The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

እኛ ባቡርና አዉሮፕላን ማረፊያ ሳይሆን የጠጠር መንገድ እንኩዋን ማግኘት አልቻልነም፡፡ ባ/ዳ ብአዴን ወጣቶች ሊግ

መንገድ ያጣው መንገደኛ ህዝብ አማራ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በባለፉት 26 አመታት በአማራ ሊሰሩ በጀት ተይዞላቸዉ፤የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦላቸዉ፤ተጀምረዉ የዉሃ ሽታ ከሆኑት መንገዶች ከፊሎ ናቸው። እኛ ባቡርና አዉሮፕላን ማረፊያ ሳይሆን የጠጠር መንገድ እንኩዋን ማግኘት አልቻልነም፡፡

1. ከሀሙሲት-እስቴ- ሁለት ግዜ የዉጭ እርዳታ ተገኝቶለት ያልተሰራ ገንዘቡም የት እንደገባ ያልታወቀ በሚዲያ በተደጋጋሚ ተነግሮለት የቀረ
2. ከደብረማርቆስ-በረቡዕ ገቢያ-ሞጣ፡ በተደጋጋሚ ቃል እየተገባና እየተለካ የቀረ
3. ከዳንግላ-ጃዊ፡ ቃል ተገብቶ የቀረ
4. በኩታበር-ወገልጠና-በጌምድር ከዛሬ 20 አመት ጀምሮ ቃል ለህብረተሰቡ በየ 5 አመቱ እየተገባ የቀር
5. ከሞጣ-እስቴ-ደብረታቦር-እብናት፤ ከሶሰት አመት በፊት ተጀምሮ የቀረ

6. ከደብረታቦር-ሀሙሲት-ስማዳ (በጉና ተራራ ምእራባዊ በኩል) በ2002 ምርጫ ስራ ተጀምሮ ምርጫዉ እንዳለቀ ስራዉ የቆመ
7. ከጋሸና-ላሊበላ ከሃያ አመት በሁዋላ የተጀመር አሁን እጅግ ጥራቱ በዎረደ መልኩ እየተሰራ ያለ
8. ከቡሬ-ወለጋ ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከሶሰት አመት በፊት ይሰራል ተብሎ የነበር
9. ከኮምቦልቻ-ምስራቅ ጎጃም በተሰራ በ 3 ወሩ ፈራርሶ አሁን ለአገልግሎት የማይሆን
10. ከመርሀ ቤቴ-አዲስ አበባ ደርጃዉን የጠበቀ መንገድ ይሰራል ተብሎ የቀር አሁን አፈር እየደለደሉ የተዉት

11. ከዳባት-ጸገዴ-ወልቃይት ይሰራል በሚል ከገበሬዉ ዉጭጭ ብለዉ በሬና ፍየሉን ከዎሰዱ በሁዋላ የተሰወሩ፡፡ ዘንድሮ በግርግሩ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ በጥቀምት ወር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል
12. ከጎንደር-ቆላድባና ከጎንደር ጎርጎራ ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከ 15 አመት በፊት ታቅዶ ያልተሰራ
13. ከጢቅ-ፈለገብርሃን በ 3 አመት መጠናቀቅ ሲገባዉ ከተጀመር 9 አመት የሆነዉ
14. ከደጀን-ጀማ ወንዝ መጠናቀቅ የነበረበት ከ 7 አመት በፊት ሲሆን እስካሁን በመንቀራፈፍ ላይ ይገኛል
15. ከመቅደላ ወረዳ-ደቡብ ጎንደር-ጋይንት የሚያገናኝ መንገድ በሚሊኒየሙ በደመቀ መኮነን የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለት ያልተጀመር ዎይም የቀረ

16. ደሴ-ሮቢት ገብያ መስመር-ደሴ ከመናፈሻ-ከደሴ-አቃስታ፡፡ ሁሉም ከዛሬ 7 አመት በፊት ተቆፍሮ ሳይሰራ የቀር
17. ጣርማ በር-ሞላሌ-መሃል ሜዳ- ሊሰራ ገንዘብ ተመድቦለት ከ 3 ጊዜ በላይ የተሰረዘ
18. ከባህር ዳር -ጢስ አባይ አስፓልት መንገድ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለት በጀት ተይዞለት ያልተሰራ
19. ከደብረብርሃን-አወሽ አና ከደብረብርሃን-አንኮበር አስፓልት መንገድ በጀት ተይዞለት የቀረ
20. ባህር ዳር ላይ አዲስ የአባይ ድልድይ ከአሮጌዉ ድልድይ በስተደቡብ በኩል በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል ተገበቶ መና ሁኖ የቀረዉ

21. ከእብናት-አምደወርቅ ደረጃዉን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ቃል ተገብቶና ተጀምሮ የቀረ
22. ከአዲስ አበባ-ላሊበላ-ወልደያ-ደላንታ-ተንታ-አቃስታ-ቦረና-ወረኢሉ-ጀማ-አለም ከተማ ፕሮጀክት ተቆራርጦ በየቦታዉ ተጅምሮ የቀረ
23. ከጭልጋ-አይከል-ማሰሮ ደንብ-መሀል አርማጭሆ-አሸሬ-ሁመራ፡፡ በ1992 ጥናቱ አልቆ ለህዝብ በ 3 አመት እንሰራዋለን ብለዉ የመሰረት ድንጋይ ጥለዉ፤ አሁን ከብጥብጡ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የመሰረት ድንጋያ ተጥሉዋል
24. ከደሴ-ሳይንት-ስማዳ-እስቴ-ባህርዳር ምርጫ በመጣ ቁጥር ለአካባቢዉ ሀዝብ ቃል እየተገባለት ያልተሰራ
25. ወረኢሉ-ጉጅፍቱ-አለም ከተማ፡ ሁለት ግዜ የአስፓልት መንገድ ሊሰራ ተጀምሮ የቀረ

26. የኮምቦልቻ-መካነሰላም-ግንደወይን አስፓልት ተሰርቶ የፈረሰ
27. ከወገራ-በለሳ-ዋግምራ ቤት ሁሉ ተቀብቶ የቀረዉ መንገድ
28. ከአዲስ ዘመን-በለሳ-ሀሙሲት
29. ከደብረብርሀን-እነወሪ አስፓልት ሊሰራ ተብሎ በጀት ተይዞለት የጠፋ
30. ከባህርዳር-ድልሸት-ጨንታ፤ የአስፓልት መንገድ በጀት ተመድቦለት የቀረ

31. ከላይ ጋይንት-ታች ጋይነት-አአ፤ደረጃዉን የጠበቀ መንገድ ይሰራል ተብሎ በየምራጫዉ ጊዜ ቃል የተገባ
32. ከደንበጫ-ፈረስ ቤት-ደጋዳሞት
33. ከባህርዳር-አዴት-ፈረስቤት-ደብረማርቆስ የመሰርት ድንጋይ ተጥሎለት የቀረ

ድርጅታችን ብአዴን አትኩሮት ሊሰጠው የሚገባ ትልቅ ህዝዝባዊ ጥያቄ ነው !!

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: