይለማሪያም ደሳለኝ
ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሎአል።

የህወሃት ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ትናንት ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓመተምህረት ለመንግሥትና ለፓርቲ ጋዜጠኞች በሰጠው
መግለጫ እንደተናገረው በኢህአደግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው አለመግባባት በህወሃትና በብአዴን መካከል ብቻ ሳይሆን በህወሃትና በኦህዴድ እንዲሁም በህወሃትና በደኢዴድ
መካከልም ነው።
ሃይለማሪያም በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫው በተለይ በብአዴንና በህወሃት አመራሮች መካከል ያለው አለመግባባት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን ገና ድርጅቶቹ በመሳሪያ ትግል ላይ ከነበሩበት
ጊዜ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ተናግሮአል። ሆኖም በመሳሪያ ትግሉ ወቅት ያልነበረውና ህወሃት የአዲስ አበባን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ቦኋላ የተፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
ዲሞክራሲያዊ ድርጅትም ሆነ ህወሃት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ላይ በነበረበት የመጨረሻው ትግል ወቅት የተመሠረተው የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ከመቸ
ጀምሮ ከህወሃት አመራር ጋር መላተም እንደጀመሩና አደባባይ ላይ የወጣው አለመግባባት መንስኤው ምን እንደሆነ ከመናገር ተቆጥቦአል።
አንዳንድ ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው የውስጥ ምንጮች እንደሚናገሩት በህወሃትና በአባል ድርጅቶቹ አመራሮች መካከል ለተነሳው አለመግባባት ዋናው ምክንያት የህወሃት አመራሮች
በአብዛኛው የተቆጣጠሩት ቁልፍ የመንግስት ሥልጣን ቦታዎችና ከአቅማቸው በላይ በዘረፋ ያካበቱት ሃብት ጉዳይ ነው።
ህወሃቶች በደም መስዋዕትነት አገኘን በሚሉት የመንግሥት ሥልጣንና በስልጣን ዘመናቸው ባካበቱት ሃብት ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር መደራደር አይፈልጉም የሚሉ ምንጮች በዚህም
የተነሳ ቀደም ሲል ለግልጥቅማቸው ሲሉ የተጠጉዋቸው የሌሎች ድርጅቶች አመራሮች እንወክለዋለን ከሚሉት ህዝብ በየዕለቱ ከሚደርስባቸው ተቃውሞና ማሸማቀቅ ለመላቀቅ ሲሉ
እንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሳት በመጀመራቸው በመካከላቸው ያለው ልዩነትና አለመግባባት እየተባባሰ እንደሄደ ይገልጻሉ።
በተለይ የመለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በህወሃት አመራሮች ምርጫ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ጠቅላይ ሚንስትርነት ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በመሳሪያ ትግል ወቅት ከፍተኛ
መስዋዕትነት የከፈሉትን የብአዴንን አመራሮችንና እወክለዋለሁ በሚለው ህዝብ ብዛት ወደ ከፍተኛው ሥልጣን እርከን መምጣት እንደነበረበት እየዋለ እያደረ ግንዛቤ እያገኘ
የመጣውን የኦህዴድ አመራሮችን በህወሃት ላይ ቂም እንዲቋጥሩ አድርጎአቸዋል የሚሉ አሉ።
የህወሃትን የበላይነት እንደቀድሞው ላለመቀበል በኢህአደግ አባል ድርጅቶች መካከል እያደገ የመጣው ልዩነት አደባባይ መውጣት መጀመሩን ከሚጠቁሙ ምልክቶች አንዱ በሆነው
በትናንትናው የሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በራሱ በሃይለማሪያም ጠቅላይ ሚንስትር መ/ቤት ሥር የሚገኘውና በአባይ ጸሃይ የሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ምርምር
ማዕከል ያወጣው የጥናት ሪፖርት ውድቅ መደረጉ ነው። በአባ ጸሃይ ዳይሬክተርነት የሚመራው የምርምር ማዕከል በዚህ ሪፖርቱ ሥራ አስፈጻሚው አካል ከህግ በላይ እየሆነ መምጣቱ
በአገሪቱ ውስጥ እየተባባሰ ለመጣው የፖለቲካ ችግር ምክንያት መሆኑን በግልጽ ቋንቋ አስቀምጦአል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ምንስትሩ መሆኑ የሚነገርለት የፖሊሲ ምርምር ማዕከል
ለአንድ አመት ያህል አካሂጄዋለሁ በማለት ያቀረበውን የጥናት ሪፖርት ሃይለማሪያም ደሳለኝ አደባባይ ላይ ወጥቶ ስለ ሪፖርቱ የማውቀው ነገር የለም ማለቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
አባይ ጸሃይ ሃይለማሪያም ደሳለኝን ካነገሱ የህወሃት መሪዎች አንዱ ሆኖ ሳለ የርሱን ሪፖርት ለማጥላላት አይዞህ ያለው ሌላ የህወሃት አንጃ መኖሩን የሚየመለክት እንደሆነ የፖለቲካ
ተንታኞች ይናገራሉ።
Source: Tensae Radio

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: