The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የአባቶቻችንና የአያቶቻችን መስዋእትና ጀግንነት በትግሬ ወያኔዎች ዘመን በእኛ አይዋረድምና አይጣስም -ገረመው አራጋው

ኢትዮጵያን ለማረድና ተቀራምቶ ለመብላት የሱዳንና የትግሬ ወያኔ ስምምነት መንስኤው በእውነት፣ በታሪክና በሀቅ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ከጥቅም ጋር የተያያዘ ጠላትነት ነው፡፡ የሱዳንና የትግሬ ወያኔ ግንኙነት ከ1976 ጀምሮ የተጠነናከረ ሲሆን ይህም የሆነ በወያኔዎች ልመና ነው፡፡ ምክንያቱም አለቃቸውና ጌታቸው የነበር ሻቢያ ማለትም ኢሳያስ ከአሁን ጀምሮ እንዳላያችሁ በማለት ከኤርትራ ስላባረራቸውና ድጋፍ ስለነሳቸው ነው፡፡ ከሱዳን ወደብ ተነስቶ በኤርትራ በኩል እየገባ ከነሱ ይደርስ የነበር ኢትዮጵያን የሚያተራምስ የምእራባዊያን በተለይም የእንግሊዝ የጦር መሳሪያ፣ ትጥቅና የምግብ እርዳታ ስለቆመባቸው ከመቸገርም አልፈው እከትሞላቸው ነበር፡፡

በዚህም ጊዜ ነው የኤርትራ በር ሲዘጋባቸውና የሻቢያ ሞግዚትነት ሲያበቃ ተከዜን ተሻግረው ጎንደር በመድረስ በወልቃይት በኩል ከሱዳን ጋር ግንኙነት የጀመሩ፡፡ ሱዳንም ይህን ችግራቸውን ያውቅ ስለነበርና መሄጃ እንደሌላቸው በማመን ለሚደርግላቸው ውለታ ምላሽ በለምነቱና በሀብታምነቱ ከሚታወቀው የጎንደር ግዛት መሬት በስስት የሚቋምጥ የመቋደስ ምኞት እንዳለው የነገሯቸው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ትግሬ ወኔያዎችም በዚህ ሁኔታ ነው የተጠየቁትን ሁሉ እንደሚፈጽሙ ቃል በመግባት በሱዳንና በምእራባዊያን እርዳታ ለስልጣን ሲበቁ የፈለጋቸውን ያህል የኢትዮጵያን መሬት ሱዳኖች መውሰድ እንደሚችሉ ያሳወቋቸውና በዚህም መልክ ግንኙነታቸው በኢትዮጵያና ሀዝቦቿ ላይ የሁለቱ ወንጀል ተመስርቶ እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ፡፡

በእንግሊዝና ሲአይኤ አማካኝነት ሱዳን ውስጥ ሻቢያና ትግሬ ወያኔዎች እስከታረቁበት 1978 ድረስ ለሶስት አመት አካባቢ ሁለቱ ጠላቶች ነበሩ፡፡ በዚህም ወቅት ነው በኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚዘጋና ኤርትራ የምትባል ሀገር ትግርኛ ብሄረሰብን ብቻ በሚወክል ሻቢያ አማካኝነት ከኢትዮጵያ መገንጠል እንዳለባት ለመታረቅ የተስማሙና የተወሰነ፡፡

ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ለሱዳን የሚሰጠው የጎንደር አስተዳደር አካል የሆነ በጣም ለምና ሰፊ ቦታ ፋሲለደስን ጨምሮ በታሪክ እስከ ደርግ ዘመን ድረስ ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ አቅርባበት አታውቅም፤ መረጃ በማቅረብ ልትከራከርበት ቀርቶ፡፡ የትግራይ አካል ስላልሆነ ግድ ባለመሰኘት ለመወዳጃ ሲሉ በጉቦ መልክ ከጎንደር እየቆረሱ ትግሬዎች በደስታ ለሱዳን የሚሰጡት በጣም ለምና ጠቃሚ መሬት ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ እንደሆነ ህጋዊና አለማቀፋዊ ብዙ መረጃዎች ያሉት ሲሆን ለሱዳን ስለመሆኑ ግን አንዳችም መረጃ የለውም፡፡ አሁን እየሆነ ያለ መንግስት ነኝ የሚል ትግሬ ሀገሪቱን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ እንደፈለገው እየሆነ በጉቦ መልክ የሀገርን በጣም ለምና ጠቃሚ ግዛት ለባእድ አሳልፎ እየሰጠ ነው፡፡

ትግሬ ወያኔ በአንድ በኩል እሱ በወልቃይት ወረራና ዘረፋ እያካሄደ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ወረራ ለማስቀጠል ሱዳን ትረዳው ዘንድ የፈለጉትን ያህል የኢትዮጵያን መሬት በጉቦ መልክ ለሱዳኖች እየሰጠ ይገኛል፡፡ አጀማመራቸውና አመጣጣቸው በአማራ ላይ ጥላቻ ተሞልተው ወንጀል እየፈጸሙ ኢትዮጵያን በማፍረስ ሁሉም እንቅስቃሴያቸውና ግባቸው ለትግራይና ትግሬ ብቻ ስለሆነ ከትግሬና ትግራይ ውጪ የሚደርስ የህዝብ በደልና የሀገር ጉዳት ለግባቸው መሳካት እንደሆነ የሚታያቸው ናቸው፡፡ የለየላቸውና ከዚህ በፊት በአለም ታሪከ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጨካኞች ሆነው እንጂ በመሪነት ደረጃ ላይ ሆነው ግን እንዴት ለምና ጠቃሚ የሆነን የሀገር ግዛት ለግል መወዳጃ ሲሉ ለባእድ ያስረክባሉ? ምን አይነት አረመኔዎች፣ ጨካኞችና አደገኞች እንደሆኑ የምናውቃቸው ብንሆንም አረመኔነታቸው፣ ጨካኝነታቸውና አደገኛነታቸው ግን ወሰንና ወደር የሌለውና በተጠናከረ ሀይል በጉልበት ካላስቆምናቸው ገና ገና ከከፋ ችግር ውስጥ ሁላችንንም የሚከቱን ሰይጣኖች ናቸው፡፡

ሰሜን ሱዳን ከ407 ብሄረሰቦች በላይ የሚኖሩባት ነች፡፡ ከሁሉም የአጎራባች ሀገሮች ጋር ግጭት አለባት፤ ከኢትዮጵያም ሀዝብ ጋር፡፡ ላለፉት 14 አመታት በዳርፉርና ቀይ ባህርን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ሱዳን እንዲሁም ላለፉት 6 አመታት በሁለቱ ቆርዶፋን፣ ብሉ ናይልና አበዬ ሰላም የሌላትና ጦርነት የሚካሄድባት ነች፡፡ ከግብጽ ጋር ከከባድ ግጭት ላይ ናቸው፡፡ ጎንደርን የሚያዋስነውና ለም የሆነው ቦታቸው ብቻ ነው ሰላማዊ የሱዳን ግዛት የሚባል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ትግሬ ወያኔወች በኢትዮጵያ በተለይም ወልቃይትን ጨምሮ በጎንደር የሚያካሂዱትን ወንጀል ለማስቀጠል ያመቻቸው ዘንድ ሀገር እያፈረሱና እየቆረሱ የባእድ ሀገር አካል የሆነን የሱዳንን ደህንነት ስለሚጠብቁና ከመሬት ጀምሮ ስጦታ ስለሚያደርጉለት ነው፡፡

ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን አፍርሰው በጋራ ለመጠቀም ተባብረው የሚሰሩ የባሽር መንግስትና ትግሬዎች ግን ሊወጡበት ከማይችሉ ጣጣ ውስጥ የገቡ ሲሆኑ በቅርብ ቀን መስመጣቸው አይቀርም፡፡ ወታደር የሆነ ባሽር ልክ እንደ ትግሬዎች ስልጣን የያዘ በጉልበት ነው፡፡ በሰልጣን ላይ 28 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ያረጃና በጣም በሽተኛ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት በወንጀለኛነት ተከስሶ ለመያዝ የሚፈለግና እንደፈለገው መንቀሳቀስ የማይችል ወንጀለኛ ነው፡፡ ከ6 አመት በፊት ምንዛሬው ከ3 ዶላር በታች የነበር የሱዳን ፓውንድ አሁን ከ23 ዶላር በላይ ደርሷል፡፡ 35 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት፣ ድሃ የሆነች፣ ማእቀብ የተጣለባት፣ በጦርነት የምትታመስና የተገለለች ሱዳን የውጪ ብድር ከ53 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከ75 በመቶ በላይ ጥቁር አፍሪካዊ እና ቀሪው ደግሞ ሀበሻዊ፣ ሜሩን፣ ኑቢያ፣ ቤጃና የመሳሰሉት የሰው ዘርን ነን በሚል ሰበብና በ407 ብህረሰቦች በጎሳና ሌላም መከፋፈል ተጨምሮበት ሱዳን የተመሰቃቀለችና በጦርነት የምትታመስ ሀገር ስትሆን መፍረሷ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡

በዚች አይነቷም ላይ ነው ተስፋ በመጣልና ታማኝ አገልጋይ በሪያ በመምሰል እያጎበደዱ ትግሬዎች ከሱዳን ጋር በማበር ሀገራችንንና ህዝባችንን የሚጎዱና በጣም ለምና ጠቃሚ የሆነን የኢትዮጵያ መሬት እንደ ቡና ቁርስ ከጎንደር እየቆረሱ ለሱዳን የሚሰጡ፡፡ መሆን የነበረበት ግን ሱዳን የመሬት ጥያቄ በኢትዮጵያ ላይ ካላት በግልጽ በመውጣት በህዝብና በህግ ፊት ቀርበው ምክንያታቸውን ከነመረጃው በማቅረብ ኢትዮጵያን በትክክልና በብቃት ከሚወክሉት ጋር መከራከርና ውሳኔውን መቀበል ነው፡፡ ይህ ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በድብቅና በምስጢር ለሁለቱ የጋራ ጥቅም በሚሆን እየተስማሙ የኢትዮጵያን መሬት መውሰድ ግን ወረራ ሲሆን ቦታው የትም ስለማይሄድ ትግሬዎች ሲባረሩ በኢትዮጵያዊያን የጋራ ሀይልና ጥረት መመለሱ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያኖች ግን በተለይም ምሁሮች በእውቀታቸውና ችሎታቸው እስከ አለም ፍርድ ቤት በመድረስ የወያኔዎችን ወንጀል ማጋለጥና ሱዳን የምትወስደውን የመሬት ስጦታ በመረጃ በተደገፈ መቃወምና ተቀባይነት እንደሌለው ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ጀግና ጎንደሬዎች በጀግንነታቸው በመቀጠልና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የሱዳንን ወራሪ ሀይል መጋፈጥና ማጥቃት ግድ የሚል ነው፡፡ የሱዳን ወራሪ ሀይል ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በመተባበር በጎንደር በኩል ሀገር እየወረሩና ህዝብን እየወጉ እንደሆኑ የሚታወቅ ሀቅ ነው እና ሁለቱንም ጠላቶች ጨክኖ ማጥቃት ግዴታ ሲሆን የህልውናና የመብት ጉዳይ ነው፡፡ አድማሱንም በማስፋት በጉሙዝ ማለትም በመተከልና በቤሻንጉል በኩል ከሚገኙ መሳሪያ ያነሱ የሱዳን ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር ግንኙነት ማድረግና በጋራ ሱዳንን ማጥቃት ግድ ይላል፡፡

ጎንደርን ጨምሮ የወልቃይት በትግሬዎች መወረር፣ በጎጃምና በአጠቃላይ በአማራ ላይ እየደረሰ ያለን የትግሬዎች ወንጀል የሚያንቀሳቅሰው ሞተሩና የሚያስሄደው ነዳጅ ዘመናት ያስቆጠረ የሱዳን እርዳታ ነው፡፡ በጦርነት እየታመሰችና በተለያየ ችግር እየሰጠመች ያለች ሱዳን ግን ትግሬዎችን በረጅም የምታዋጣቸው ስለመሆኗ በቅርብ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትቅደም

ገረመው አራጋው

 

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: