The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የአማራን የስነልቦና ከፍታ በእግር ኳስ ውጤት ቀርቶ በግድያም አይዋዥቅም (ተሻሽሎ በድጋሚ የቀረበ) – አያሌው መንበር

በዚህ ጉዳይ ላይ በህዳር ወር የግሌን ሀሳብ አስፍሬ ነበር።ዛሬም ጉዳዩ ተመሳሳይ ሁኔታ ስለተከሰተ ለማስታወስ ያህል እንጅ ብዙ አልጨምርበትም።የአማራ ህዝብ ስነልቦና ስንል በእኔ እይታ የሀገር ዳር ድንበር የማስከበርና የአይደፈሬነት ባህልን ያዳበረ ባህሉን ወጉን ታሪኩን ማንነቱን ያስከበረና የሌላውን ያልጠላ መመኪያ ማለት ነው።ይህ በህወሃት ዘንድ የማይወደደው እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲጠፋ የሚፈለገው ግን ሊጠፋ የማይችል አንጡራ ሀብታችን ነው።

የሆነው ሆኖ በመቀሌ ህወሃት ትግሬዎች የአማራውን ክለብ ባህር ዳር ከነማን ጨዋታውን ከሥፖርት ውጭ በሆነ መንገድ ማንነት ነክ የሆነ በደል ፈፅመውበታል።ለዚህ ቀን ጠብቆ የሚወጣ የፎቶም ይሁን የቪዲዮ ማስረጃ አለ።

ሁሌም የሚያነጫጫቸውን የበታችነስ ስሜት የወለደው “በሁሉም ዘርፍ የትግራይ የበላይነትን” የመገንባትና ለመስበክ #ትግሬና #አማራን ለዘላለም የማያቀራርብ ፀያፍ ስድብ #አማራውን በመሰደብ፣ድብደባ በመፈፀም፣ ክልሽና ካሜራ በመደቀን “ምንም የተፈጠረ ነገር የለም” ብላችሁ አስተባብሉ በማለት የተለመደ ባህርያቸውን ሰሞኑንም ደግመውታል።

ይህንን ተከትሎ ህግ ቢኖር ኖሮ የባህር ዳር ከነማ በሁለት መንገድ (በፖለቲካዊና ህጋዊ አሰራር) ካሳ ማግኘት ይችል ነበር።አንደኛው #ብሄሩን መሰረት አድርጎ የተሰደበውን፣የተደበደበውን (በፖሊስ ጭምር) #የአማራን_ህዝብ #የትግራይ_ክልላዊ መንግስት በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ፣ይህንን የፈፀሙትን ቢያንስ የፀጥታ ሀይሉ ላይ ቅጣት በማሳለፍ፣ እና ሽማግሌ አዘጋጅቶ የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲባል ማድርግና ህዝብ ለህዝብ ማቀራረብ ይገባው ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም በሁለተኛው መንገድ #በስፖርታዊ ጨዋነትና ስፖርትን መሰረት ባደረገው በደል የባህር ዳር ከነማና የወከለው ህዝብ ሊካስ ይገባው ነበር።ካሳውም ከውጤት እስከ ገንዘብ ሊደርስ ይችላል።ይህ አሰራርም አለው።

ሆኖም ህግ የለም።የአማራው ህዝብ መንግስትም የለውም።ስለዚህ ይህንን መጠበቅ የዋህነት ነው።የሀገሪቱ ህዝብ ግማሽ የሚሆነው የአማራ ህዝብ አንዳንዴ ወጣ ገባ እያሉ ሲላላ ወደ ህዝቡ ሲጠብቅ ወደ ህወሃት በሚለጠፉ አመራሮች የሚመራ ነውና።

እናም እንደጠበቅኩት ሁሉ ውጤቱ “የባህር ዳር ከነማንም የአማራን ህዝብም ያፍንልናል” ባሉት መንገድ እንደሚሆን ፍንጮች እየወጡ ነው።ይህ ውጤትን ለመቀሌ መስጠት ለህወሃት ሁለት ጥቅም አለው።አንደኛው በስነ ልቦናው ጠንካራ የሆነውን የአማራ ህዝብ በማፈን #የተገዥነት ባህርይ እንዲያዳብርላቸው ይፈልጋሉና ውጤቱን ላይሰጡት ይችላሉ።በተቃራኒው ይህንን በማድረግ በበታችነት ስሜት የሚባዝነውን የህወሃት የውሸት ታሪክ ሰለባ የሆነውን የትግራይ ህዝብ “አሸናፊ ነህ” በማለት በሁሉም ዘርፍ የስርዓቱ የበላይ እንደሆኑ ያሳዩበታል፤ህዝባቸውን በትምክህት እንዲወጠር፣ስርዓቱንም ደሙን ለግሶም ቢሆን እንዲጠብቀው ያደርግላቸዋል።ምክንያቱም እነርሱ መንደር ኳስ ግጥሚያ “የብሄር የበላይነት ማሳያ” መለኪያ ከሆነ ሰነባብቷልና።

ይህ ግን እውን የአማራውን ስነ ልቦና ይጎዳዋል? እነርሱ እንዳሰቡት “የተገዥነት ስሜት” ውስጥ በመግባት እንዲቆዝም ያደርገዋል ወይ? ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ውጤቱ ረጅም የማያስኬድ ይሆናል።የአማራ ህዝብ ብልህ ነው።ስነልቦናውን በዚህ መልኩ ልታወርደው አትችልም።ምክንያቱም 5 ሚሊዮን ዜጎቹ በህወሃት ሲጠፉበት ስነ ልቦናው ስለተሰለበ አይደለም ዝም ያለው።ጊዜ እየጠበቀ እንጅ።ያንን ደግሞ ወቅት ጠብቆ እያሳያቸው ነው።እናም ይህንን በተመለከተ ከ6 ወር በፊት የፃፍኩትን ላካፍላችሁ።

Posted on November 3, 2016 by አያሌው መንበር
የአማራ ህዝብ የራሱ የሆነ የስነ ልቦና ከፍታ አለው።ይህ የስነ ልቦና ልኬት ቀን እየጠበቀ የሚነሳ እንጅ የሚኮሰምን ወይም የሚጠፋ አይደለም።

ይህ ወቅት የአማራ ወኔ በአዚም ከቆዘመበት እንደገና ያንሰራራበት ነው።ይህንን እውነት የማይቀበል ካለ የአደባባይ እውነትን ላለመቀበል የግል Ego የወጠረው (ሽንፈትን ላለመቀበል ወይም ላለማመን የሚሻ) አልያም በአማራ ሞት ከበሮ መደለቅ የሚፈልግና ይህ ከፍታ ግን የሚያስደነብረው ብቻ ነው።

ባለፉት አመታት የአማራን ህዝብ የራሱ የሆነውን ማንነት፣ ወግና ፍልስፍና ትቶ የሌሎችን እንዲቀበል ሙሉ በሙሉ ባይገደድም የራሱን በሚፈልገው መንገድ ይዞ እንዲቀጥል ግን አልተፈቀደለትም።ሽንፈትን እንደማይቀበል ስለሚታወቅም የተለያዩ ተቀፅላዎች እየወጡለት ወኔው ወይም የስነ ልቦና ከፍታው እንዲደበዝዝ የአጥፊ ስም እየሰጠው በሌሎች ወገኖቹ ዘንድ በስፋት ተሰርቷል።ሊቀበላቸው የማይችሉ የፋብሪካ ውጤት የመሰሉ፤ውሸት ነገር ግን እንዳይታወቁ ቅብ የተቀቡ ታሪኮች ተፅፈውለታል።ስነ ልቦናውን ለመምታት ቅስም ሰባሪ ቃላትም ተሰጥተውታል።ይህንን ለማስተባበል ከመሞከር ይልቅ ቀንን ማሳለፍ የመረጠው ብልሁ የአማራ ህዝብ ካለፋት ሁለት አመታት ጀምሮ ግን አንድ አረም ስለተነቀለለትና እራሱን እያደራጀ ስለመጣ ስነ ልቦናው ወደነበረበት እየመለሰው ነው።በእኔ እምነትም የአማራን ስነልቦና መገንባት አማራን በፖለቲካ እንዲሳተፍ ከመወትወት ሁሉ ቀድሞ መሰራት ያለበት የቤት ስራ ነበር፤ነውም።ይህ ደግሞ ከአንዳንድ አባቶች እና ከበርካታ አያቶች የሚገኝ ሲሆን ይህ ወጣት በሚመቸው መንገድ ቀምሞ የአማራን ጠንካራ ስነ ልቦና መገንባት ስራየ ብሎ ተያይዞት ውጤቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ አግኝቶታል።ባለፈው አንድ አመት የአማራ ታሪክ ጎልቶ ባይወጣ እንኳን የኢትዮጵያ አለኝታ የሆኑ የቀድሞ ነገስታቶቻችን በተለያየ አጋጣሚ ሲወደሱ ተመልክተናል።ሽለላ እና ቀረርቶ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ አልባሳት በዘመናዊ ዳንስ ቤት ሳይቀር ተውበው ቀርበዋል።እግር ኳሳችን አማራ አማራ ብሏል።ወጋችን የጎሪጥ ሳንተያይ ማውጋት ጀምረናል።

ይህ የአማራ ስነልቦና መነሳሳት የአማራን የትግል ወኔ ወለደ።የትግል ወኔው ግን ፖለቲካውን ገና በደንብ አልወለደውም።ይህ የሆነበት ደግሞ ፖለቲከኞች ስለጠፉ ወይም ስላልተወለዱልን ሳይሆን በዙሪያችን ኢህአፓ ቅኝት አዙሪት በመኖሩ፣ የመሬት ላይ ትግልን በትክክል ካለመገንዘብ በወቅቱ ካለመገምገም፣ ከወቅቱ ጋር ፈጥኖና እራስን አዋህዶ ካለመሄድ ወዘተ የመጣ ነው።ይህ ለሌሎች በር ሊከፍት ቢሞክርም ተደርምሶ ግን አይሰበርም።

የአማራ ስነ ልቦና ቶሎ አይጦዝም ቶሎ አይንኮታኮትም።አሁን የሚሻን የእኛን ፖለቲከኞች ብቻ ጠንካራ መንፈስ እና ጠንካራ አንድነት እንዲላበሱ ማድረግ ነው።ገጭ እንገው መልካም ነው።ግን ገጭ እንገውን ቶሎ መጠገን ግዴታ ነው።በእኛ መንገራገጭ ጊዜ የዋሆች ሊያሾፉብን ቢፈልጉ አንበሳጭም።መበሳጨት በገጭ እንገው ውስጥ የአተያይ ስህተት ተፈፅሞ ቁማሩን እንዳንበላ ቶሎ መመለስ እንጅ።ለዚህ ደግሞ ማንንም አንሻም እራሳችን እናስተካክለዋለን።የፖለቲካ አቋማችን መለኪያውም ይህንን ማለፍ ነው።መርህ ላይ የተመሰረተ ትግል።አማራነትና አማራነትን ለድርድር አለማቅረብ።በአማራነት ማዕቀፍ ውስጥ ግን በራስት የጠራ እይታ እራስን ማየት።ይህ የማይቻል የሚመስል ግን የሚቻል ፈታኝ ነገር ነው።የአማራ ብሄርተኝነትን ኤሊቱ አልወለደውም ታችኛው ማህበረሰብ እንጅ።ይህ በእኛም ሀገር ሆነ በአለም ላይ በአለም ከተሞከሩት ብሄርተኝነቶች የተለየ ነው።የአብዛኛው ብሄርተኝነት ከምሁራን ይጀምራል፤ መነሻውም ጥላቻ ነው።መድረሻው ደግሞ መፈረካከስ።የእኛ ግን ምሁራኖቻችን ብዙም የማይደግፉትና ከታችኛው የመጣ በመሆኑ ለግንጠላ የማይዳርግ ለቁማርም የማይመች ነው።የሚያንዣብበውን ሁሉ የእኛ ብሄርተኝነት በድል ይመልሰዋል።

እናም አይደለም ሳንወድቅ ወድቀን እንነሳለን።

ምክንያቱም የአማራ ስነ ልቦና በእብሪተኝነት ሳይሆን በአይሸነፌነትናና ብልሃተኛነት የተሞላ ነውና።

 

የመቀሌ ስታዲየሙ ሁከት….. በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ዕይታ | ለማየት እዚህ ይጫኑ

ከወያኔ የተሻለ ስነልቦና መገንባት እንችላለን ወይ በሚል ለዶ/ር አበባ ፈቃደ የቀረበ ጥያቄና ዶክተሯ የሰጠችው ምላሽ

የምስጋናው አንዷለም ንግግርን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሕብር ራድዮ ወቅታዊ ዜናዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

posted by Gheremew Araghaw

 

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: