The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ (አያሌው መንበር)

በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ
(አያሌው መንበር)

ህወሃቶች አጀንዳ መዘዝ ሲያደርጉ መቸም የሚያክላቸው የለም።ዛሬ ደግሞ በVOA ጋዜጠኛዋ አዳነች ፍሰሃየ በኩል መቀሌን ከሁለቱ የአማራ ከተሞች (ከባህር ዳርና ደብረ ብርሃን)፣ከአዋሳ፣…ወዘተ እያወዳደሩ፣ ሁለት ትግሬዎችን ለምስክርነት በመጥራት <<እኛ እኮ ነን በድህነት ውስጥ ያለን፣የተረሳን ነን>> የሚልን አስቂኝ ዘገባ በመስራት አጀንዳ ሰጥተውናል።ይህ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት አባይ ወልዱ የትግራይ ኪራይሰብሳቢዎች “በህዝቡ ስም አትነግዱ” በማለት ከገለፀው ጋር ተቀራራቢ ይሁን ተቃራኒ አንባቢ የሚፈርደው ሆኖ እውነታው ግን የሚከተለው ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ነገር ለማሰስሰብ አስቤ በይደር ይዠው የነበረውን እቅድ ይህንን እንዳየው ግን ወቅቱ አሁን ነው መሰለኝ ብየ የመንግስትና የNGO መረጃዎችን ለማገላበጥ ሞከርኩ።ከዚያም አሸማቃቂ ሀገራዊ መረጃዎችን ተመለከትኩ።በእርግጥ በመረጃው መሰረት ከሆነ ለውጦችም ይታያሉ።
እንዲያው የሆነው ሆኖ እ.ኤ.አ በ1995 46 የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶው ህዝብ ከዓለማቀፉ የድህነት መስመር በታች እንደሚኖር ይህ አሃዝ በ2004/5 እንደቀነሰ ያሳያል።ሌላ የመንግስት የGTP II አሃዝ የድህነት መጠኑ በ2014 ወደ 23 በመቶ እንደወረደ ያመላክታል።
በመጀመሪያው ጊዜ (ከ95 እስከ 2004) በዚህ ዳታ ላይ የድህነት መጠኑ በትግራይ ሰፋ ብሎ 48.5 በመቶ በአማራ ደግሞ 40 በመቶ ነበር ይላል Poverty and Inequality in Ethiopia 1995 to 2004 በሚል በአ.አ.ዩኒቨርሲቲው ጣሰው ወልደ ሀና፣ በዓለማቀፉ የምግብ ፖሊሲ የጥናት ተቋሙ John Hoddinott እና Stefan Dercon በተባሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አማካኝነት የተጠናቀረውና መነሻውን መንግስታዊ ዳታ ያደረገው መረጃ።
ይህንን መረጃ ከ1995 እስከ 2011 ስንመለከት የትግራይ የድህነት ቅነሳ አሃዝ ከ48 በመቶ ወደ 30 (የ18 በመቶ ልዩነት አሳይቴ) ሲወርድ የአማራው ግን ከ40 በመቶ ወደ 30 በመቶ (10 በመቶ ብቻ ነው) ቅናሽ ያሳየው።
ይህ እንግዲህ ባለው የሀገር ውስጥ የምጣኔ ሀብታዊ እድገት እንኳን እንደሌላው እኩል መጠቀም ያለመቻሉ አንዱና ዋናው ማሳያ ነው።በ2014 በተደረሰበት የ23 በመቶ የድህነት ቅነሳ (ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ህዝብን) ክልላዊ ንፅፅር ለጊዜው ባለገኘውም ከዚህ የተለየ አሃዝ እንደማይኖር ግን ነባራዊ ሁኔታው ይነግረናል።
አንዳንድ ተጨማሪ ሰነዶችን ለማገላበጥ ያህል እስኪ የኢህአዴግን “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ትንሽ እንቃኘው።በዚህ እቅድ ውስጥ የተለያዩ ሀገራዉፕ ዳታዎች ታጭቀዋል።ክልላዊ የአፈፃፀም ንፅፅር አለመሰራቱ ሆን ተብሎ ለትችት እንዳይጋለጥ ቢመስልም ያለው ላይ ተንተርሶ ግን አስተያየት መስጠት ይቻላል።ለአሁኑ የቁጠባና እና ኢንቨስትመምት እንዲሁም ወጭ ንግድን (Export) እንመልከት።
ቁጠባ በየትኛውም ሀገር ተርፎህ ሳይሆን አብቃቅተህ ለተሻለ ነገር ስትል የምታስቀምጠው ሀብት ነው።በዚህ መለኪያ ስናየው ኢትዮጵያውያን አብቃቅተው ብቻ ሳይሆን ተቸጋግረውም ቢሆን ይቆጥባሉ።በተለይም የቁጠባና ብድር ተቋማት እንደ አስገዳጅ ህግ እያደረጉ አርሶ አደሩን እየቀፈደዱ ያስቆጥባሉ።የቀበሌ አመራርም መገምገሚያው እንደነበር እኔ ራሴ አረጋግጫለው።የሆነው ሁኖ ቁጠባ ብዙ ክፋት የለውም።ክፋቱ ግን የቆጠብከው ለራስህና ለአካባቢህ ሳይውል ሲቀር ነው።
በኢትዮጵያ ያለው የቁጠባ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ይባልበት ከነበረው ከ10 በመቶ በታች ቁጠባ በጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ አሃዝ ተምዘግዝጎ ወደ 25 በመቶ እየተጠጋ ነው።ከዚህ ውስጥ የአማራ ክልል ትልቅ ድርሻ አለው።
ቁጠባ ብዙ ጊዜ የሚውለው ለሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ነው።የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ደግሞ አማራን ተጠቃሚ ያላደረገ እንደሆነ አንድ ዳታ ልጨምር።
አንድ የመንግስት መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው ዓመት ወደ 2ሺህ የሚጠጋ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲሰጥ ለትግራይ 6 ሚሊዮን ህዝብ 187 ፕሮጀክት፣ ለ30 ሚሊዮን አማራ ህዝብ ግን 159 ፕሮጀክት (ለዚያውም ሊሰራ የማይችል) ነው የተሰጠው።በቀላል ሂሳብ ስሌት ስንመለከት ትግራይ 187 ሲደርሳት አማራ 159 ሳይሆን 935 ፕሮጀክቶች ሊደርሱት ይገባ ነበር።
በገቢ ደረጃም ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በገለፁት መሰረት ከ2006 እስከ 2009 ወደ ትግራይ በኢንቨስትመምት ስም 12.6 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ሲደረግ ወደ አማራ የሄደው 2.8 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው።የአማራው ከትግራዩ በ4 እጥፍ ያንሳል፤ አማራው ከትግራይ ህዝብ ደግሞ በትንሹ በ6 እጥፍ ይበልጣል።
ወደ ምሳሌ ብንገባ እንኳን ባለፉው ዓመት 2008 ዓ.ም እኮ የ5 ቢሊዮን ብር ግዙፍ (በሀገር ደረጃ ምናልባት ግዙፍ ይመስለኛል) ፋብሪካ የተመረቀው፣ በዚህ ወር እኮ ነው የመጀመሪያው #ሞተር ፋብሪካ እዛው መቀሌው የተመረቀው፤በዓመት 18 ቢሊዮን ብር ገቢ ያስገኛል የሚባለው 120 ፋብሪካን በአንድ ላይ ያቅፋል የተባለው በ2.3 ቢሊዮን ብር የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተገነባ ያለው መቀሌ አይደለም እንዴ?፣90 አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ባለሀብቶችን ያሳተፈው የትግራዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤግዚቪሽን እኮ እየተካሄደ ያለውና የእናንተን ተጠቃሚነት ያሳየን ትናንት ግንቦት 19 ነው….የኬሚካል፣የጨርቃጨርቅ፣ የብረታብረት ፋብሪካዎች ትግራይ አይደሉምን? ይህ እኮ ሀቅን መካድ ነው።
የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንትን ስናይ ደግሞ ለአማራ የተመደበው 4.5 ቢሊዮን ብር በሲስተም ለትግራይ መሰጠቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ስለሆነም አማራ የሚቆጥበው የቁጠባ ገንዘብ ለትግራይ ኢንቨስትመንት እየዋለ ነው ማለት አይደለምን?
ሌላው ጉዳይ የገቢ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ሁኔታን ስንመለከት እ.ኤ.አ በ2009 ከነበረበት 54 ቢሊዮን ገደማ በ2016 ወደ 170 ቢሊዮን ብር አድጓል።ከዚህ ውስጥ የአማራ ግብር ከፋይነት ድርሻ በሀገሪቱን ከፍተኛ ነው።
የክልሉ ገቢ አሰባሰብ በ2012 ዓ.ም (ከሶስት ዓመት በኋላ) የክልሉ ወደ 18 ቢሊዮን ያድጋል ይላል እቅዱ።የሚሰበሰበው ገንዘብ በቀጥታ ወደፌደራል ገቢ ሆኖ ነው የበጀት ድልድል የሚደረገው።
ይህ የታክስ ገቢ አሰባሰብ የሚያደገው እንግዲህ የህዝቡ የገቢ መጠን ሳያድግ፣ ብዙም Value add ባልተደረገበት፣ የክልሉ ህዝብም ግብርና ላይ በተንጠለጠለበት ነው።
ሰብስቦ ለራሱ እንዳይጠቀም እንኳን የሚልከው ወደ ፌደራል መንግስት ነው።ከዚያም አጠቃላይ የሀገሪቱ አቅም ታይቶ ነው የሚከፋፈለው።የሀገሪቱ ከፍተኛ በጀት ለካፒታል ፕሮጅፕክቶች ማስፈፀሚያ ሲበጀትም አማራ ተጠቃሚ አይሆንም።ምክንያቱም ባለፈው እንደጠቀስነው ለአማራ ህዝብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይገነባሉ ተብለው ከተያዙት ፕሮጀክቶች ከሀምሳ በላይ ሳይፈፀሙ ሲቀሩ በትግራይ ግን በየጊዜው ነው የምረቃ ሪቫን የሚቆረጠው።ስለዚህ አማራ ሁለት ጊዜ ይበደላል ማለት ነው።
የወደፊቱን የሀገሩቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ስንመለከት ደግሞ የበለጠ ያሳስበናል።አብዛኛው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለው ትግራይና አዲስ አበባ ዙሪያ ነው።የግብርናን ጉዳይም በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ እናውቀዋለን። የግብርና ውጤቶች ወጭ ንግድ ድርሻ 3.6፣ በመቶ የአምራች ኢንዱስትሪው ደግሞ 12.5 በመቶ ነው።
በ2020 በአብዛኛው አማራ የሚያመርተውና የሚተዳደርበት የግብርና ምርቶች ወጭ ንግድ ድርሻ በ6.5 በመቶ እንዲታድግ እቅድ ሲያዝ ትግራይንል አ.አ ዙሪያን ያማከለው አምራች ኢንዱስትሪ ግን ወደ 26 በመቶ እንዲያድግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራበት ነው።ይህንን ስንመለከት ኢንዱስትሪ ወደ አማራ እንዲስፋፋና ፍትሃዊ እንዲሆን የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር ወይም 1/3ኛ የሀገሪቱ የግብርና ምርት አምራቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የግብርና ምርት ወጭ ንግድ እድገትን የሚያሳይ እቅድ ሳይነደፍ ለቀጣዩ ዘመንም አማራ ዛሬ ቆም ብሎ እምቢ ካላለ የበለጠ ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።በደላችን በሁሉም ዘርፍ ነውና ትግላችንም ሁሉን ዓቀፍ መሆን አለበት።..
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ
አዳነች ፍሳሀየ ትግራይ ከእነ “ባህር ዳር፣ደብረ ብርሃን፣አዋሳ፣አዲስ አበባ” ስትነፃፀር ችላ ተብላ በድህነት አረንቋ እየማቀቀች ነው የምትለን ሁለት ትግሬዎችን ለስምክርነት ጠርታ እንግዲህ አይኗን በጨው ቀብታ ነው።ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ ነውና ነገሩ።
ሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት ውስጥ ውስጥ ሆና በተከታታይ እድገት ውጥ ማለፏ እኮ ወደነጋቲቭ የገባውን የኦሮሚያና አማራ የምጣኔ ሀብት መነቃቃት ትግራይ በእጇ ስላስገባች እንጅ ሌላ ምንም ሎጅክ የለውም።ለአንድ ሀገር እድገት እንቅፋት ከሚባሉት አንዱ የሰላምና መረጋጋት አለመኖር ነው።ኦሮሚያም አማራም ባልተረጋጋ ህይወት ውስጥ ናቸው።
የሀገሪቱ እድገት ግን ቀጥሏል እያሉን ነው።ይህ ለምን ሆነ ሲባል ምንም እንኳን ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም መገመት ግን አያዳግትም። የአምራች ኢንዱስትሪው ትግራይ ላይ በመገንባቱ የአለመረጋጋቱ ሰለባ አለመሆኑ ትልቅ ድርሻ ይይዛል።የአገልግሎት ዘርፉ (ባህር ዳርና ጎንደር ብዙ ሆቴሎች ከ90 በመቶ በላይ ሰራተኛ ቀንሰዋል) ሽባ ሁኗል።4ቱም የትግራይ አየር ማረፊያዎች እና ሆቴሎች ግን ስራ ላይ ናቸው።አሁንም የአገልግሎት ዘርፉ አልቆመም።የግብርና ምርት ላይ መሰረት ያደረገው አማራው ደግሞ ገበሬው ወቅቱን ጠብቆ ባያዘምርም ቢያንስ ስራ አላቆመምና ራሱን መመገብ ችሏል።
በጥቅሉ “የሀገሪቱ” (የትግራይና የትግራይ ባለሀብቶች) እድገት ያላቆመው የምጣኔ ሀብት ክምችቱ ወደ ትግራይ መዞሩ መሆኑን ልብ ይሏል።የክልሉን የኢንዱስትሪ ዝርዝር ማውጣት የሚቻል ከሆነ እንጨምራለን።የአዲስ አበባን ካነሳንም የምጣኔ ሀብት ዘረፋው የተያዘው በጥቂት የትግራይ ተውላጅ ፊውዳሎች ነው።
ታድያ በየትኛው መስፈርት ነው ዛሬ መቀሌ በተፈጥሮ ብቻ እያደጉ ካሉት ከአዋሳ ወይም ከባህር ዳር ጋር የምትነፃፀረው?
መቀሌ ማለት እኮ ልክ ምዕራባውያኑ አልሸባብን እየደገፉ እንውጋው እንደሚባለው ሁሉን ቅልጭም አድርጋ ውጣ አላየውም አልሰማሁም እያለች ሰጭውንም ሌላውን በነገር የምትጎሽም አጋሰስ ከሆነች ሰነባብታለች።ይህች ጩኸት የመጣችው የሌላው አካባቢ ጩኸት ስለበረከተ አፍ ለማዘጋት ነው።
ለማንኛውም አዳነች ፍሳሃየ የተባለች ጋዜጠኛ የምትሄድበት መንገድ አሳፋሪነት ዛሬም ቀጥሏል፤ የህወሃት አጀንዳ ሰጭነት ወደ ውጭም ተሸጋግሮ ይኸው በመጨረሻ “ትግራይ በድህነት አረንቋ” በማለት ይሳለቁብናል።
ከድህነትም ከህወሃት ስናይፐር ጋርም ስቃዩን እያየ ያለው አማራውና ኦሮሞው ግን ዛሬም ስለሰብአዊነት ይጮሃል።የመኖር መብቴ ይከበርልኝ እያለ ይጠይቃል።ህወሃት ደግሞ እኔ እኮ አንተን አላውቅህም፤ላንተ አልታገልኩም እያለ መግደሉን ቀጥሏል።

posted by Gheremew Araghaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: