The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የሕወሓት መንግስት 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮችን ማስገባቱ ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ መንግስት ከሁለት መቶ የማያንሱ አዳዲስ ታንኮችን በጅቡቲ ወደብ በኩል ማስገባቱ ተሰማ:: ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ መንግስት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ውስጥ ቢሆብም እነዚህን ታንኮችን ማስገባቱ አነጋጋሪ ሆኗል::

ታንኮቹ ጅቡቲ ወደብ የደረሱት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ እንደሆነ የሚገልጹት ምንጮቻችን ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ባለበት ወቅት ወደ መሃል ኢትዮጵያ የተወሰኑትን ታንኮች ማቀስቀስ መጀመሩን ገልጸውልናል::

የውጭ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የተራድኦ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በተራበበትና ነጋዴዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ንግዳቸውን ማንቀሳቀስ ባልቻሉበት ወቅት መንግስት 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮችን ማስገባቱ እያነጋገረ ነው::

የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከሁለት ሳምንት በፊት ጅቡቲ እንደነበሩ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

posted by GA

Single Post Navigation

Leave a comment