The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

Archive for the category “Political Opinion”

የአባቶቻችንና የአያቶቻችን መስዋእትና ጀግንነት በትግሬ ወያኔዎች ዘመን በእኛ አይዋረድምና አይጣስም -ገረመው አራጋው

ኢትዮጵያን ለማረድና ተቀራምቶ ለመብላት የሱዳንና የትግሬ ወያኔ ስምምነት መንስኤው በእውነት፣ በታሪክና በሀቅ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ከጥቅም ጋር የተያያዘ ጠላትነት ነው፡፡ የሱዳንና የትግሬ ወያኔ ግንኙነት ከ1976 ጀምሮ የተጠነናከረ ሲሆን ይህም የሆነ በወያኔዎች ልመና ነው፡፡ ምክንያቱም አለቃቸውና ጌታቸው የነበር ሻቢያ ማለትም ኢሳያስ ከአሁን ጀምሮ እንዳላያችሁ በማለት ከኤርትራ ስላባረራቸውና ድጋፍ ስለነሳቸው ነው፡፡ ከሱዳን ወደብ ተነስቶ በኤርትራ በኩል እየገባ ከነሱ ይደርስ የነበር ኢትዮጵያን የሚያተራምስ የምእራባዊያን በተለይም የእንግሊዝ የጦር መሳሪያ፣ ትጥቅና የምግብ እርዳታ ስለቆመባቸው ከመቸገርም አልፈው እከትሞላቸው ነበር፡፡

በዚህም ጊዜ ነው የኤርትራ በር ሲዘጋባቸውና የሻቢያ ሞግዚትነት ሲያበቃ ተከዜን ተሻግረው ጎንደር በመድረስ በወልቃይት በኩል ከሱዳን ጋር ግንኙነት የጀመሩ፡፡ ሱዳንም ይህን ችግራቸውን ያውቅ ስለነበርና መሄጃ እንደሌላቸው በማመን ለሚደርግላቸው ውለታ ምላሽ በለምነቱና በሀብታምነቱ ከሚታወቀው የጎንደር ግዛት መሬት በስስት የሚቋምጥ የመቋደስ ምኞት እንዳለው የነገሯቸው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ትግሬ ወኔያዎችም በዚህ ሁኔታ ነው የተጠየቁትን ሁሉ እንደሚፈጽሙ ቃል በመግባት በሱዳንና በምእራባዊያን እርዳታ ለስልጣን ሲበቁ የፈለጋቸውን ያህል የኢትዮጵያን መሬት ሱዳኖች መውሰድ እንደሚችሉ ያሳወቋቸውና በዚህም መልክ ግንኙነታቸው በኢትዮጵያና ሀዝቦቿ ላይ የሁለቱ ወንጀል ተመስርቶ እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ፡፡

በእንግሊዝና ሲአይኤ አማካኝነት ሱዳን ውስጥ ሻቢያና ትግሬ ወያኔዎች እስከታረቁበት 1978 ድረስ ለሶስት አመት አካባቢ ሁለቱ ጠላቶች ነበሩ፡፡ በዚህም ወቅት ነው በኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚዘጋና ኤርትራ የምትባል ሀገር ትግርኛ ብሄረሰብን ብቻ በሚወክል ሻቢያ አማካኝነት ከኢትዮጵያ መገንጠል እንዳለባት ለመታረቅ የተስማሙና የተወሰነ፡፡

ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ለሱዳን የሚሰጠው የጎንደር አስተዳደር አካል የሆነ በጣም ለምና ሰፊ ቦታ ፋሲለደስን ጨምሮ በታሪክ እስከ ደርግ ዘመን ድረስ ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ አቅርባበት አታውቅም፤ መረጃ በማቅረብ ልትከራከርበት ቀርቶ፡፡ የትግራይ አካል ስላልሆነ ግድ ባለመሰኘት ለመወዳጃ ሲሉ በጉቦ መልክ ከጎንደር እየቆረሱ ትግሬዎች በደስታ ለሱዳን የሚሰጡት በጣም ለምና ጠቃሚ መሬት ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ እንደሆነ ህጋዊና አለማቀፋዊ ብዙ መረጃዎች ያሉት ሲሆን ለሱዳን ስለመሆኑ ግን አንዳችም መረጃ የለውም፡፡ አሁን እየሆነ ያለ መንግስት ነኝ የሚል ትግሬ ሀገሪቱን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ እንደፈለገው እየሆነ በጉቦ መልክ የሀገርን በጣም ለምና ጠቃሚ ግዛት ለባእድ አሳልፎ እየሰጠ ነው፡፡

ትግሬ ወያኔ በአንድ በኩል እሱ በወልቃይት ወረራና ዘረፋ እያካሄደ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ወረራ ለማስቀጠል ሱዳን ትረዳው ዘንድ የፈለጉትን ያህል የኢትዮጵያን መሬት በጉቦ መልክ ለሱዳኖች እየሰጠ ይገኛል፡፡ አጀማመራቸውና አመጣጣቸው በአማራ ላይ ጥላቻ ተሞልተው ወንጀል እየፈጸሙ ኢትዮጵያን በማፍረስ ሁሉም እንቅስቃሴያቸውና ግባቸው ለትግራይና ትግሬ ብቻ ስለሆነ ከትግሬና ትግራይ ውጪ የሚደርስ የህዝብ በደልና የሀገር ጉዳት ለግባቸው መሳካት እንደሆነ የሚታያቸው ናቸው፡፡ የለየላቸውና ከዚህ በፊት በአለም ታሪከ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጨካኞች ሆነው እንጂ በመሪነት ደረጃ ላይ ሆነው ግን እንዴት ለምና ጠቃሚ የሆነን የሀገር ግዛት ለግል መወዳጃ ሲሉ ለባእድ ያስረክባሉ? ምን አይነት አረመኔዎች፣ ጨካኞችና አደገኞች እንደሆኑ የምናውቃቸው ብንሆንም አረመኔነታቸው፣ ጨካኝነታቸውና አደገኛነታቸው ግን ወሰንና ወደር የሌለውና በተጠናከረ ሀይል በጉልበት ካላስቆምናቸው ገና ገና ከከፋ ችግር ውስጥ ሁላችንንም የሚከቱን ሰይጣኖች ናቸው፡፡

ሰሜን ሱዳን ከ407 ብሄረሰቦች በላይ የሚኖሩባት ነች፡፡ ከሁሉም የአጎራባች ሀገሮች ጋር ግጭት አለባት፤ ከኢትዮጵያም ሀዝብ ጋር፡፡ ላለፉት 14 አመታት በዳርፉርና ቀይ ባህርን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ሱዳን እንዲሁም ላለፉት 6 አመታት በሁለቱ ቆርዶፋን፣ ብሉ ናይልና አበዬ ሰላም የሌላትና ጦርነት የሚካሄድባት ነች፡፡ ከግብጽ ጋር ከከባድ ግጭት ላይ ናቸው፡፡ ጎንደርን የሚያዋስነውና ለም የሆነው ቦታቸው ብቻ ነው ሰላማዊ የሱዳን ግዛት የሚባል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ትግሬ ወያኔወች በኢትዮጵያ በተለይም ወልቃይትን ጨምሮ በጎንደር የሚያካሂዱትን ወንጀል ለማስቀጠል ያመቻቸው ዘንድ ሀገር እያፈረሱና እየቆረሱ የባእድ ሀገር አካል የሆነን የሱዳንን ደህንነት ስለሚጠብቁና ከመሬት ጀምሮ ስጦታ ስለሚያደርጉለት ነው፡፡

ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን አፍርሰው በጋራ ለመጠቀም ተባብረው የሚሰሩ የባሽር መንግስትና ትግሬዎች ግን ሊወጡበት ከማይችሉ ጣጣ ውስጥ የገቡ ሲሆኑ በቅርብ ቀን መስመጣቸው አይቀርም፡፡ ወታደር የሆነ ባሽር ልክ እንደ ትግሬዎች ስልጣን የያዘ በጉልበት ነው፡፡ በሰልጣን ላይ 28 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ያረጃና በጣም በሽተኛ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት በወንጀለኛነት ተከስሶ ለመያዝ የሚፈለግና እንደፈለገው መንቀሳቀስ የማይችል ወንጀለኛ ነው፡፡ ከ6 አመት በፊት ምንዛሬው ከ3 ዶላር በታች የነበር የሱዳን ፓውንድ አሁን ከ23 ዶላር በላይ ደርሷል፡፡ 35 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት፣ ድሃ የሆነች፣ ማእቀብ የተጣለባት፣ በጦርነት የምትታመስና የተገለለች ሱዳን የውጪ ብድር ከ53 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከ75 በመቶ በላይ ጥቁር አፍሪካዊ እና ቀሪው ደግሞ ሀበሻዊ፣ ሜሩን፣ ኑቢያ፣ ቤጃና የመሳሰሉት የሰው ዘርን ነን በሚል ሰበብና በ407 ብህረሰቦች በጎሳና ሌላም መከፋፈል ተጨምሮበት ሱዳን የተመሰቃቀለችና በጦርነት የምትታመስ ሀገር ስትሆን መፍረሷ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡

በዚች አይነቷም ላይ ነው ተስፋ በመጣልና ታማኝ አገልጋይ በሪያ በመምሰል እያጎበደዱ ትግሬዎች ከሱዳን ጋር በማበር ሀገራችንንና ህዝባችንን የሚጎዱና በጣም ለምና ጠቃሚ የሆነን የኢትዮጵያ መሬት እንደ ቡና ቁርስ ከጎንደር እየቆረሱ ለሱዳን የሚሰጡ፡፡ መሆን የነበረበት ግን ሱዳን የመሬት ጥያቄ በኢትዮጵያ ላይ ካላት በግልጽ በመውጣት በህዝብና በህግ ፊት ቀርበው ምክንያታቸውን ከነመረጃው በማቅረብ ኢትዮጵያን በትክክልና በብቃት ከሚወክሉት ጋር መከራከርና ውሳኔውን መቀበል ነው፡፡ ይህ ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በድብቅና በምስጢር ለሁለቱ የጋራ ጥቅም በሚሆን እየተስማሙ የኢትዮጵያን መሬት መውሰድ ግን ወረራ ሲሆን ቦታው የትም ስለማይሄድ ትግሬዎች ሲባረሩ በኢትዮጵያዊያን የጋራ ሀይልና ጥረት መመለሱ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያኖች ግን በተለይም ምሁሮች በእውቀታቸውና ችሎታቸው እስከ አለም ፍርድ ቤት በመድረስ የወያኔዎችን ወንጀል ማጋለጥና ሱዳን የምትወስደውን የመሬት ስጦታ በመረጃ በተደገፈ መቃወምና ተቀባይነት እንደሌለው ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ጀግና ጎንደሬዎች በጀግንነታቸው በመቀጠልና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የሱዳንን ወራሪ ሀይል መጋፈጥና ማጥቃት ግድ የሚል ነው፡፡ የሱዳን ወራሪ ሀይል ከትግሬ ወያኔዎች ጋር በመተባበር በጎንደር በኩል ሀገር እየወረሩና ህዝብን እየወጉ እንደሆኑ የሚታወቅ ሀቅ ነው እና ሁለቱንም ጠላቶች ጨክኖ ማጥቃት ግዴታ ሲሆን የህልውናና የመብት ጉዳይ ነው፡፡ አድማሱንም በማስፋት በጉሙዝ ማለትም በመተከልና በቤሻንጉል በኩል ከሚገኙ መሳሪያ ያነሱ የሱዳን ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር ግንኙነት ማድረግና በጋራ ሱዳንን ማጥቃት ግድ ይላል፡፡

ጎንደርን ጨምሮ የወልቃይት በትግሬዎች መወረር፣ በጎጃምና በአጠቃላይ በአማራ ላይ እየደረሰ ያለን የትግሬዎች ወንጀል የሚያንቀሳቅሰው ሞተሩና የሚያስሄደው ነዳጅ ዘመናት ያስቆጠረ የሱዳን እርዳታ ነው፡፡ በጦርነት እየታመሰችና በተለያየ ችግር እየሰጠመች ያለች ሱዳን ግን ትግሬዎችን በረጅም የምታዋጣቸው ስለመሆኗ በቅርብ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትቅደም

ገረመው አራጋው

 

መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል -ምሕረት ዘገዬ


ፈረንጆች “Charity begins at home.” ይላሉ፡፡ እንዲህ ሲሉ መልካምነት ወይም በጎነት ከቤት እንደሚጀምር ለመግለጽ ነው፡፡ እኔም ከዚህ አባባል ኮርጄ “መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል” አልሁ፡፡ በመሠረቱ ከቤት የማይጀምር ነገር የለም፡፡ ከቤት የሚጀምር ነገር በጎም ሆነ ክፉ በውጭም ይታያል፡፡ ከቤት ያልጀመረ ከውጭ አይመጣም፡፡ ስለዚህ የብዙ ነገሮች መሠረት ቤት ነው፡፡ የሰው ዕድገት የሚጀምረው ከቤት በመሆኑ ቤታችን በኛነታችን ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ “እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ” መባሉም ለዚህ ነው፡፡

እናትና አባት መልካም ሰዎች ከሆኑ በአብዛኛው ልጆችና የልጅ ልጆችም መልካም የመሆናቸው ዕድል የሰፋ ነው፡፡ በተቃራኒው እናት ክፉ ብትሆን ሴት ልጆቿ የእርሷን መጥፎ አርአያ ተከትለው ክፉ የመሆን መጥፎ ዕድል ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ለአብነት ባሏን የምታታልል ሚስት ማታለል የፅድቅ ሥራ እንደሆነ ያህል የምታምን ልጃገረድ ነው ለማኅበረሰቧ የምታበረክተው፡፡ ባል ሰካራምና አምሽቶ የሚገባ በድራቦሹም በሥራ ስትደክም የዋለችዋን ባለቤቱን የሚያንገላታና በስካር መንፈስ በመነዳት ቤተሰቡን የሚያምስ ከሆነ ወንዶች ልጆቹም ሲያድጉ የርሱን ባሕርይ በመያዝ ቤታቸውን የሚበጠብጡ ይሆናሉ፤  ዕድል ከዚህ ካልሰወራቸው፡፡

መግቢያየ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ለአንድ ሀገር አመራርም እንበለው አስተዳደር ከጥሩ ቤተሰብ መውጣት ወሳኝ ነው፡፡ ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ የሀገራችንን የአስተዳደር ልጓም የሚይዙ ዜጎቻችንን አስተዳደግና የልጅነት ባሕርይ ብናጤን ምናልባትም ብዙዎቹ ለተቆናጠጡት ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት የሚያበቃ የኋላ ታሪክ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ወደ እገሌና እገሌ አልገባም፡፡

ይህችን መጣጥፍ ለመክተብ ያነሳሳኝ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ሰምቼ ነው፡፡ እባካችሁን ወደየአእምሮኣችን እንመለስ፡፡ የኛን የተጣመመ ባሕርይ ከማቃናትና ከመግራት በተጓዳኝ የልጆቻችንን የወደፊት ሕይወት የተበላሸ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥረት እናድርግ፡፡ የሰማሁት ነገር በጣም አደገኛና ሀገርን የሚያጠፋ ነው፡፡ ከዚህ ጠማማ መንገድ በአፋጣኝ  ካልተመለስን በየጓዳችን የተጠመደው ፍንጅ ጊዜ እየጠበቀ የሚፈነዳና ማንንም ከማንም ለይቶ የማይምር ነው፡፡ ሕወሓት በከፈተልን የጥፋት ጎዳና እየተመምን ዘር እንኳ እንዳይተርፍ በጣም አደገኛ አቅጣጫ እየተከተልን ነው፡፡ በዛሬ ውስጥ ሆነን በየቤታችን የምነሠራው ነገር ነገ በግልጽ የሀገራችንን መፃዒ ዕድል እንደሚወስን መጠራጠር የለብንም፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች ከምነግራችሁ አሳዛኝ ተሞክሮ ብዙ መማር እንደሚገባን ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡

አንድ የወያኔ ሚኒስትር ነው፡፡ ለሰዎች ደኅንነት ስል የማንንም ስም አልጠቅስም፡፡ ሚኒስትሩ ዘመድ ይሞትበታል፡፡ ከረምረም ብሎ ጓደኞቹ ሊጠይቁት ሰብሰብ ብለው ወደቤቱ ይሄዳሉ፡፡ ልቅሶው ስለሰነበተ ቴሌቪዥን ተከፍቶ እንግዶቹም ቤተሰቡም ይመለከቱ ነበር፡፡ በዘመናዊ ቤተሰብ ውስጥ እንደዱሮው የመረጃ ምንጭን ለረጂም ጊዜ መዝጋት ተገቢ አለመሆኑ መረሳት እንደሌለበትና ሚኒስትሩም ያደረገው ከዚህ አኳያ መጥፎ እንዳልሆነ ይታሰብልኝና በዚህ የቴሌቪዥን ሥርጭት ሳቢያ የተከሰተው ነገር ግና ሁላችንንም የሚያስተምር፣ ከተኛንበትም የሚያነቃ አቢይ ቁም ነገር ነው፡፡

ሚኒስትሩና ጓደኞቹ የደራ ጨዋታ ይዘዋል፡፡ በነገራችን ላይ በወያኔው የዘር ፖለቲካ አገላለጽ መሠረት ሰዎቹ ሳይወዱ በግዳቸውና ባጋጣሚ ከሦስቱም “በጥባጭ” ነገዶች የሚወለዱ ናቸው፡፡ ሚኒስትር ተብዬው ደግሞ ኦሮሞ ነው፡፡ ‹ተብዬው› ማለቴ በዚህ ሥርዓት አእምሯዊ የጤንነት ደረጃውንና ትምህርታዊ የብቃት መሥፈርቱን አሟልቶ የሚሾም ሰው እንደሌለ በሚገባ ስለምረዳ ነው፡፡ በስህተት ተሹመህ “ሰው” መሆንህ ቢደረስበት ተዋርደህና አለሥራህ ሥራና አለስምህ ስም ወጥቶልህ በአናቱም ላይ “ሙሰኛ” የምትለዋን የነሱን የሠርክ ስም ተሸልመህ ወደ ዘብጥያ ልትወርድ ትችላለህ፡፡ ወያኔ ጋ ቀልድ የለም፡፡ ጤናማ አስተሳሰብና አመለካከት እንዲሁም ብሔራዊ የሀገር ፍቅር ስሜት ካለህ በምንም ዓይነት የኃላፊነት ቦታ ላይ አትሾምም፤ ሰው መሆንህ እስኪያጠራጥር ድረስ እጅግ የዘቀጠ ስብዕና እንዳለህ በአደባባይ ካልተመሰከረልህ የወያኔን ሹመት አታገኛትም (ሹመት ከፈለግህ ማሟላት ስለሚገባህ መሥፈርት ፍንጭ ልስጥህ – ሰካራምነት፣ ውሸታምነት፣ ዘሟችነት፣ ሙሰኝነት፣ ጎጠኝነት፣ አጨብጫቢነት፣ አላዋቂነት….)፡፡ ባለሥልጣናቱ “ሰው” መሆን ከፈለጉ በድብቅ ነው ሰው መሆን የሚችሉት፡፡ ዐዋቂና ምሁር መሆን ካማራቸው እነዚህንም መሆን የሚችሉት በሥውር ነው፤ ከተነቃባቸው ይባረራሉ፡፡ አሃ፣ ሰው ከሆኑማ “እንዴት”ንና “ለምን”ን ዐወቁ ማለት እኮ ነው፡፡ “ለምን?” ብለህ መጠየቅ ጀመርክ ማለት ደግሞ ጤናማ ሰው መሆን ጀመርክ ማለት ነውና ወያኔ አለቀለት ማለት ነው፡፡ ወያኔ ጋ ለመኖር ጭንቅላትህን ቦርጭ ካለህ እዚያ ውስጥ ወትፈህ አለበለዚያም ዘመድ ካለህ በአደራ መልክ አስቀምጠህ ባዶ ቀፎህን ነው መግባት ያለብህና የምትችለውም፡፡ በዚህ ዘመን ለትልቅ ሥልጣን የሚታጩትና የሚሾሙትም ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ በመብራት እየተፈለጉና ሥይጠናም(ሥልጠና) እየተሰጣቸው ነው፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ደቡቦች በከፍተኛ ደረጃና በብዛት እየተሾሙ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አማራ ጠሉ ኃይለማርያም በቀደደው የአሻንጉሊትነት የሥራ መደብ ደቡባውያኑ አልተቻሉም አሉ፡፡ ኧረ ደቡብ ከተነሳስ አይቀር ብዙ መዘዝ መጥቶብናል እናንተዬ! (በጨለማ ሰውን የሚደፉ ወጣቶች ከደቡብ እየፈለሱ አዲስ አበባን እየሞሉና ዜጎች እንደደሮ በ12 ሰዓት ወደ ቆጣቸው እንዲከቱ በመገደድ ላይ ናቸው ይባላል፡፡ በቆንጨራና በኮብል ስቶን ማጅር ማጅሩን እያሉ በተለይ “ንዑስ ከበርቴ”ውን የኔ ቢጤ  ድሃ እየፈጁት እንደሆነ በስፋት ይነገራል፤ ወይ ዕዳችን! “አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ” አሉ? የዘንድሮ ዘንድሮስ ከምንጊዜውም ዘንድሮዎች ለዬት አለች፡፡) ስንክሳሩ ብዙ ነው ወንድሜ፡፡….

የዚያን ጣጠኛ ቲቪ ነገር ቀጠልኩ፡፡ በኦሮምኛ ቋንቋ ይተላለፍ የነበረው ዝግጅት ተጠናቅቆ የአማርኛው ሊቀጥል ሲል ይሉኝታንና መደባበቅን የማያውቀው የሚኒስትሩ ትንሽዬ ልጅ “እነዚህ ጭራቆች ደግሞ መጡ!” ይልና ቴሌቪዥኑን ጥርቅም ያደርገዋል፡፡ ሚኒስትሩም ጓደኞቹም ባለቤቱም ክው አሉ፡፡ አያ ሚኒስትር አፉ እየተሳሰረ የሞት ሞቱን “ሕጻን እኮ ነው፤ ም….ምን ያ’ቃል? ብላችሁ ነው፡፡” ይላል፡፡ የኦሮሞም የአማራም ደም የነበረው አንዱ የተማረ ጓደኛው “አይ፣ የእናንተን ይዞ እንጂ ይህ ሕጻን ከራሱ ምን አለውና እንዲህ ይላል?” በማለት በአማርኛ ይናገራል፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ በእኩልነትና በፍትህ ሊያስተዳድር በሚኒስትርነት ማዕረግ በወያኔ የተሾመው ሚኒስትር በኦሮምኛ “አንተ! በነዚህ መሃል እንዲህ ትለኛለህ?…” በማለት በትግሬዎችና በአማራዎች ፊት ሊያሳጣው እንደማይገባ በወቀሳ መልክ ጠቆም ያደርገዋል፡፡ ያ ሰው ከልቡ ሰው ነውና ቋንቋ ሳይቀይር (ኮድ ሳይለውጥ) በአማርኛ “አዎ፣ ችግሩ የኛ የአሳዳጊዎች ነው፡፡ ጥላቻን እየጋትን እናሳድጋቸዋለን፤ ሲያድጉም ያን ተግባራዊ እያደረጉ እርስ በርስ ከመጋጨትና ከመነታረክ ውጭ ሌላ የሚጠቅም በጎ ነገር አይሠሩም፡፡…” ይለዋል፡፡ የጨዋታ አጀንዳ ይለወጥና ሰላምም ይወርድና በቤቱ ውስጥ ሕይወት እንደአዲስ ትቀጥላለች፡፡

ቴሌቪዥኑ ግን አልተዘጋም ነበር፡፡ ተራውን ጠብቆ የባሰው መጣ፡፡ አማርኛው አለቀ – (ያው የነበረውም እንደነገሩ ለወጉ ያህል እንጂ አማርኛ እንኳን አሁን አሁን እየሞተች ነው)፡፡ ትግርኛው ሊቀጥል “ጥእና ሃበለይ ዝተፈተውኩም ተኣዘብትና…” የሚል አስገምጋሚ የትግርኛ ጋዜጠኛ የቲቪው መስኮት ላይ ድቅን ይላል፡፡ ያ ሕጻን ያ ትግራዋይ ጋዜጠኛ የጀመረውን የእንኳን ዋላችሁ/አመሻችሁ ዐረፍተ ነገር እንኳን እስኪጨረስ አልጠበቀውም፡፡ “ምናባታቸው እነዚህ ዐውሬዎች!” ይልና አሁንም ድርግም ያደርገዋል፡፡ ሚኒስትሩና ባለቤቱ የሚገቡበትን አጡ፡፡ በየቤቱ ይህን መሰል ጉድ ሞልቷል፡፡ ገመና ሸፋኙ ቤት ይሸፍነዋል እንጂ፡፡

ኢትዮጵያ ማለት እንዲህ ሆነች፡፡ ከዚህ ገፋ አድርጌ ብናገር ደስ ባለኝ ፡፡ ነገር ግን ሰዎችን ላላስፈላጊ መስዋዕትነት መዳረግ ነው፡፡

ምን አይታችሁ – ወያኔዎች የዘሩትን ገና በብዛትና በዓይነት ያጭዳሉ፡፡ የዘራውን የማያጭድ ገበሬ የለምና፡፡ ማን ተጠቃሚ ማን ተጎጂ እንደሚሆን የወደፊቱ ታሪካችን በግልጽ ይመሰክረዋል፡፡ ወያኔዎችን ስታዘባቸው ባሏን የጎዳች መስሏት የገዛ ገላዋን በጋሬጣ የተለተለችውን ጅላጅል ሚስት ይመስሉኛል፡፡ የዘሩት የጥላቻ መርዝ ወደነሱ እንደማይዞር ያሰቡት አይመስሉም፡፡ በአማራ ላይ ያላቸው ጭፍን ጥላቻ እነሱንም ሀገሪቱንም ወደማይወጡት አዘቅት እየከተታቸው ነው፡፡ የሚሾሙት ሆድ አደር ሁሉ አማራንና ኢትዮጵያን የሚጠላ ይምሰላቸው እንጂ እነሱን እንደሚወድና እንደማይወድ እንኳን ለማወቅ ግድ ያላቸው አይመስሉም፡፡ እናም ለአማራ የጣዱት የወጥ መቀቀያ ጎላ ውስጥ እነሱም ገብተው ሊንፈቀፈቁ  እንደሚችሉ አልተገለጠላቸውም – እንደወያኔ ልበ ሥውርና አእምሮ-ድፍን መቼም የትም የለም –  በዘወትር ጸሎታችን “እጅግ ቸርና ሩህሩህ አምላክ” ብለን የምንጠራው እግዚአብሔር እነዚህን ወያኔዎች እንዲህ የጨከነባቸውና ባልጩት ራስ አድርጎ የፈጠራቸው ለምን ዓላማና በመጨረሻው ምን ሊያደርጋቸው ዐቅዶ እንደሆነ ሳስበው ሁል ጊዜም ይገርመኛል፡፡ ሌላውን ሁሉ ተውት፡- ከትግራይ ሕዝብ በግርድፍ ግምት ከ60 እስከ 70 በመቶው በአሁኑ ሰዓት የሚኖረው የት ነው? ይህ ሕዝብ ደላውም አልደላውም በስማቸው አተረፍም አላተረፈም እየኖረ ያለው ግን ከቀሪ ወንድምና እህቶቹ  ጋር ከትግራይ ክልል ውጭ ነው – ውጭ ሀገራትን ጨምሮ፡፡ ታዲያ ወያኔዎች ለሌላዋ ኢትዮጵያ ከሚያጠምዱት ቦምብና ፈንጅ ይህን ብዙ ትግራዋይ እንዴት ሊያድኑት ይችላሉ? እነዚህ ሰዎች ሁል ጊዜ የሚያቅዱት ዕቅድ “ሀ”ን ብቻ እንጂ ዕቅድ “ለ” የሚባል ከችግር መውጫ ብልኃት ኖሯቸው የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ያው “ደፋርና ጭስ… “ እንደሚባለው በብላኔ የሚገቡበትን ጣጣ ሁሉ በብላኔ ይወጡታል፤ ይህ የዕውር ድምብር አካሄዳቸው እስካሁን ብዙም ያከሰራቸው አይመስልም፤ እንጂ ለሠርገኛ ጤፍ የተዘጋጀ ብረት ምጣድ ቀይና ነጭ ጤፍን መርጦ ሳይቆላቸው እንደሚቀር ለሕወሓት ብቻ እንዴት ተገለጸለት? ሁል ጊዜ የሚገርመኝ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው አሁን እዚህ አለቦታው የደነቀርኩባችሁ፡፡ ወደጀመርኩት –  እያንዳዱ የአሁን ዘመን ባለሥልጣን – አማራም ቢሆን – ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ መሆን እንዳለበት የሕወሓት ፅኑ እምነት ነው፤ መለስም “ሥልጣን የምንሰጠው በታማኝነት እንጂ በትምህርት ብቃትና በችሎታ አይደለም” ብሏል በግልጽ፡፡ ስለዚህም ነው አለምነው መኮንንን የመሰለ የወያኔ ዕንባ ጠባቂ ባሕር ዳር ላይ አማሮችን ጠፍንጎ ለማሰር በወያኔ ተሹሞ የምናየው፡፡ ስለዚህም ነው ገነት ዘውዴን የመሰለች ከወያኔ በልጣ ስለወያኔ የምትብከነከንና የምትጨነቅ ሲሞቱባትም ከሚስቶቻቸው በበለጠ ሙሾ የምታወርድ የአማራ ዮዲት ጉዲት “ወላድ አትይሽ”ን ልንመለከት የቻልነው፡፡ ብዙ ምሣሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ አትታዛቡኝና ይሄ ነገር የድግምት ይመስለኛል፡፡ የመረገምም ጣጣ ሳይኖርበት አይቀርምም እላለሁ፡፡ አንድ ለሂትለር ያደረ ይሁዲ ሌላ ምሥኪን ይሁዲን ይዞ በኦሽትዊዝ የጋዝ ቼምበር አስገብቶ በይሁዲነቱ ምክንያት ሲያቀልጠው ይታያችሁ – ከዚህ በላይ ዕንቆቅልሽ ደግሞ ሊኖር አይችልም፡፡ በመሠረቱ አማራ ሆኖ ትግሬ መሆን ወይም ትግሬ ሆኖ አማራ መሆን በራሱ ምንም ማለት አይደለም፤ የምርጫ ጉዳይም ነው፡፡ ነገር ግን አልተፈጠርኩበትም ብለህ የካድከው ነገደም ቢሆን የመኖር መብት እንዳለው ማመን ይገባል እንጂ ገና ለገና ለሆድህም ይሁን አንዳች ነገር ተዙሮብህ ክደህ የወጣህበትን ማኅበረሰብ ሊያጠፉት ከተሰለፉ ወገኖች ጋር ተደርበህና ተባበብረህ ለማጥፋት መነሳት በዕብድነት ብቻም አይገለጽም፡፡ ከዕብደትም በላይ ነውና እንዲህ ዓይነት ሰው መመርመር አለበት፡፡ የዲኤንኤው ስብጥር (ኮምፖሲዚሽን) ተመርምሮ መታወቅና ህመሙ እንዳይዛመት ክትባት ሊፈጠርለት ይገባል፡፡  ለወደፊቱ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ምሁራን አንድ በሉን፡፡

ለማንኛውም በዚያ ከእህልና ግፋ ቢል ከፊደል ዘር መለየት ያላለፈ ችሎታና ዕውቀት ሊኖረው ከማይጠበቅ ሳይወድ በግዱ ጃዋር ሞሀመድን እንዲሆን ከተፈረደበት ኢትዮጵያዊ ሕጻን ብዙ የምንማረው ነገር አለ፡፡ አባትና እናቱ አጥፍተዋል፡፡ ማንንም ማሳበብ አይችሉም በትልቁ ነው ያጠፉት፡፡ እነሱ ንስሃ ይግቡ፤ ይጸጸቱና ወደደጉ መንገድ ይመለሱ፡፡ ለነሱ ከዚህ በላይ ምክር የለኝም፡፡

ወደኛ ልመለስ፡፡ እኔም ልጆች አሉኝ፡፡ አንቺም ልጆች አሉሽ፡፡ አንተም ልጆች አሉህ፡፡ እናተም ልጆች አሏችሁ፤ ባይኖሯችሁም እንኳን የኛ ልጆች የናንተም ናቸው፡፡ ሀገር የምትገነባው ወይም የምትፈርሰው  ከሕጻናቷ ጀምሮ ነው፡፡ ከታች የጠፋ ከላይ ቢፈልጉት አይገኝም፡፡ እባካችሁን የኛን ስሜት በልጆቻችን ላይ ለመጫን አንሞክር፤ ልጆቻችንን የእምነቶቻችንና የጥላቻ ማቆያ ማኅደሮቻችን ከማድረግ እንቆጠብ፡፡ የራሳቸው ስብዕና እንዲኖራቸው እንጂ የኛ ጥላዎች ወይም ሲዲና ዲቪዲዎቻችን አድርገን አንጠቀምባቸው፡፡ ታሪክ እንሥራ፡፡ ቢያንስ ነገን ለነሱ እንተውላቸው፡፡ የኛን ዘመን አበላሽተን የነሱንም አናበላሽባቸው፡፡ በጥላቻ አናሳድጋቸው፡፡ ፍቅርንና መዋደድን እናሳያቸው፡፡ የኛ ስህተት የኛን ሕይወት አጨለመ፡፡ በዚያም ምክንያት የረባ ሕይወት ሳንኖር እንደአባ መሸ በከንቱ እንዲሁ ጊዜያችን ተቃጠለ፡፡አንድ ጊዜ ተፈጥረን አንድ ጊዜ ብቻ በምንኖርባት ምድር ብዙ ዕድሎችን አበላሸን፡፡  የልጆቻችን ጊዜስ ለምን በከንቱ ይቃጠላል? በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ እንነጋገር፡፡ በተለይ ሰለጠነ በሚባለው ዓለም ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እስካሁን የገነባችሁትን የልዩነት አጥር አሁኑኑ አፈራርሱና ቢያንስ ልጆቻችሁ በፍቅርና በመተሳሰብ የሚኖሩባትን የጋራ ሀገር ለመፍጠር ሞክሩ – ሰው እንዴት በቤተ አምልኮትና በጽላት ሳይቀር ይጣላል?(አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኪሮስ… እያለ ታቦታትንም በጎሣና በነገድ የሚከፋፍል ምን ዓይነት ትውልድ ላይ ደረስን?)፡፡

የሰው ወርቅ አያደምቅም፡፡ ዝንታለሙን በሰው ሀገር መኖርም የሚቻል አይደለም፤ ቢቻልም የማንነት ጥያቄያችንን በአግባና ዘለቄታ ባለው መልክ አይመልስልንም፡፡ በጥቅሉ ሲታይ  አካሄዳችን አያምርምና በአፋጣኝ እንለውጠው፡፡ ከሁሉም የነሣን ሆነን በኋላ ቀርነት አለንጋ ተገሽልጠናል፡፡ ሀገራችንን ከተጠመዱባት ፈንጂዎች ነፃ እናውጣት፡፡ አንዱ ዘዴ ልጆቻችንን በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲኖሩ መምከርና በተግባርም ማሣየት ነው፡፡ በየቤታችን ይህን ዘመቻ ብናጧጡፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እናመጣለን፡፡ ወያኔ የዘራውን መርዝ የምናረክስበት በርሱ መንገድ በመጓዝ ሳይሆን በተቃራኒው ፍቅርን በመዝራት ነው፡፡ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ፣… የእግዜር ፍጡራን እንጂ አንዳቸው አንዳቸውን እንደድብኝት ጠፍጥፈው የሠሩዋቸው የሸክላ ውጤቶች አይደሉም፡፡ ያለፈ ችግር መኖሩ ብዙዎችንን ሊያሳምን ይችላል፤ እንኳንስ በማኅበረሰብና በሀገር ግንባታ በቤተሰብ ደረጃ እንኳን ብዙ ችግሮች እየደረሱ በዕርቅና በስምምነት ግን ቤትና ትዳር እየታደሰ ከቀድሞው ወደተሻለ ትልቅ ደረጃ ይደረሳል፡፡ የኛ ባልሆነ ጊዜ በተፈጠሩ ችግሮች የኛ የሆነን ጊዜ በከንቱ ማበላሸትና ማባከን ብልኅነት አይደለም – ሞኝነት እንጂ፡፡ በማንትስ ጊዜ የደነቆረ ማንትስ ይሙት እያለ ይኖራል እንደሚባለው አንድ ወቅት በተፈጸመ ስህተት ዝንታለሙን ማሞስካትና ሕዝብን ሆድ ማስባስ ጤነኛነትን ካለማሳየቱም በላይ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ቅኝታችን ከሰላምና ከዕርቅ ውጭ ሆኖ ባለፈ ነገር ብቻ መብከንከን ከሆነ በዚህች ሀገር ማንም በሰላም አይኖርም፡፡ በሰላም ለመኖር የሚከፈል መስዋዕትነት ደግሞ በግድ በደም ብቻ የሚሰላ ሊሆን አይገባም፡፡ በፍቅርም ጠላት ተብሎ የተፈረጀን ወገን ማንበርከክ ይቻላል፡፡ በይቅርታም ወዳጅ ማፍራትና የተቀያየሙትን ኃይል ማቅረብ ይቻላል፡፡ በእልህና በቂም በቀል የትም መድረስ እንደማይቻል እኛ ኢትዮጵያውያን ኅያው ምሥክሮች ነን፡፡ የከረረ ይበጠሳል፤ ከተውት ግን ይመለሳል፡፡

ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ጫፍ ወደመሀል ሲሰባሰቡ ይታየኛል፡፡ ሀገራችንን ፈጣሪ ይባርክልን፡፡ ከሃይማኖት ጽንፈኞች፣ ከወያኔ ወጥመዶች፣ ከሙስና አሜከላዎች፣ ከሞራላዊ ዕሤቶቻችን ቀበኞች፣ ከማይምነት ጥቁር ግርዶሽ፣ … እግዚአብሔር ሀገራችንን በቶሎ ነፃ ያውጣልን፡፡ ደግሞም በርትተን እንጸልይ፡፡ ከ2000 ዓመታት በላይ በዓለም ዙሪያ ተበታትነው የነበሩ እስራኤላውያንን እንኳ ቃል ኪዳኑን ጠብቆ  የታፈረችና የበለጸገች የአንዲት ሀገር ባለቤት አድርጓቸዋል፡፡ እኛ ደግሞ ለርሱ ከነርሱ እንበልጥበታለን፤ ሀሰት አይደለም፡፡ “እናንተስ ለኔ እንደኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” ብሎ ፈጣሪ ስለኛ ለነሱ የተናገረው ስለሚወደን ነው፡፡ እኛ አምነነዋል፤ እነሱ ግን ገና አላመኑትም፡፡ ስለዚህ ተስፋችን እርሱም ነው፡፡ የኛ የኃላፊነት ድርሻ ግን ትልቁ ነው፡፡ ምክንያቱም “አዳም ሆይ! በላብህና በወዝህ ጥረህ ግረህ ብላ” ተብሎ ወደ ምድር ወርዷልና ቢያንስ አሻሮ እንኳን ሳንይዝ ወዳለው – ወደፈጣሪ – መጠጋት ስንፍና መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

Mz23602@gmail.com

posted bv Gheremew Araghaw

ጣራው ለሚያፈስ ቤት -የወለል እድሳት (ይገረም አለሙ)

መላ አከላቷን ዝንጀሮ እሾህ ወግቷት
መቆም መራመድ መቀመጥ ተስኖአት
የትኛውን እንንቀልልሽ ብለው ቢጠይቋት፣
ብታስቀድሙልኝ የመቀመጫየን
እኔ እነቅለዋለሁ ቁጭ ብዬ ሌላውን፣
በማለት መለሰች ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር ስላወቀች፡፡

ጣሪያው በሚያፈስ ቤት ውስት እየኖሩ ክረምት በመጣ ቁጥር እየተሰቃዩ በጋ  ሲሆን የወቅት መለዋወጥ የተፈጥሮ ባህርይ መሆኑ ተዘንግቶ ነገር አለሙን በመርሳት ወለሉን ቢያድሱት ግድግዳውን ቀለም ቢያብሱት አይቀሬ ነውና ክረምት ሲመጣ የሚሆነውን አስቡት፤ከንቱ ልፋት አጉል ብክነት፡፡

የቤቱ ወለል እድሳት ቢሻ፣ ግድግዳው ቀለም ቢያምረው፣ ጣራው ደህና እስከሆነ ድረስ መኖር አይከለክልምና ቅድሚያ መቀመጫየን እንዳለችው ዝንጀሮ መቀመጫን አስተካክሎ ሌላ ሌላውን በሂደት ቀን ሲፈቅድ አቅም ሲጎለብት ማደስ ይቻላል፡፡ ጣሪያው የሚያፈስ ቤት ውስጥ እየኖሩ ክረምቱ አልፏል ብሎ ወለል ማደስ ቅድግዳ ቀለም መቀባት ግን አንድም ሞኝነት ሁለትም አጭበርባሪነት ነው፡፡እንዲያም ሲል ከዛሬ ያለፈ አለማሰብ ይሆናል፡፡በአን ጎራ ካለነው እኛ ከምንባለው እነማን ከየትኛው ጎራ እንደሆኑ  እናንተው አስቡት፡፡

ሀገራችን ቤታችን ናት፤ ጣራዋ በብልሽትም በእርጅናም ተበለሻሽቶ በበጋ ለጸሀይ ሀሩር፣ በክረምት ለዝናም ዶፍ ብንዳረግም  ለምደን ተላማምደነው  እንኖራለን፡፡ገዢዎቻንም የእኛ ቻይነት፣ የፈረንጆቹም ጩኸት እንዴትነት ገብቷቸው ወለሉን እያደሱ፣ ግድገዳውን ቀለም እየቀባቡ  ለአላፊ አግዳሚውም ሆነ ለደርሶ ሀጅ ጎብኝው ችግሩ አንዳይታወቅ አንደውም ያማረ የሰመረ መስሎ አንዲታይ በማድረግና መኖሩን ችለውበታል፡፡ ያማረው ቤታችን ሞንዳላው ኑሮአችን እያሉ በሚያሰሙት ፕሮፓጋንዳም እኛን እያደነቆሩም አቀጣጫ እያሳቱም ከፈረንጆቹ ጋር እየተሞዳሞዱ ረብጣው ሳይነጥፍባቸው፣ ዲፕሎማሲያዊው ድጋፍ ሳይቋረጥባቸው፣ሲገድሉና ሲያስሩ የሚሰማው ተቃውሞም ከቃል ወደ ተግባር ሳይሸጋገርባቸው ሀያ ስድስት ዓመት እንደዋዛ ገዙን፡፡ ሁሉንም ነገር አይተው ገምተው ጠብ- መንጅቸውንም ተማምነው ገና አርባ አመት አንገዛችኋለን እያሉ ነው፡፡ ይበሉ! የታገሉት ለምንና ለማን ሆነና፡፡ ጥያቄው እኛ የምንባለው ከተቃውሞው ጎራ ያለነው ብዙ እኛዎች ያለፈውን የሰሩትን እያየን የወደፊት ምኞት ዝግጅታቸውን እየሰማን ምን አልን ምንስ አደረግን ነው ? ብዙዎቻችን ካለንበት ነቅነቅ ያላልነው  ከመማረር ወደ ማምረር ተሸጋግረን  ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ አውርደን ከመጯጫህ ወጥተን  አገዛዝ በቃን በማለት  የምንችለውን ጠጠርም ቢሆን ለማስቀመጥ ዝግጁ ነን ወይ? ነው ጥያቄው ይህ ካልሆነ ወያኔ ከምኞት ፍላጎቱም በላ ይገዛናል፡፡ አንደ አያያዛችን ከሆነ ብዙዎቻችን በአፋችን እንጮሀለን እንጂ በወያኔ የተፈጸመው ነገር ሁሉ ውስጣችን ዘልቆ አልተሰማንም ለዚህም ነው ከመማር ወደ ማምረር መሸጋገር ያልቻልነው፡፡ ይህ ባይሆንማ ኖሮ ወቅት እየጠበቀ ወያኔ በሚሰጠን መጫወቻ ከአንልፋችን እየባነንን በምናሰማው ውግዘት ጩኸት  ጣሪያው ለሚያፈስ ቤት የወለል እድሳት የምንጠይቅ ባልሆነ ነበር፡፡ በእኔ እምነት ጣራው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነው፡ እንደ አብርሀም ሊንከን አባባል የህዝብ፣ በህዝብ፣  ለህዝብ፣  የሆነ መንግሥት ፡፡ ስለሆነም ይህ በሌለበት/በተነፈግንበት/ ሀገራችን  ሌሎች የህግም በሉት የሰብአዊ መብት፣ የቋንቋም በሉት የሀይማኖት ጥያቄዎችን ማንሳት  ታሰርን ተሰደድን ተገደልን እያሉ መጮህ ከሂደቱ ለማትረፍ እንጂ ከግቡ ለመድረስ የማንታገል ያስመስላል፡፡

ዴሞክራሲ ቅንጦት ተደርጎ በሚታይበት አገዛዝ ውስጥ እየኖሩ ስለ ቋንቋ፣ስለ ሀይማኖት፣ስለ ብሄር ብሄረሰብ፤ስለ ህግ በላይነት፣ስለ ሰብአዊ መብት መከበር ስለ ነጻ ምርጫ ወዘተ ማሰብ፣  መጠየቅ፣ መጮህ ጣራው በሚያፈስ ቤት እየኖሩ ወለል ለመቀየር ግድግዳ ለማደስ የመንደፋደፍ ያህል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ሲሆን ምላሽ የሚያገኙ ናቸው፡ ብቻ ሳይሆን ያለ እነዚህ ተግባራዊነት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊኖር ስለማይችል ወያኔ በሥልጣን ለመቆየት ጠመንጃውን እንደሚተማመን ሁሉ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ለሥልጣን የሚበቃ ግለሰብም ይሁን ፓርቲ እነዚህን ነገሮች ማክበርና ማስከበር የህልውናው ጉዳይ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከፈረሱ ጋሪው የሆነውን መያዣ መጨበጫ ያጣውን ነገራችንን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ በሚያስችለው መንገድ አንደየአቅማችን እንራመድ፡፡ለዚህ ደግሞ ቀዳሚው ነገር ራስን መለወጥ ነው ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ዘመን ተሸጋሪ አባባል ብጠቅስ ማለት የፈለኩትን ይበልጥ የሚያሳይልኝ መሰለኝና እነሆ!

የአሜሪካፕሬዝዳንት የነበሩት አብርሀም ሊንከን ለኮንግረስ ያስተላለፉት ሁለተኛው መልዕክታቸው ተብሎ በሚጠቀሰው ንግግራቸው «አንድ ትውልድ ያልፍና ሌላ ትወልድ ይተካል፣ ዓለም/መሬት ግን ለዘለአለም ትኖራለች፡፡ ጸጥ ረጭ ያለው ያለፈው ግዜ ፍልሰፍናዎች (ዶግማስ) አውሎ ነፋሳዊ ለሆነው ለዛሬው ችግር ለመፍትሄነት አይመጥኑም፡፡ ጊዜያችን ችግር ያዘለ ስለሆነ በአዲስ ሁኔታ ማሰብና በአዲስ ሁኔታም መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ ማውረድ ይገባል፡፡ ያን ግዜ አገራችንን ለማዳን እንችላለን፡፡ ታሪክን ልናመልጥ አንችልም፣ልንሸሸው አይሆንልንም፣ ክፉም ሰራን ደግ እንዘከራለን፣ (እንታወሳለን) ግለሰባዊ መታወቅ ወይም አለመታወቅ አንዳችንንም ሆነ ሁላችንን አያተርፈንም፣የምናልፍበት እሳታዊ ፈተና (ፍርድ) በክብር ወይንም በውርደት ማለፋችንን ይመሰክራል»

ብዙዎች እኛ ፤ እነርሱ ወያኔዎች ምንም በሉዋቸው ምን ባነገቡት ዓላማ ሊደርሱበት በሚያስቡት ግብ አንድ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ አይደለም ሰው ነፋስ አያስገቡም፡፡እንዲህም በመሆናቸው ነው ታግለው ያሸነፉት፣ ሀያ ስድስት ዓመታትም በዙፋኑ ለመዝለቅ የበቁት፡፡ በተቃውሞው ሰፈር ያለነው እኛ ግን ብዙ እኛዎች ነን፡፡ ሰንደቅ ኣላማ ለብሶ ከሚፎክረው፣ ኢትዮጵያ እያለ ከሚዘምረው፣ የብሄር ኩታ ለብሶ ከሚያቀነቅነው ፖለቲከና አይደለሁም እያለ ከሚሸውደው  ወዘተ ብዙ እኛዎች መካከል  የቤታችን ጣራ ተቀይሮ ሁላችንም የጸሀዩ ሀሩር ሳጠብሰን፤ የክረምቱ ዝናም ሳያበሰብሰን መኖር የምችልበት ቤት እንዲኖረን ምን ያህሉ ነን ከምር የምንሻው ተብሎ ቢጠየቅ  ከብዙዎቹ ተግባር በማየት የምናገኘው ምላሽ አሉታዊ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ለወያኔ ግዞት ያመቻቸን መሰረት አልባው ልዩነታችን መሰረት የለሽ በመሆኑ ለገላጋይ ዳኛ ለመካሪ ሽማግሌም የሚመች አይደለም፡፡ ብዙዎች በቤታችን ጣራ መቀየር በየግላቸው ያምናሉ፣ነገር ግን ይህን እምነት የጋራ ለማድረግ ይቸገራሉ፣ለምክንያትነት የማይበቃው ሰበባቸው የሚያሳብቅባቸው ደግሞ ጣራው እኔ በምለውና በምፈልገው መንገድ ካልሆነ በስተቀር ባይለወጥ ይቅር የሚሉ ከራስ በላይ የማያስቡ መሆናቸው ነው፡፡ በግልጽ ቋንቋ ለመናገር እኔ አባዋራ የማልሆንበት ቤት አንኳን ጣራው ግድግዳውም ይደርመስ የሚሉ ነው የሚመስሉት፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ለስሙ ከተቃውሞው ጎራ ከትመዋል እንጂ አድራጎት ንግግራቸው የተቃውሞ አይደለም፡፡ ጣራው እያፈሰሰም ለጸሀይ እየዳረገም ቢሆን ወለሉ ከታደሰ ግድጋዳው ቀለም ከተቀባ ርካታ የሚሰጣቸው አይነት ናቸው፡፡ ያ ባይሆን  ከሀያ ስድስት አመታት አገዛዝ በኋላ ዛሬ ስለ ህግ በላይነት፣ ስለ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ስለ ሀብት እኩል ተጠቃሚነት፣ ስለ ፍትህ ወዘተ ለወያኔ  ማላዘኑ በቆመ ነበር፡፡ እነዚህ ከእባብ እንቁላል እርግብ የሚጠብቁ ሊባሉ የሚበቁ ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀርና ቢረሳን  የህዝቡ ጥያቄ ትክክል ነው፣ የሰጡትን ዝም ብሎ የማይቀበል ጠያቂ ትውልድ ፈጥረናል ወዘተ ብለው ተመጻድቀውና ተሳልቀው ለተቃውሞ መውጣቱም ሆነ ያነሳው ጥያቄ ትክክል ነው ያሉትን ህዝብ በገፍና በግፍ አስረው እያስተማርነው ነው ተሀድሶ እየሰጠነው ነው ከሚሉ ሰዎች ምን ሊገኝ ጥያቄ እንደሚቀርብ ጩኸት እንደሚሰማ አይገባኝም፡፡

እያዩያ አለማስተዋሉ፣እየሰሙ አለማዳመጡ፣ እያነበቡ አለመገንዘቡ በእኛ ሰፈር በመብዛቱ እንጂ ወያኔዎች ከጅምሩ በመቃብራችን ላይ ሲሉ በግልጽ ነግረውናል፡፡ጽፈው አስነብበውናል፣ በተለያየ መንገድ በዘፈንም በፊልም አሳይተውናል፡፡እኛ ሰፈር ግን በምኒልክ ዘመን የደነቆረ ምንይልክ ይሙት እንዳለ ይኖራል እንደሚባለው ሆነን በወያኔ ድል ማግስት የተጀመረው ጩኸት፣ልመና ተማጽኖ፣ ስድብ ዘለፋ የመግለጫ ተቃውሞ  ወይ መሻሻል ሳይሳይ ወይ አርጅቶ ገለል ሳይል እስካሁን አለ፡፡

ሎሬት ጸጋየ  ገብረ መድህን የአባቶቻችን ነገር ሳስታውሰው ትዝ የሚለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ እንዳለው  እስከ ዛሬ የመጣንበት የፖለቲካ ጨዋታ አላዋጣም፣ የያዝነውም ተለይይቶ ጉዞ  ከምንለው ቦታ የሚያደርስ አልሆነም ስለዚህ ራሳችንን ፈትሸን፣ አመጣጣችንን ገምግምን ድክት ጥንካሬአችንን ለይተን፣ለዘመኑ የሚስማማውን አስተሳሰብ እንያዝ፣ ለትግሉ የሚመጥነው መንገድ እንከተል በማለት የሚታትሩ ብቅ ሲሉ ከወያኔ ሰፈር ባልተናነሰ ጩኸቱ የሚበዛውም ሆነ  ትንሽ ትንሽ መሰናክል ማስቀመጥ የሚጀመረው እኛ ከምንባለው ብዙዎቹ እኛዎች በኩል ነው፡፡

ቤቱ ጣራው ዝናብ ቢያፈስም፣ ጸሀይ ቢያስመታም ወለሉ ካማረ፣ ግድግዳው ቀለም ከተቀባባ ለእኔ ይመቸኛል፤ የጣራው ነገር አያስጨንቀኝም ማለት መብት ነው ምርጫ ነው፡፡ ለዴሞክራሲ ነው የምታገለው የሚል ሁሉ ይህን ምርጫ መቀበል የሰዎቹን መብት ማክበር ይገባዋል፡፡እነርሱ ደግሞ ጣራው መቀየር አለበት ብቻ ሳይሆን ካልተቀየረ በቤቱ ውስጥ መኖር አንችልም በሚለው ወገን እየተከለሉም እየተመሳሰሉም እያደናገሩም መኖሩን አቁመው አቋማቸው ጥቅም የሚያገኙበት ሳይሆን ከልብ የሚያምኑበት ከሆነ   መብታቸውን በይፋ መጠቀም እምነታቸውን በግልጽ ማራመድ ይኖርባቸዋል፡፡መሸፋፈን ለመኝታ ግዜ ብቻ ይሁን፡፡ ማለባበስ ይቁም!

በጣም አስቸጋሪው መፍትሄ አጥቶ የግዞት ዘመናችንን እያራዘመው ያለው በጣራው መቀየር ላይ ልዩነት ሳይኖር መቀየር ያለበት እኔ በምለው መንገድ ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡የነገሩ ክፋት የሚብሰው ደግሞ የዚህ አስተሳሰብ አራማጆች በሚሉት መንገድ ለመቀየር ስንዝር የተግባር እንቅስቃሴ የማያደርጉ መሆናቸው ነው፡፡ተግባሩ ቀርቶ እንዴት በምን ሁኔታ በማን ጣራው መለወጥ እንደሚችል ግልጽ አቋም የላቸውም፡፡ አቋማቸውን ገልጸው መንገዳቸውን አሳይተው ሊደርሱበት የሚያልሙትን ግብ ነግረው ደፋ ቀና በሚሉት ላይ ለመዝመት ግን እንቅልፍ የላቸውም ፡፡እንዲህ መሆን የለበትም፣ አንደዚህ ለምን ይደረጋል፣ በዚህ መንገድ ለምን ይኬዳል ከማለት በስተቀር እንዲህ ይሁን በዚህ መንገድ መሄድ ያዋጣል ወዘተ በተግባር ቀርቶ በቃል ደረጃ እንኳን አይናገሩም፡፡

ግልጽ አቋም በጣራው መለወጥ ላይ፣ የቤታችን ጣራ ከተለያየ አቅጣጫ ብዙ ስም የወጣለት ገዢዎቻችንም ሊያደናብሩንና አቅጣጫ ሊያስቱን በከጀሉ ቁጥር አዳዲስ ስም እያወጡ  በአንድ ያልረጉበት ሲሆን የምንሻው ግን ግልጽ ነው፡፡ዴሞክራሲያዊ ጣራ፡፡ ወራጅና ማገሩ ቆርቆሮና ምስማሩ በህዝብ ለህዝብ የህዝብ ሆኖ የሚሰራ ጣራ፡፡ይህን የሚጠላ ወይንም የማይፈልግ በአንደበቱ ባይናገረውም በተግባሩ እንለየዋልን፡፡የመጀመሪያው ወያኔና በዙሪያው ተኮልኩለው ተጠቃሚ የሆኑት ናቸው፡፡ለጥቆ የምናገኛቸው ሀያ ስድስት አመት ሙሉ ተቀዋሚ መባል ያልሰለቻቸው ምን አልባትም የሚያኖራቸው ወያኔ ተሰናብቶ ዴሞክራሲያዊ ሥርኣት ቢሰፍን ወለሉ ይታደስ ግድግዳው ቀለም ይቀባ አይነት የይስሙላ ተቃውሞ እያሰሙ መኖር አይችሉምና የጣራውን ለውጥ አይፈልጉትም፡፡ ሲስልስ ወያኔን ከማውገዝና ከማጥላላት ባለፈ የተጀመረም ሆነ የተሰነቀ ነገር የማይታይባቸው ነገር ግን ይህንኑ መኖሪያቸው ያደረጉ እናት ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ብሉኮ ብትከናነብ ህዝባችን ተገደለ ታሰረ በዘራችን ብቻ ተጠቃን  እያሉ ነሸጥ ሲያደርጋቸውም በመገንጠል እያስፈራሩ፣ ሰከን ያሉ እለት ደግሞ ስለ አንድነት እየዘመሩ ያሉ፣ የሚኖሩ ወገኖች ያኔ ይህን ማድረግ አይችሉምና በአፋቸው የሚናገሩት/የሚነግዱበት  ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በተግባር እውን ሲሆን ለማየት ይሻሉ ብሎ ማሰብ ይቸግራል፡፡

በድርድርም በሉት በግርግር፤በሰላማዊ ሰለፍም በሉት በጩኸት፣በጽሁፍም ይሁን በንግግር የሚቀርቡ ጣራውን በመለወጥ ላይ የማያተኩሩ ነሮች ሁሉ ጣራው ለሚያፈስ ቤት የወለል እድሳት የመፈልግ ያህል ነውና ሲብስም እቅጣጫ የሚያስት ትግል የሚያዘናጋ ለገዢዎች እፎይታ የሚሰጥ ወዘተ ነውና ይታሰብብት፡፡ በሁሉም መንገድ በየትኛውም መስመር ትግል ጣራውን ለመቀየር፡፤

posted by Gheremew Araghaw

በአዴን ያስቆረጠው የኢትዮጵያ ጡት! – በያሬድ ይልማ

ይህ ጽሁፍ በሶስት ምክንያቶች ተፃፈ!!!
የመጀመሪያው ምክንያት ፣ ሶስት ሺህ አመት ሳይነካ የኖረ ውበት ስለተነካ

ስለ አፍሪካ ከሚፅፉ በሳል፣ እጅግ አስገራሚ ደራሲዎች መካከል ጥራ ብባል ፣ መጀመሪያ ላይ የምጠራው ደራሲ የሚሆነው ሰው፣ ዊልበር ስሚዝ ነው! ለዚህ ደግሞ እራስወዳድ ሊያስብለኝ የሚችል ኢትዮጵያዊ ምክንያት አለኝ! በአንድ ጭብጥ ላይ የፃፋቸው ሁለት መፀሐፎች ( ሪቨርጋድ እና ዘ-ሰቭንዝ ስክሮል) ውስጥ ባለችው አገሬ ኢትዮጵያ ምክንያት ነው፡፡ የመፅሐፉ ገፀ-ባህሪያቶች መሃል ኢትዮጵያዊያ መኖሯ ብቻ ሳይሆን፣ የመፅሐፉ አንድ ክፍል በሚያስገርም ተረክ የተፃፈው በውቡ እና ባለግርማው፣ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጌጥ በሆነው በአባይ ፏፏቴ ላይም ጭምር ስለሆነ ነው፡፡

በተለይ ሪቨርጋድ፣ “ስልብ” በሆነውና እና እጅግ አስገራሚ ተሰጥኦ ባለቤት በሆነው “ታይታ” በሚባል ገፀ-ባህሪ ላይ የተመሰረቱት የዊልበር ስሚዝ መፀሐፎች ላይ ያለው ይህ ሰው ፣ የግብፅ ፒራሚዶች በተሰሩበት ዘመን እንዴት ተሰሩ በምን አይነት መንገድ እና ለምን ተሰሩ ከሚለው እንዲሁም በጣም ስለሚያስገርመው የእርከን እና የውሃ መስመር ስራቸው ብሎም ከሱ ጋር የሚያያዘውን አባይ ላይ ያለውን ከሃይማኖት የሚልቅ አምልኮ ይዳስሳል፣ በተጨማሪም ግብፃዊያን ፈርኦኖች እና ልኡሎች ዘ-ሂኮስ በመባል ታሪክ ከሚያነሳቸው ኑቢያዊያን ጋር ስለነበራቸው ከፍተኛ ትግል እንዲሁም ግብፅን የሚያጠጣት ወንዝ፣ አባይ እስከሚነሳበት ምድር፣ የዛሬዋ አገራችን ኢትዮጵያ ድረስ ያደርጉ የነበሩትን ፣ የመንፈሳዊነት ይዘት ያለውን ጉዞ ሳይቀር፣ “ታውረስ” በሚባል ጦረኛ ልኡል ገፀ-ባህሪ የሚያስገርም እና መሳጭ ፍሰት ያለው ታሪክ በ1994 አስነብቧል፡፡

በሪቨር ጋዱ ገፀ-ባህሪ ታይታ ስራዎች ላይ በሚያተኩር አርኪዎሎጂካል ፍለጋ ላይ በኋላም ፣ ግኝቶቹን በመፍታት ፣ የታይታ ቀመሮች ድብቅና ሚስጥራዊ መልእክቶች ወደሚመሯቸው አቅጣጫ እንዲሄዱ የሚያደርጋቸው ሁለተኛው የዊልበር ስሚዝ ዘ-ሰቭንዝ ስክሮል መፀሐፍ ፣ እኔ ባንድ ወቅት ተቀጥሬ ከሰራሁበት ሪፍት ቫሊ ሳፋሪስ የተሰኘ በማስጎብኘት እና በስፖርታዊ የአደን ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ባለቤት እስከ ስዬ አብረሃ እና ሌሎች የወቅቱ የመከላከያ ኮሎኔሎች ሳይቀር የተካተቱበት እጅግ አስገራሚ መፀሐፍ ነው፡፡

የዚህ ደራሲ ዋጋ እና የፃፈው መፀሐፍ ፋይዳ ለእኔ ይብስ ሰማይ የሚደርሰው ደግሞ፣ ፀሐፊው የታይታን ምጡቅ ገፀ-ባህሪያዊ አእምሮ ተጠቅሞ ከሶስት ሺህ አመታ በፊት ፣ ከአባይ ወንዝ ፏፏቴ አካባቢ (በኢትዮጵያዊያን ነዋሪዎች) በገጠማቸው ከፍተኛ ጦርነት ወቅት ፣ የአባይን ፏፏቴ በአርባስምንት ሰአት ውስጥ ፣ አቅጣጫውን ቀይሮ እንዲፈስ በማድረግ ከመጣባቸው የጠላት ጥቃት እና አደጋ እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸውን ይዞታዎቻቸውን ፣ ከአባይ ፏፏቴ ውስጥ እንዴት እንደሸሸገ፣ ከዚያም መልሶ ፏፏቴውን ከስፍራው የመለሰበትን ሁኔታ ላነበበ ሰው፣ ዛሬ ላይ ከሶስት ሺህ አመታት በኋላ ያለውን የአባይ ፏፏቴን ተጨባጭ ሁኔታ ስመለከት ስለሚገርመኝ እና በዚያው ልክ ስለሚያበግነኝም ጭምር ነው፣ የመፅሓፍ ማስታወቂያ እስኪመስል ድረስ የዊልበር ስሚዝን መፀሐፍ ዝርዝር ውስጥ ገብቼ መናገር ያስፈለገኝ!

ሁለተኛው ምክንያት፣ ያንን የኢትዮጵያን ውበት የነኩትና የቆረጡት ሰዎች ሁለነተና ስለሚያበሳጨኝ
የሞኝ ዘፈን ሁሌ ሆያሆዬ አይደል ተረቱ ፣ የደደብ ትምክህት ከማናደዱ በላይ የሚገርመኝ መመሳሰሉ ነው! ባንድ ወቅት አቶ አባዱላ ገመዳ ተናገሩት ተብዬ በግልፅ የሰማሁት ነገርን ልግለፅና ለምን እዚህ መሃል እንደገቡ ወይም ከማን ጋር እንደሚመሳሰሉብኝ እናገራለሁ፡፡ የባቢሌ ሳንክቹዋሪ- በአፍሪካ እጅግ ልዩ ዝርያ ያላቸውን ዝሆኖች የሚያስጠልል በጣም አስፈላጊ የእንስሳት መናኻሪያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ታዲያ አቶ አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ ፣ ሁለት እስራኤላዊያን ባለሃብቶች ፣ አንድ “ሪ” ያለበት ነገር፣ እንጆሪ ወይ ደግሞ መንደሪን ሊያለሙ ቦታ ጠይቀው ከባቢሌ ጥብቅ ስፍራ (ሳንክቹዋሪ) ተቆርሶ ሲሰጣቸው፣ በፕሬዝዳንቱ ድርጊት ግራ የተጋቡ አንድ ትልቅ የዘርፉ ምሁር፣ “እንደው ጌታዬ ዝሆኖቹ የት ወስደን እንጠብቃቸው፣ ይኸው ነው የቀረቀቸው የተፈጥሮ መኖሪያ ስርፋቸው እና፣ ከርስዎ ባላውቅም ሌላ ቦታ ጠፍቶ ነው! ብለው ቢጠይቋቸው፣ “ህዝባችንን ከድህነት የምናወጣው በግብርና ነው፣ ለዚያ ደግሞ በዝሆን ሳይሆን በበሬ ነው የምናርሰው” ብለው በመልሳቸው እኚህን ክቡር የዘርፉ ባለሞያ ጥንብርኩሳቸውን አውጥተው አባርረዋቸዋል፡፡

ታዲያ የሚገርመኝ መመሳሰል ያለው እንደዚህ አይነቱ የኢትዮጵያ የወቅቱ መሪዎች አስገራሚ እርምጃዎች አቋም ላይ እና ከዚያ በኋላ የሚሰጡትን መልስ ውስጥ የሚታየው የህዝብ ንቀት፣ ትምክህት ከሁሉ በላይ ልክ የሌለው የእውቀት ማነስ ፣ ተሳስተው ሳይሆን ሆን ብለው የሚያደርጉት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ እዚህ ጋር አንድ በስም የማላስታውሳቸው የባህር ዳር ከተማ መስተዳድር ሰው ከሶስት አመት በፊት፣ በጢስ አባይ ሁለት የሃድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ምክንያት ስለተሰወረው የአባይ ፏፏቴ ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ተጠይቀው የሰጡትም ምላሽ ፣ ድርጊቱ እንዲፈፀም ፊረርማቸውን ካኖሩት እኩል ባይሆንም በንግገራቸው ብቻ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ወንጀል ሰርተዋል አስብሎኛል፡፡ እንዲህ አሉ፣ “ የአባይ ፏፏቴ አንድ አምፖል አያበራም ለባህር ዳርም ሆነ ለዚህ ለጭስ አባይ አካባቢ ነዋሪ- ለዚህም ነው እዚህ ፏፏቴው ጋር ከመድረሱ በፊት ጠልፈል ወስደን ሃይል እንዲያመነጭ የምናደርገው !”

አባዱላ የዝሆን ጥብቅ ስፍራ ለምን ለእንጆሪ እርሻነት ተሰጠ ሲባሉ፣ “ የአገራችንን ህዝብ ከድህነት ለማውጣት በዝሆን ሳይሆን በበሬ ነው የምናርሰው” ይሄኛውም አገር በዚህ ስሟ ሳትጠራ በፊት የነበረን የአለም ውበት፣ “ ለባህርዳር ህዝብ የአባይ ፏፏቴ አንድ አምፖል አያበራም” ከዚህም በፊት እንዲሁ፣ ከነዚህ ሹመኞች የስልጣን አባት እና አጥማቂ በላይ በዚህ አርእስትን ያለጭብጥ እና ሃቅ በቃላት የማፈናጠቅ ሊቅ በሆኑ ሟች መለስ፣ ከታሪካዊውና ታላቁ የኤርትራ መገንጠል አስፈላጊነት ጥያቄ ( ከወረቀት መቀደድ ጋር ያመሳሰሉበትን ) ንግግራቸው እስከ የነገነት ዘውዴንና ዩናትድ ተባረክና ቤተሰቦቹ ሽርክና ኢትዮጵያን 245 ሚሊዮን ብር ያስወጣውና (የፕላዝማ ቴሌቭዥን ) በኋላ በወጉ ሶስት አመት ሳያገለግል በየትምህርት ቤቱ መጋዘን ተጥለው የቀሩትን ግዢ በተመለከተ፣ የቅንጦት ቴሌቭዥን በመሆኑ የት ሊሰቀል ታስቦ እንደሆን ሲጠየቁ፣ ካስፈለገ ዛፍ ላይ እንሰቅለዋለን ብለው ፓርላማ መሃል እንዳላገጡበት፣ እነኚህም አርአያቸውን በመከተል መልካቸው ቁርጥ ነው፡፡

ላጠፉት እና ለተሳሳቱት ማንኛውም ታሪካዊ ስህተት መከላከያነት የሚሰጡት ምላሽ፣ ቀን አልፎ የሚያስጠይቃቸው እንካ አይመስላቸውም፣ በራሳቸው ተፀፅተው አሊያም አርመው ወደፊት ለመሄድ እና የህዝብ ወገንተኝነትን ለማሳየት! ከአባይ ፏፏቴ መጠለፍም ጀርባ ያለው ይኸው ንቀት እና የህዝብ ወገንተኝነት መጥፋት ነው!!
ሶስተኛው ምክንያት፣ ይህንን የአባይን ውበት እንዲጠፋ የሚፈቅዱት በዘር ጥላቻ ቂም ተነሳስተወ በመሆኑ ነው፡፡

በተፈጥሮ አቀማመጧ ኢትዮጵያ፣ ከሶሪያ ተነስቶ ሞዛምቢክ ድረስ የሚወረወረው የስምጥ ሸለቆ መስመር ከላይ ካናቷ እስተ እታችኛው ክፍሏ ድረስ ፣ ሁለት በምእራብና በምስራቅ እንደተንጣለሉ የሚቀሩ ከፍ ያሉ ደጋ ስፍራዎች እንዲኖሯት አድርጎ ሰንጥቆ ፣ መሃሏን በረባዳማ አቀማመጥ ይዘው ዝቅ ባሉ የስምጥ ሸለቆ ውብ ተፈጥሮ ፣ እንዲሁም እምቅ ለሃይል ማመንጫነተት ሊሆኑ የሚችሉ እዛም እዚም እያጓሩ የሚርመሰመሱ ወንዞችን የታደለች አገር ናት፡፡ የአባይ ወንዝም እንዲሀ በፈሰሰበት ሁሉ አስገራሚ መልክአ-ምድርን ሰንጥቆ እየፈጠረ ስለሚጓዝ ጭስ አባይ ፏፏቴ ሆኖ ከሚወረወርበት ስፍራ ትንሽ ዝቅ ሲባል እንዲሁ ተመሳሳይ የውሃ አወራረድ እና መልክአ-ምድራዊ አቀማመጥ ማየት ይቻላል፡፡

በፈረንጆች አቆጣጠር በ1973 ለመጀመሪያ ጊዜ የጭስ አባይን የጎበኘው የኤምኤስኤንቢሲ ፕሮዲዩሰር ሪቻርድ ባንግሰ በአራት መቶ ሜትር ስፋት እና በአርባ አምት ሜትር ርዝማኔ ወደ ምድር ተወርውሮ በቪክቶሪያ ሃይቅ ከሚፈጠረው ፏፏቴ ለጥቆ የአፍሪካ ግርማ እስከመባል የበቃውን ጭስ አባይን የገለፀበት ቋንቋ በማርች 2004 (Stealing Nile-“Famous fall No More”) ልክ ከ200 አመት በፊት ጄምሰ የገለፀውን ውበት ሳይቀየር አገኘሁት ብሎ (ስኮትላንዳዊ አሳሽ ጄምስ ብሩስ እንደፃፈው) የአባይን ፏፏቴ ከነውበቱ እንዳገኘው ይናገራል፡፡ እ አ አ በ2004፣ ለአይማክስ ፊልም ቀረፃ ከቡድኑ ጋር አብሮ የመጣው ሪቻርድ በፏፏቴው ላይ ያየውን አሳዛኝ ድርጊት በከፍተኛ ሃዘን በዚሁ ፅሁፉ፣ (Stealing Nile-“Famous fall No More”) ዘርዝሮ ይናገራል፡፡

ከአስር አመታት በላይ በፊት ስልሳ ሶስት (63 )ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጥቶበት ለባህር ዳር ከተማ የመብራት ፍላጎት 450 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያመነጭ ታስቦ በችኮላ እና ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል የተገነባው የጭስ አባይ ሁለት ፕሮጀክት፣ ተዳክሞ የነበረውን የፏፏቴውን መጠነኛ የውሃ ጠለፋ ከናካቴው፣ ጭል ጭል ወደምትል ጉድ የቀየረ አሳዛኙን የኢትዮጵያን መንግስት በአላዋቂዎች የተሞላ አመራር ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

ጭስ አባይ ከተማዋ ውስጥ አንድ ቀን አብሮኝ ያሳለፈ የዛው ከተማ ተወላጅ እና አሁን ጭል ጭል እያለች የምትወርደዋን ጅረት ጋይድ ሆኖ በማስጎብኘት ስራ ላይ ያለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ከጥቂት ወራቶች በፊት ህዝቡ ውስጥ ያለውን ምልልስ እንዲህ ነበር ያስቃኘኝ፡፡

የአማራ ክልል ህዝብን የሚመራው በአዴን ፣ ለበላዮቹ እሺ ብሎ አባይን ሲያዘርፍ፣ ድምፅ በነሳው ድህነቱ ተለጉሞ ጭጭ ያለው የጭስ አባይ ነዋሪ ፣ ጭስ አባይን ናፍቆ ከራሱ እንባ የማትበልጥ ችፍ ችፍ የምትል “የኢሃዲግ ጅረት” ስር ቁጭ ብሎ ፣ “ምን አደረግናቸው ግን እንደው ድሮስ አባይ ፏፏቴውን እያየሁ ነበር ግጥም የምገጥም፣ ዛሬስ ግን ምን ልበል ጎበዝ፡፡
በእኛ ስም የሚጠሩቱ፣ “አባይ ላይ ያለንን ቁጭት ተወጣነ!” “እድሜ ዝንተአለም ወደ ግብፅ ሲፈስ፣ አያት ቅድመ አያቶችህ በቁጭት የሚገጥሙትን ግጥም የሚደብት፣ የሚያሳዝን የሚያስተክዝ ፣ ከዚያም አልፎ አንገት መድፋትን በሚጮኹ ቃላት እየገለፀ ቁስልህን ያባብስብህ የነበረው አይነት ማላዘን፣ ቀን አለፈበት፡፡

ስለዚህ እነዛን የሚያስተክዝና የሚደብት ስሜት የሚፈጥሩብህን ግጥሞች ፣ መቀየሪያ ጊዜው አሁን ነው! ምክንያቱም አባይ ልንገድብ እዚ ግባ የማይባል ጊዜ ብቻ ነው የቀረውና አሉት ለጭስ አባይ ነዋሪ፡፡

ምን ቢል ጥሩ ነው፣ ባህር ዳር ላይ ነው የሚገደበው ወይ? – አይደለም ሱዳን ጫፍ ነው የሚገደበው ሲሉት እና ታዲያ ጭስ አባን ምን ወሰደው? መልሱ አንድ ነው! በዘር የተለከፈው የኢትዮጵያ መንግስት እያለ፣ እንዲሁም የሚጠላው እና የሚፈራው ብሄር የአባይን ግርማ ፣ ሃብት፣ ውበት እንዲያጣጥም ፈፅሞ ፈቃዱ አይደለም፣ ይህ ነው ሃቁ!
ይነገር ከተባለ! …አባይን ገድቦ የሚያቆም ስፍራ በአማራ ክልል ስላልነበረ አይደለም አባይ ከአማራው ደጃፍ ርቆ እየፈሰሰ ሱዳን ከመግባቱ በፊት ህዳሴ ተብሎ የተገደበው፡፡

መጀመሪያም ቢሆን አባይን ያክል ጉድ ወንዝ ከጣና ፣ ከጎኑ ደግሞ አማራ የሚባል ብሄር ተፈጥሮ ፈቅዳ በማኖሯ ዘላለም የሚያርረው የአውሬ አመራር ቆሽት፡ በዘር ህዝብ ጥላቻ ጥምቀት በፈጠሙ የአመራሩ ፍልፋዮች ሸፍጥ፡ አባይን የወለደውን የአማራን ምድረ-ማህፀን ሾተላይ አድርገው፡ ህዝቡን ባገሩ ካባይ ቆርጠው ማለያየታቸው፣ አባይን አሶሳ ላይ መገደባቸው!፡፡
ለዘመናት ግብፅ የኢትዮጵያዊያንን ቁጭትና እንባ ከአሸዋ እየለወሰች በልታ ስትሳለቅ እንደኖረች እንዲሁ፡- ክፉው የኢትዮጵያ አመራርም፣ ከአማራው ህዝብ ማጣት እና ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ላቦት በተቀማ ገንዘብ ፡ ሲሚንቶ ገዝቶ የቂም ግንብ ገንብቶ፡ በገባው ውል መሰረት ወደ ከርሱ ዶላር ሲያጋብስ አማራውን ይህ በወሰኔ የሚለው ካባይ የሚጣቀስ አንዲት ጥሪት ለመቶ አመት እንዳይኖረው መሆኑ ነው እንጂ፡፡ ግና የእሱን ነገር ወደኋላ ተወት አድርገን፣ ፏፏቴውን ለምን ሰለቡት ብለን ብንጠይቅ ምላሹ የዘር ቂም ያመmጣው ጣጣ ነው! ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከዚህ ሰውን ከስፍራው ከሚያጎድል ጎጠኝነት አውጥቶ የድሮው ግርማዋ ላይ፣ የአባቶች ሆደሰፊነትን ያድለን እላለሁ!

የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከአለም መስህቦች አንዱ የሆነውን የጭስ አባይን ፏፏቴ፣ ሰው (ለዚያውም ሰንካላ አእእሮ ያለው) እንጂ ተፈጥሮ አላቋረጠችውም!

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!”

posted by Gheremew Araghaw

በአማራ ላይ የተሰለፉ አምስተኛ ረድፈኞች (Fifth columnist) – ቬሮኒካ መላኩ

የሰው ልጅ ታሪክ እንደሚያስረዳን አለም በመንታ ባህሪያት የተዋቀረች ትመስላለች ። ሰማይ ስንል መሬት አለ ። እሳት ስንል ውሃ አለ ፣ ብርሃን ብለን ጨለማ አለ ፣ አርበኛ ብለን ባንዳ አለ እንደዚህ እንደዚህ እያልን ብዙ ነገሮችን መጥቀስ እንችላለን ።

ከነዚህ ባህሪያት መገለጫ አንዱ ሰው ነው ። የሰውም ባህሪ እንደዚሁ ለየቅል ነው። በሰው ውስጥም ክፋትና በጎነት ፣ታማኝነትና ክህዴት ፣ ሁሉም ተቃርኖ አለ ። በአንድ ብሄር ፣ ማህበረሰብ ፣ እንድሁም ቤተሰብ ውስጥ የአስተሳሰብ ዝምድና ከሌለ የስጋ ዝምድና ብቻውን ሰዎችን ማወዳጄት ፣ በአንድ አላማ ስር ማሰባሰብ እንደማይችል ከአንድ ማህበረሰብ ብሎም ቤተሰብ የተገኙ ልጆች እርስ በርሳቸው ሲቆራቆሱ እና ሲጨራረሱ የአለም የትግል ታሪክ ያስተምረናል ።

ሰሞኑን ከአማራው አብራክ እየወጡ ራሱን አማራውን ከጀርባ በጦር የሚወጉትን ቡድኖች ወዳጄ ዶ/ር GM Melaku “ዋለልኞች” ብሎ ስም አውጥቶላቸዋል ። እኔ በበኩሌ ከስፔኖች ተውሼ “አምስተኛ ረድፈኞች ” በማለት ልሰይማቸው ።

ዛሬ በወዳጄ በ GM Melaku ስያሜ መሰረት “ዋለልኞች ” በእኔ አጠራር ደሞ ስለአምስተኛ ረድፈኛ አጠር አድርጌ ልፅፍ ነው ። ይችን አጠር ያለች ጦማር መፃፍ ያስፈለገኝ ከሁሉም በላይ የአማራ ብሄርተኝነትን ደንቃራ እና ጋሬጣ ሆኖ እየጎዳው ያለው ” አምስተኛ ረድፈኛ ” የሚባለው ቡድን ነው ብዬ ስላመንኩኝ ነው ። አማራን የሚጎዳው በይፋ በጉያቸው ሾተል ፣በጭናቸው ክላሽንኮቭ በያዙ ጠላቶቹ ብቻ ሳይሆን ከጉያው በወጡ የወዳጅ ጠላትም ጭምር ነው ።

አምስተኛ ረድፈኛ ማለት ፤ አንድ በሚስጥር የተደራጀ ቡድን ወይም ግለሰብ ሲሆን ፣ ለጠላት በመወገን የራሱን ሕዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከመሀል ሆኖ የሚቦረቡር ማለት ነው ፡፡

እንደዚህ ዐይነቱ ጠላት ደግሞ ከለየለት የውጭ ጠላት የበለጠ አደገኛ ነው ፡፡ ለዚህም ነው አማራ ሲተርት ” ፈጣሪዬ እኔ ከጠላቶቼ እራሴን ስከላከል አንተ ከወዳጅ ጠላት ጠብቀኝ “ ተብሎ የሚፀለየው ፡፡

አምስተኛ ረድፍ የሚለው ሀይለ ቃል በመጀመሪያ ለውስጥ ቦርቧሪዎችን ለመግለፅ የተጠቀመው ስፔናዊው የፋሽስት ጀኔራል ሞላ ነው። ከ1936 እስከ 1939 በተካሄደው የስፓኝ የርስ በርስ ጦርነት ጊዜ ማድሪድ ስትከበብ ፋሽስቱ ጀነራል ሞላ በውስጥ አርበኝነት ስለሚያገለግሉት ደጋፊዎቹ ሲናገር < < እኛ ማድሪድን በአራት ረድፍ እያጠቃናት ነው። በከተማይቱ መሃል ደሞ 5ኛ ረድፍ አለን>> በማለት ከገለፀው የተወሰደ ነው።

በኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክም ” አምስተኛ ረድፈኛ ” አማራውን ፍዳ ሲያሳየው ፣ወገኖቹን ሲያስጨፈጭፍና ፣ለጠላት አጋልጦ ሲሰጠው ታሪክ መዝግቦታል ።
አረብ ፋቂህ የተባለው የኢማም አህመድ የግል ፀሃፊ በአረብኛ ” Futuh al-habasha በማለት ፅፎት “the conquest of abyssinia ” በሚል ርእስ ወደ እንግሊዚኛ የተመለሰው መፅሃፍ እንደሚከተለው ያለ “የአምስተኛ ረድፈኞች ” አሰቃቂ ድርጊት ተመዝግቦ አንብቤለሁኝ… …

< < ኢማም አህመድ ጠንካራውንና የማይደፈረውን የአምባ ግሸን ምሽግ ለመስበር ብዙ ሞከረ ። እዚህ ምሽግ ውስጥ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት የነጋሲ ልጆች ፣የልጅ ልጆች ፣ዘመዶች እና ብዙ ሀብት ይገኝ ነበር ። ኢማሙ ከቱርክ እና ከፓኪስታን በመጡ መድፍ ተኳሾች ቢሞክርም የክርስቲያኖቹ አምባ የማይደፈር ሆነ። ወታደሮቹም አለቁበት። 3 ወር ሙሉ አምባ ግሸንን ለመስበር ሞከረ የማይቻል ሆነ።ወደ አምባው መውጫ ያለው ሁለት በር ብቻ ስለነበር በሩን ይዘው አልበገር አሉ። በመጨረሻ ኢማም አህመድ (ግራኝ) የአምባ ግሸንን ምሽግ ለመያዝ በውጊያ መሞከርን ትቶ አምባው ካሉ የክርስቲያን ተዋጎዎች መካከል አምባውን አሳልፎ የሚሰጠው ከሃድ መፈለግ ጀመረ። በወርቅ እና በገንዘብ የተደለለ ሰውም ተገኘ ።በዚህም መሰረት የግራኝን ጦር በስርቆሽ በር በኩል እየመራ ወደ አምባው በድብቅ አስገባቸውና የክርስቲያኑን ጦር ከጀርባ በኩል አስጨፈጨፋቸው። የአምባ ግሸንም ጠንካራ ምሽግ ተሰበረ ። >> እያለ ይቀጥላል ።
The conquest of Abysinia. Page. 345.

ይሄ ከመፅሃፉ የጠቀስኩት ቁራጭ ታሪክ የሰዎችን ፣ የከሃድያንን እርቃነ ማንነት እና የሚያደርሱትን ወሰን የለሽ ጉዳት የሚያመለክት ነው ። በአገራችን ውስጥ በታሪካችን ዘርዝረን መንዝረን ሳንመለከተው እየቀረን ይሆናል እንጅ የዚህ አይነት የትውልድ አራሙቻዎች ሲከሰቱ ተስተውሏልም እንማርበትም ዘንድ ተመዝግቧል ።

አሁን ከአማራ ህዝብና የአማራን ብሄርተኝነት ለመገንባት በምናደርገው ትግል “የአማራ አምስተኛ ረድፈኞች ” ምን ማለት እንደሆነ የተግባባን መሰለኝ ። ያልገባው ካለም አምስተኛ ረድፈኛ ” ማለት ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጥተው አማራን ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ ፣ ከጀርባ የሚወጉ ( Back stabber) የአማራን ለምድ ለብሰው እንደ ተኩላ የሚተውኑ ማለት ነው።
አስተውላችሁ ከሆነ እነዚህ አጎብጓቢ ረድፈኞች ሲፅፉም ሆነ ንግግር ሲጀምሩ እንድህ በማለት ይጀምራል… < < እኔ አማራ ነኝ ነገር ግን በብሄር መደራጀት አላምንም ።>> ይላሉ ። ይች የአነጋገር ዜዬ መለያ ባህሪያቸው ናት ። ለእኔ አደገኛው ይሄ ነው። እነዚህ ሰዎች “አማራ ነኝ ” ብለው ይጀምሩና “በብሄርም መደራጀት አላምንም ” ብለው ድስኩራቸውን ቀጥለው የኦሮሞውን ፣የሱማሌውን ፣የትግሬውን ፣የወላይታውን፣የ80 ውን ብሄር መደራጀት ችግር የለውም ብለውን እርፍ ይላሉ የአማራውን መደራጀት ግን በርበሬ እንዳጠኑት ልጅ ሲያስነጥሳቸው ይውላል ።
ከ 500 አመታት በፊት ጠላቶቻችን ፈ ት ለፊት ተጋፍጠው ማሸነፍ ስለማይችሉ እየተጠቀሙ ያሉት በዚህ “በአምስተኛ ረድፈኛው ” ቡድን በኩል ነው።

የአማራ አምስተኛ ረድፈኞች የሚሰሙኝ ከሆነ ጥቂት ምክር ቢጤ ጣል ላድርግና ፅሁፌን ልዝጋው ። ረድፈኞች ከእናንተ ጋር የአንድ ቤተሰብ እና የአንድ ወገን ልጆች ብንሆንም በአስተሳሰብ አንገናኝም ። የአንድ ክልል ፍሬ ብንሆንም ጎራችን ለየቅል ነው። የአንድ ወጥ ባህል ልምድና አካባቢ ውልዶች ብንሆንም ግባችን የተለያየ ነው ። ባንድ መልክ ያደግን ብንሆንም በተዥጎረጎረ ባህሪይ ጎልምሰናል ። ለእኔ የሚጣፍጠኝ ለአንተ ይመርሃል ። ለእኔ የሚጥመኝ አንተን ያቅርሃል ። ህዝባችን ያለበት አስከፊ ሁኔታ ቆራጥነትን የሚጠይቅ ሌላው ቀርቶ ከአንድ አብራክና ከአንድ መሀፀን የተገኙትን የአንድ አባትና የአንድ እናት ልጆች የሚያታግል ነው። ነፃነት የሚባለውን ክቡር ነገር ለማግኘት ጠላትን ብቻ ሳይሆን የወዳጅ ጠላትንም መፋለም የግድ ይላልና ትግላችን “ከአምስተኛ ረድፈኞች ” እና “ዋለልኞች “ጋርም መሆኑ መታወቅ አለበት።

ሕገ መንግሥቱን ማሻሻልና የባህር በር ጥያቄ የተካተቱበት ረቂቅ የፖለቲካ ድርድር አጀንዳ ቀረበ

17 Jun, 2017 By ዮሐንስ አንበርብር (Reporter)

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና 16 ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ድርድርና ውይይት ለማድረግ በተስማሙት መሠረት፣ የሕገ መንግሥቱ የተለያዩ አንቀጾችን ከማሻሻል አንስቶ እስከ የባህር በር ጥያቄ የተካተተበት 13 ነጥቦችን የያዘ ረቂቅ አጀንዳ ለውይይት ቀረበ፡፡

የድርድርና የውይይት አጀንዳዎቻቸውን ኢሕአዴግን ጨምሮ 17 ፓርቲዎች ለድርድር መድረኩ የሙያና የጽሕፈት አገልግሎት ድጋፎችን ለሚያቀርበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ካቀረቡ በኋላ፣ ፓርቲዎቹ ባዋቀሩት አጀንዳ አደራጅ ኮሚቴ ተጠናቅረውና ቅርፅ ይዘው እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት 13 ጥቅል ርዕሶችን የያዘ ረቂቅ የመወያያ አጀንዳ ተቀርፆ ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ሁሉም ፓርቲዎች በተገኙበት ለውይይት ቀርቧል፡፡

በቀዳሚ አጀንዳነት የቀረበው የምርጫ ሕጎችን ለማሻሻል የተቀመጠው አጀንዳ ነው፡፡ በውስጡም የምርጫ ሕጉን፣ የፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅንና የፓርቲዎች ሥነ ምግባር አዋጅን በውስጡ አካቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ስለአገር አቀፍ ምርጫ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው አንቀጽ አልተካተተም፡፡

ይሁን እንጂ ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል በሚለው ሌላ አጀንዳ ሥር የሕገ መንግሥቱ የተለያዩ አንቀጾች እንዲሻሻሉ በመቅረባቸው በንዑስ አጀንዳነት ተይዘዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንቀጽ 39፣ 40፣ 47፣ 72(3) ይገኙበታል፡፡

ሌሎች አዋጆችን ማሻሻል በሚለው ዓቢይ አጀንዳ ሥር ደግሞ የፀረ ሽብር ሕጉ፣ የብዙኃን መገናኛና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና የሲቪክ ማኅበራት ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና ታክስ አዋጆችና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በንዑስ የድርድር አጀንዳነት ቀርበዋል፡፡

ብሔራዊ መግባባት፣ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ጉዳይ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን መከተል እንዳለባቸው፣ ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማትን መፍጠር፣ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ድንበርን መወሰን (በውስጡ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንደተካተተበት ተገልጿል) በዓቢይ አጀንዳነት የተረቀቁ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የክልሎች ድንበር አከላለል፣ የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ አወቃቀር፣ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋን የተመለከቱ ዓቢይ አጀንዳዎችም ይገኘብታል፡፡ ፓርቲዎቹ ቀደም ባለው ውይይታቸው ድርድሩ የሚመራበትን ደንብ ማፅደቃቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ደንብ መሠረት በአደራዳሪነት መድረኩን የሚመሩት ከራሳቸው ከፓርቲዎቹ በዙር የሚመረጡ እንዲሆኑ ስምምነት ተደርሶ በሥነ ሥርዓት ደንቡ ተካቷል፡፡

ይህንኑ በመከተልም ለዕለቱ የተመረጡ አደራዳሪዎች በቀረበው የድርድር አጀንዳ ላይ ውይይት እንዲጀመር መድረኩን ከፍተዋል፡፡ መድረኩ ለውይይት ክፍት ከተደረገ በኋላ ከውይይት ይልቅ ንትርክ መባል የሚችል አተካራ እስከ ቀትር ድረስ ተስተውሏል፡፡

የንትርኩ መነሻ የተወሰኑ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው የድርድር አጀንዳዎች ውድቅ እንደተደረገባቸው ለመግለጽ የተጠቀሙባቸው ጥርጣሬ አዘል ንግግሮች ናቸው፡፡ በመድረኩ የተሰየሙትን አደራዳሪዎች መጠራጠር፣ ፈቃድ ሳያገኙ ንግግር ማድረግና እንዲያቆሙ ሲጠየቁ የውይይት መሪዎቹን አለመስማት ተሰማርተዋል፡፡

በዚህ አተካራ ውስጥ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ተሻለ ሰብሮ ትኩረት በመሳብ ግንባር ቀደም ነበሩ፡፡ አቶ ተሻለ ሙግት ውስጥ የገቡት ፓርቲያቸው ካቀረባቸው ከ30 በላይ የድርድር አጀንዳዎች ውስጥ ተቀባይነት አግኝተው የቀረቡት 13 ብቻ ናቸው የሚል ምክንያት ይዘው ነው፡፡

ለአብነት ያህል ካነሱት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ አልተካተተም የሚል ይገኝበታል፡፡ አጀንዳ አደራጅ ኮሚቴ ከነበሩት ሦስት የፓርቲ ተወካዮች መካከል የእርሳቸው ፓርቲ የተወከለ ሲሆን፣ አጀንዳዎችን በማደራጀት ሒደት ውስጥ በሦስቱ ተወካዮች መካከል ልዩነት እንዳልነበረ ቀሪዎቹ ሁለት ተወካዮች በወቅቱ ተናግረዋል፡፡ የራዕይ ፓርቲ ተወካይ የኮሚቴው አባል ግን ልዩነት እንደነበር በውይይቱ ወቅት ጠቁመዋል፡፡

የአጀንዳ አደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ አጀንዳዎቹ የተለዩበትን ሒደት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በዋነኝነትም ከሦስት በላይ በሆኑ ፓርቲዎች በድርድር አጀንዳነት የቀረቡ ሐሳቦች ተለይተው መደራጀታቸውን አብራርተዋል፡፡ የሚመጋገቡ ነጥቦችን በማግባባት መጠናቀሩንም ገልጸዋል፡፡

ከሦስት በታች ፓርቲዎች የቀረቡ የውይይት አጀንዳዎችን ያቀረቡ ፓርቲዎች፣ ኢሕአዴግ በሰጠው አስተያየት መሠረት የሁለትዮሽ ድርድር ማድረግ እንደሚችሉ በመግለጹ አለመካተታቸውን አብራርተዋል፡፡

የራዕይ ፓርቲ ሊቀመንበር ያነሱት የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ውድቅ አለመደረጉን የአደራጅ ኮሚቴው አባልና የኢሕአዴግ ተወካይ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ገልጸዋል፡፡ ይህ ጉዳይ የምርጫ ሕጎችን ማሻሻል በሚለው ርዕስ ሥር በተዘረዘሩት ንዑስ ነጥቦች ማለትም በፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ የተሸፈነ በመሆኑ የድርድሩ አካል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ከፖሊሲ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የድርድር ጥያቄዎች ውድቅ መደረጋቸውን አቶ አስመላሽ ተናግረዋል፡፡ በሰጡት ምክንያትም በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ድርድር ማድረግ ትርጉም እንደማይሰጥ፣ በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ድርድር ሳይሆን ውድድር ትክክለኛ አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ማብራሪያዎች የቀረቡ ቢሆንም ንትርኩ ግን ሊቆም አልቻለም፡፡

ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ያረቡት አጀንዳ ያላግባብ ውድቅ እንደተደረገባቸው ማቅረብ ቀጥለዋል፡፡ መላው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ተሰማ ሁንዱማ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነቱን በሕዝበ ውሳኔ እንዲያስከብር ፓርቲያቸው በአጀንዳነት ቢያቀርብም አለመካተቱን በመጥቀስ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብን የሚወክለው ገዳ የተባለ ፓርቲ በበኩሉ ‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለው የአገሪቱ መጠሪያ ስም ‹‹የኩሽ መሬት›› በሚል ስያሜ እንዲቀየር ያቀረበው የድርድር ነጥብ አለመካተቱን በመጥቀስ ክርክር አቅርቧል፡፡

በውይይቱ ማብራሪያዎች ከተሰጡ በኋላ ንትርኩ መቀጠሉ ግራ እንዳጋባቸው የገለጹት የኢሕአዴግ ተወካይ የቀድሞው ትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ‹‹ወደዚህ ውይይት እስክንገባ አሥር በሚሆኑ ውይይቶች ሥነ ሥርዓት ተከትለን የሰከነ ውይይት አድርገናል፡፡ ዛሬ በድንገት ነገሮች ፈር የሳቱት ለምንድነው? የውጭ ታዛቢዎች ስላሉ ነው?›› ሲሉ ምፀታዊ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በዕለቱ የተካሄደውን ውይይት በታዛቢነት እንዲከታተሉ ጥሪ ከተደረገላቸው የውጭ ታዛቢዎች መካከል በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር፣ የእንግሊዝ፣ የጀርመንና የካናዳ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ ከአገር ውስጥ በታዛቢነት የተጋበዙ የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ ድርድሩ የሚመራበትን ደንብ ታዛቢዎች ከመታዘብ ወጪ ሐሳብ መሰንዘር እንደማይችሉ፣ ለመገናኛ ብዙኃንም ስለድርድሩ አስተያየት እንዳይሰጡ ይገድባል፡፡ ይሁን እንጂ በዕለቱ የነበረውን ረብ የለሽ ንትርክ የአገር ውስጥ ታዛቢዎች በጉርምርምታ ለመገሰጽ ሞክረዋል፡፡

አቶ ሽፈራው በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ‹‹የኩሽ መሬት›› በሚለው የመደራደሪያ አጀንዳ ላይ ኢሕአዴግ ለመደራደር ሥልጣን እንደሌለው፣ በተመሳሳይም የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት በሕዝበ ውሳኔ እንዲለይ በቀረበው ነጥብ ላይ ኢሕአዴግ እንደማይደራደር ገልጸዋል፡፡ የመደራደሪያ አጀንዳዎቹን ያቀረቡት ፓርቲዎች በራሳቸው መንገድ ማስፈጸም እንደሚችሉ አቶ ሽፈራው አክለዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ንትርኮቹ መስከን በመቻላቸው የቀረቡትን 13 ረቂቅ አጀንዳዎች አንድ በአንድ ወደ ማፅደቅ ሒደት ተገብቷል፡፡

ኢሕአዴግን ከወከሉት መካከል አቶ ሽፈራው የፓርቲውን አቋም ግልጽ አድርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ኢሕአዴግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለድርድር እንደማይቀመጥ ተናግረዋል፡፡ አገሪቱ አሁንም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ሆና በዚህ ጉዳይ ላይ መደራደር እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የንግድ ሕጉን የማሻሻል ሥራ በሒደት ላይ በመሆኑ መደራደር ሳያስፈልግ፣ ፓርቲዎች በማሻሻል ሒደቱ ተሳታፊ እንደሆኑ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

ቁጥር አንድ አጀንዳ ሆኖ የቀረበውን ምርጫ ሕጎችን ማሻሻል የሚለውን አጀንዳ ኢሕአዴግ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀበለው፣ እንዲሁም በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የቀረበውንም እንደሚቀበለው ገልጸው፣ በሌሎቹ ላይ ድርድር እንዲደረግ ፓርቲዎቹ የፈለጉበትን ምክንያት ካብራሩ በኋላ ኢሕአዴግ አቋሙን እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡

በሰጡት ማብራሪያ መሠረት የምርጫ ሕጎችን ማሻሻል የሚለው ቁጥር አንድ አጀንዳ ተቀባነት አግኝቶ እንዲያልፍ ፓርቲዎቹ ተስማምተዋል፡፡

በቁጥር ሁለት አጀንዳ ሥር የተዘረዘሩ አዋጆች (ፀረ ሽብር ሕጉና የመሳሰሉት) እንዲሻሻሉ የጠየቁ ፓርቲዎች ምክንያቶቻቸውን ከዘረዘሩ በኋላ፣ የኢሕአዴግ ተወካዮች የፓርቲያቸውን አቋም በቀጣይ ውይይት እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ለሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት ቀጠሮ ተይዞ የዕለቱ ውይይት አብቅቷል፡፡

EMF

posted by Gheremew Araghaw

From Ethiopianness to Ethnic Fragmentation: the Adversity of Retrospective Logic By Messay Kebede (PhD)

A leitmotiv of ethnic politics in Ethiopia is the use of retrospective logic as an essential argument to justify its ideological stand. By this I mean the view that Menelik’s southern march, which is responsible for the creation of modern Ethiopia, was nothing else but a violent destruction of preexisting nations. Such statements as “Ethiopian colonization” and “the invention of Ethiopia” as well as the description of Ethiopia as “prison of nations and nationalities” all signify that modern Ethiopia has emerged on the ashes of annihilated preexisting nations.

Far from me to deny the violent and annexing character of the southern expansion. But it is one thing to point out conquest and domination, quite another to speak of eradication of existing nations. The present ethnonationalist discourse is a product of the derailment of modern Ethiopia. It does not predate modern Ethiopia; rather, it is what modern Ethiopia has given birth owing to its socioeconomic failures. What is in play here is a thinking that throws back into the past what is but a product, thereby transfiguring the effect into a cause.

Unsurprisingly, objections proliferate. The Eritrean insurgency, peasant uprising in Bale, the Oromo mutiny of 1966 led by General Tadesse Birru, etc., are events that not only occurred prior to the Ethiopian revolution of 1974, but were also eminently part of the general discontent that brought down the imperial regime. Agreed, but the whole question is to know whether these uprisings, including the Eritrean one, were really triggered by nationalism or whether they were part of the general demands of the Ethiopian people for equality, justice, and economic development. The fact that the forces that destroyed the imperial regime were inspired by the then prevailing Marxist-Leninist ideology suggests that social divides and subsequent confrontations were more based on class alignments than on identity politics. The debate within the Ethiopian student movement over the question of knowing whether the primary contradiction is the contradiction between classes or nationalities is proof enough that the issue of the primacy of identity politics was by no means a settled matter.

To be sure, groups promoting ethnonationalist ideologies were present, but their presence was marginal for quite some time. Precisely, their influence started to grow as a result of the Derg’s repressive policy and its utter inability to respond to the demands of equality and economic development. Stated otherwise, what was an issue of equality progressively grew into ethnic alignments as the new regime not only dashed all the hopes raised by the Revolution, but also aggravated all the ills of the imperial regime. Last but not least, the revolutionary regime could not even defend the integrity of the country: its shameful military defeat against armed ethnonationalist forces announced the beginning of the downward trend of Ethiopian nationhood in favor of ethnonationalist movements under the hegemonic control of the TPLF. Once in control of Ethiopia, the TPLF launched an active and deep-going ethnicization of the country, which is essentially a policy of divide and rule by which alone it could sustain its hegemonic position.

This is to say that ethnonationalism in Ethiopia is a product of all the above prior developments and occurrences, and not, as the retrospective logic claims, a fact that existed prior to the formation of modern Ethiopia. The correct expression is not “the invention of Ethiopia,” but the invention of ethnonationalist movements in Ethiopia. In so saying, my purpose is not so much to demean such movements as to assert that, as any ideologically driven movement, ethnonationalism is a construct by which elites vying for the control of power mobilize people. Still less am I implying that its posteriority to modern Ethiopia turns ethnonationalism into a negligible political nuisance. On the contrary, I am stressing the undeniable fact of changed Ethiopia to the point that any viable and lasting remedy for the ills of the country must include the ethnic factor.

Understanding ethnonationalism as a byproduct of modern Ethiopia is a theoretical position that has a great beneficial outomce. It views ethnonationalism as a protest rather than as a clash between incompatible or alien cultures. Protest is manageable being but a demand for reforms, however far-reaching the reforms may be. By contrast, the view that modern Ethiopia resulted from the sequestration of already existing nations has nothing to offer but the dismemberment of Ethiopia or, as the TPLF’s solution demonstrates, the preservation of a political unity so structured as to ensure the hegemonic position of one ethnic group. Obviously, this last solution does nothing more than defer the inevitable dislocation of the country.

To sum up, the retrospective reconstruction of Ethiopian history puts us neither in the path of peace and stability nor of democracy. Stability and democracy demand concessions and compromises, neither of which is possible with the claim that today’s Ethiopians actually belong to different nations.

The Endless Plight of Ethiopians: Death at Home and Dehumanization Abroad

The Endless Plight of Ethiopians: Death at Home and Dehumanization Abroad

By Aklog Birara (Dr)

Open Letter

Barely three years after more than 160,000 Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia were expelled from the Kingdom, an estimated 400,000-750,000 Ethiopian migrant workers face a dire situation again. No one really knows the exact number involved; but it is in the hundreds of thousands. The eminent nature of these mass deportations reveal two intractable and interrelated fundamental human rights issues in international and domestic policy.

Despite its constant rhetoric that it has embarked upon a period of unprecedented “renaissance” for its large population, Ethiopia’s police state is incapable of creating work opportunities or providing basic services. Instead, the regime resorts to all forms of cruel and inhumane treatments including encouraging hundreds of thousands to leave Ethiopia. The exodus of people is unprecedented in Ethiopian history. The regime continues to believe that this exodus generates foreign exchange and is therefore worth the sacrifice of tens of thousands of lives and the dignity of Ethiopians.First and foremost is the inability of the Ethiopian government to meet the hopes and aspirations of its bulging youth. Those under the age of 35 constitute 70 percent of Ethiopia’s 104 million people. Experts estimate that Ethiopia needs to create more than 2.5 million jobs each year. Compounding this lack of opportunity is a crushing and debilitating system of government that crushes all forms of dissent, rejects the right to demand services and to hold government officials accountable for crimes against extrajudicial killings, forcible disappearances, evictions, displacements, jailing and torture.

Hence, the allure of a better life abroad and the push from cruel and inhumane treatment constitute the key divers of indescribable flight and brain drain from Ethiopia. Ordinary Ethiopians prefer to take risks and leave their homeland in droves than to suffer from humiliation, recurrent assaults and slow deaths at home. The government of Ethiopia is incapable of removing the root causes that led millions of peaceful citizens in Oromia, Amhara, Konso and other locations to revolt against this crushing system barely one year ago. More than 1,000 innocent people were murdered; and no one has been held accountable for these atrocities. Unwilling to respond to the popular revolt, the regime declared a State of Emergency for six months that it has now extended by 4 more months. For practical purposes, political, social and spiritual space is totally closed. A closed society cannot create jobs or establish an environment in which citizens would have a fighting chance to make a living in their homeland.

If the regime has failed to match the East Asian Miracle of growth and development over the past 27 years, do not expect that it can match them in the next 30 or 50 years. The fundamentals are broken and cannot be fixed by the same crowd that enriched themselves over a quarter century!! The tragedy in exclusionary and repressive governance shrouded under the developmental state is that, the regime’s leaders refuse to compare their contributions with the best of the best in the East and South Asia, Latin America, North and Sub-Saharan Africa. Instead, they keep telling the Ethiopian people that the regime is doing better than the Imperial regime and the Dergue, both of which are long gone and history. Why not dare to compare Ethiopia’s growth with current success stories such as Botswana, Mauritius, Seychelles, Namibia and increasingly Ghana, Kenya, Rwanda etc.? Ethiopia’s per capita income is a third of Sub-Saharan Africa.

The regime has failed miserably in meeting the demands and needs of Ethiopian youth. They leaves in droves because the system is both hostile and disempowering. Any regime incapable of responding to its youthful population is at the same time incapable of serving the country and all of its citizens. Immigrants suffer from this vicious and cruel system.

Second, even in better times, Saudi Arabia is not known for humane treatment of migrant workers. Migrant workers do not have human rights; they are treated as disposable modern “slaves.” Therefore, the Saudi Arabia’s “Saudization” or indigenization program comes at the worst time for Ethiopian migrant workers. Millions of Ethiopians suffer from one of the worst cases of drought famine. A 2017 assessment of fragile states by the Fund for Peace identifies Ethiopia among the 15 most fragile countries in the world. The report underscores the fact that the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) that dominates the government exercises total monopoly over political, economic, security and other policy and decision-making institutions. “The TPLF control is self-evident. The military establishment is Tigrean.” Group grievances are common and are left un-addressed. Ethiopia’s middle class is in shambles. Wealth is concentrated in a few hands, mostly Tigreans. The TPLF controls almost all natural resources.

In a similar vein the Carnegie Endowment for International Peace opined that “The EPRDF position of power remains fundamentally fragile, owning primarily to the internal contradictions of the EPRDF regime.” Consequently, the regime is incapable and unable to meet the basic needs of citizens.

Against these dire conditions, migrant workers face enormous problems in Ethiopia. History is likely to repeat itself. Three years ago, those who returned to Ethiopia from Saudi Arabia found themselves in a worst condition and thus returned to Saudi Arabia and other countries in droves. At the time, Human Rights Watch and other human rights groups reported degrading conditions, indescribable human rights abuses by police and gangs in Saudi detention camps. The current deportation order might be far worse than the last. Because the numbers are far greater and the decision is not reversible or flexible. On 19 March, 2017, the Ministry of the Interior of Saudi Arabia issued a national campaign under the title of ‘A Nation Without Violations’ and gave “illegal migrants” 90 days from March 29, 2017 to leave the country without paying penalties. According to the edict, “illegal migrants” who fail to leave within the time frame will be evicted forcibly or face other punishments.

What is the responsibility of the government of Ethiopia?

First and foremost is for the Ethiopian government to express outrage against this cruel and unusual punishment and to defend the human rights of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. It is to urge the government of Saudi Arabia to treat Ethiopians with respect and dignity and to negotiate a reasonable, honorable and safe exit for all Ethiopians regardless of age, gender, religion, ethnicity, health condition, income level and marital status. On this score, Ethiopian officials are consistently numb and show zero interest for Ethiopian lives either at home or abroad.

The decision by Saudi authorities to “revive the economies of companies and establishments and protect small businesses and projects from illegal expats, while also reducing unemployment rates and creating a safe economic and social environment” might seem reasonable on the surface. After all, all nations serve their national interests first. Currently, Saudi society depends on an estimated 9-12 million foreigners to support the economy, especially services. The Middle East Monitor estimates that a third of Saudi’s population is composed of foreigners from a broad spectrum of countries including Ethiopia. These foreigners claim that they are “unpaid, underpaid and ill-treated” by their employers. Worse off among these are migrant workers and illegal immigrants. Those who protest for decent wages and decent treatment are often “flogged and jailed.” They are treated worse than “dogs.”

The world community and callous governments such as Ethiopia’s show minimal interest. Ethiopian officials are much keener to benefit from remittances migrant workers send to Ethiopia more than they show an ounce of empathy for their ill treatment. The Ethiopian Embassy is literally closed for business when it comes to migrant workers.

It is true that in 2013, international pressure and especially vigorous and worldwide campaign spearheaded by Ethiopian Diaspora groups, most notably by the Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia and now the Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) did a terrific job persuading both the Saudis and Ethiopian authorities to repatriate more than 160,000 Ethiopians.

Given the magnitude of the problem and the intractable root causes that push Ethiopians out of their homeland, Diaspora fund mobilization and support to repatriate more than 400,000 Ethiopians is virtually untenable.

The cost of repatriation must therefore be borne primarily by the government of Ethiopia. It is unreasonable to expect poor migrants who borrowed and used all family savings to migrate to Saudi Arabia to pay for their transportation to the country they left in the first place. The government ought to also entertain the notion of “regularization or legalization” of migrant workers whose skill sets are in demand within Saudi Arabia. It is inevitable that given lack of opportunities in Ethiopia, many thousands will renter Saudi Arabia, making the administrative costs of repeated reentry and expulsion prohibitive for the Saudis while tarnishing their public image perpetually and irreparably.

Further, the government of Ethiopia owes it to Ethiopian families of migrants to demand that the government of Saudi Arabia stop its barbaric treatment and abusive treatment of Ethiopian migrant workers. In 2013 Human Rights Watch and the Regional Mixed Migration Screening (RMMS) reported that returnees told them that “they were detained for weeks by Saudi authorities in appalling conditions with severe overcrowding, lack of access to air and daylight, sweltering heat and limited medical assistance.

Further Ethiopians suffered from “theft of migrants’ belongings, beatings, sexual abuses, rapes, maiming, flogging and killings.” Sadly, the government of Ethiopia never voiced concern let alone outrage. Given this negligence by Ethiopian officials, the international media did not report the atrocities.

Ethiopians should therefore conclude from this that similar atrocities will persist. If they cannot count on the government to deal with the root causes for their flight, it is unlikely that it will take a different position this time around. Yet, the situation in 2017 is even more ominous and much more urgent. In 2013/2014 165,000 Ethiopians were deported over the course of only 4 months. The United Nations Department of Economic and Social Affairs (UNDSA) estimates that at least 260,000 Ethiopian migrant workers returned to Saudi Arabia in 2016 alone.” UNDSA maintains a data base on the number of legal or regular Ethiopian migrants to Saudi Arabia, which in 2016 numbered 124,000. It does not have an accurate count of irregular or illegal migrants estimated at more than 4 times this number. Sadly, Ethiopians continue to migrate through Yemen and other locations, often risking their lives and human rights. Expulsions alone have done little to nothing to contain the tide.

Reports indicate that the government of Ethiopia has granted 50,000-80,000 entry visas to Ethiopians. At least twenty thousand have returned to Ethiopia. Depending on which source you believe, hundreds of thousands are in limbo and desperate. Reports indicate that Saudi authorities have begun to arrest thousands. These prisoners are housed in concentration camps where they face the prospect of communicable diseases, hunger and ill-treatment.

This humanitarian crisis requires urgent and concerted response from the global community in general and human rights groups such as UNHCR, Red Crescent, the International Red Cross, the International Office for Migration (IOM) and other non-governmental organizations. IOM is best prepared and equipped to facilitate the deportation process while providing sustenance to those in detention centers as it did in Yemen in 2013. It is IOM that quotes the much higher figure of 750,000 Ethiopian migrants in limbo and facing deportation immediately.

The sheer number of these migrants makes it virtually impossible for the government of Ethiopia to repatriate all of them at the same time. Far worse, Ethiopia does not have the economic and infrastructural capacity to accommodate returnees and to restore their lives. This is the reason why the government requested IOM to raise global awareness, mobilize funds, spearhead the repatriation effort, provide post-arrival assistance and assist in the reintegration process.

However, IOM cannot negotiate the terms of treatment of Ethiopians in Saudi Arabia or defend and safeguard that their fundamental human rights and human dignity. It cannot negotiate a longer grace period and time frame. Only Ethiopia’s Ministry of Foreign Affairs and its Prime Minister, Hailemariam Dessalegn can do these.

At minimum, the Prime Minister should make an official visit to Saudi Arabia and make a personal plea to the highest officials of the Kingdom. The Prime Minister should also call on his own government to establish a high level Commission of Experts to look into the root causes of the problem; and come up with long term solutions for this recurring tragedy. Ethiopia should change its national shame image by offering solutions to social ills rather than punish dissent and crush human rights.

In the meantime, Ethiopia’s Prime Minister should commit his government to repatriate all those willing to leave Saudi Arabia free of charge. The safe return of Ethiopians cannot be left to the government of Saudi Arabia that wants them out. Nor can it be left to a third non-governmental organization whose primary role is facilitation.

The government of Ethiopia can no longer mask the problem. It is a national disgrace. It should be honest and bold enough to tell the Saudis and the global community that it cannot accommodate this enormous demand without global funding, including funding from the World Bank.

The large Ethiopian Diaspora has a vital role to play.

It should carry out a concerted global effort by seeking international media coverage by renowned entities such as CNN, BBC and Al-Jazeera.

It should initiate a letter campaign to draw attention to human rights groups.

Last but not least, the Diaspora should muster the courage to alert the global community that the deteriorating human rights situation in Ethiopia is the root cause of the problem; and that the global community should stop shoring up one of the most corrupt, inept and repressive regimes in the world.

In this connection, Human Rights Watch’s report “Detained, Beaten, Deported: Saudi Abuses against Migrants during Mass Expulsions” depicts the structural problems deportees face. “Many arrived back in their countries destitute, unable to buy food or pay for transportation to their home areas, in some cases because Saudi officials arbitrarily confiscated their personal property. Many of the hundreds of thousands of migrants Saudi Arabia has deported in the last year and a half have been sent back to places where their safety is threatened.”

Evidence shows that Ethiopians won’t be safe at home when they return. By all measurements, the condition in Ethiopia is more suffocating, hostile and unwelcoming than it was three years ago.

What should we urge the government of Saudi Arabia to do?

Consider relaxing the departure date

Stop beating, flogging, torturing and abusing Ethiopian migrants; and bring those responsible for injustice including rapes to justice; and treat migrants with due process of international law. In 2013 in a neighborhood of southern Riyadh, where the majority of residents are Ethiopians, at least three Ethiopian workers were killed and numerous maimed and beaten.”
Improve conditions of detention centers for migrants, provide proper shelters, safe drinking water, adequate sanitation and food; and

Allow the Office of the United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR) to exercise its mandate to determine the refugee status of asylum seekers and entertain the noble idea of recognizing a large number of Ethiopians as political refugees similar to other foreign migrants and immigrants.

emf

posted by Gheremew Araghaw

የሺህ አመት ባሏን በሃያ አመት ውሽማ የለወጠችው ከተማ – ያሬድ ይልማ

ሳህለስላሴ የተባለው በስራ ዘርፋችንም ለልቤም ቢሆን ቅርብ የነበረ ወደጄ፣ የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ለትምህርት ከሄደበት አውሮፓ ወደ አገር ቤት ሶስት አመት ሳይሞላው ተመለሰና ፣ እንባ ረጭተን የሸኘነውን ጓደኞቹን አስደነገጠን፡፡ “ምን ሆነህ ነው! ከኤርፖርት እቤት ተመልሰን በወጉ እንባ እና ሲቃችንን ሳናባርድ እንዲ ቀልባችንን የምትገፍፈው? ” ፣ ብለን አምባረቅንበት፡፡ ምክንያቱም የአቶ ሳህለስላሴ ልጅ ፍሬፅዮንን ፣ ሁላችን እጅግ በጣም የምንወደው ልዩ ኢትዮጵያዊ ስለነበር፡ የአሸኛኘቱ ነገር አይረሴ ነበርና ነው፡፡

ያላለቀሰ ፣ ያልተነፋረቀ አልነበረም፡፡ ግን ግን ሶስት አመት ሙሉ የማይደርቅ የሚመስለው፣ ኡመር የተባለው ጓደኛችን ልቅሶ ነበር፡፡ ፍሬፅዮንን ከሸኘንና ኤርፖርት ውስጥ ከገባ ከአራት ሰአት በኋላ ቢራ እየጠጣን ተንሰቅስቆ ሲያለቅስ ያየው፣ ሳምሶን የተባለ ጓደኛችን፣ “ኤጭ በቃ አትነፋረቅብን፣ ምን ቀንተህ ነው እንዴ እንደዚህ እምታላዝነው! በል በቃህ አንደዚህ በማያባራ እንባ አሟርተህበት “ፍሬ” በሄደበት አውሮፕላን ተመልሶ መጥቶ አብራችሁ እንዳታነቡ!” ብሎ አሹፎበት ነበር፡፡ ፍሬን ስናየው የደነገጥነውም ለዚሁ ነበር፡፡

ግን የመጣው እጅግ በጎ ለሆነ ፣ ለዚህ ፅሁፍ መነሻ ለሆነኝና እንደ አስረጂነት የምጠቀምበትን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ማህበራዊ ጥናት ለማካሄድ ነበር፡፡  “ፍሬ” (ቅፅል ስሙ ነው) አውሮፓ ሄዶ ሲያጠናው ለነበረው ትምህርት (International peace, conflict and Justice Management) የመመረቂያ ፅሁፉን መስራት ወስኖ የነበረው “በሃረር ከተማ ልዩ ስሙ “አራተኛ” በተከሰተ ሃይማኖታዊ ምክንያት በነበረው ፀብ ከባድ እልቂትን ሊያመጣ ሲችል ፣ እዛው ከስሞ ስለቀረ ፣ አንድ ልዩ ክስተት” !መነሻ ምክንያቱን እና እንዲሁም – ወዴትም ሳይስፋፋ ድንገት እንዴት ከሰመ? ስለሚለው ዋነኛ ሃቅ ጥናታዊ ድምዳሜ ለመስጠት ነበር፡፡

እንደ ፈረንጅ አቆጣጠር በሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት ገደማ፣ ሃረር አራተኛ በሚባል ሰፈር በጥምቀት በአል ወቅት ፣ በተነሳው በዚሁ ሃይማኖታዊ ምክንያት በነበረው ፀብ ፣ ህይወታቸውን ያጡ የዚያው የሃረር ከተማ ነዋሪ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ከነዚያ ከርስቲያኖች ሞት በኋላ በነበሩት ቀናት ውስጥ የሙስሊም “ኢድ” ስለነበር ፣ ከተራ ነዋሪው እስከ መንግስት ድረስ ፣ ተሰራጭቶ የነበረ ፍራቻ ነበር፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ክስተት መነሻነት በከፍተኛ  የቂም በቀል ስሜት ፣ ልክ እንዳለፉት የክርስትያኖች እጣፈንታ ፣ በእስልምና እምነት ተከታዮች የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ደግሞ የማይቀር እልቂት ይከሰታል ተብሎ፣ ለሳምንታት ሃረር ከተማ ቀይ መብራት እንደበራባት ከቆየች በኋላ፣ በዚህ ምንያት ነው፣ ይህ ስለተደረገ ነው፣  ተብሎ ለመናገር በማይቻልበት መልኩ፣ ያ ደም ያቃባል የተባል የቂም ደመና የት እንደገባ ሳይታወቅ፣ ድንገት የሽብር እና ስጋት ስሜት የገባበት ጠፍቶ፣ ህይወት ዳግም እንደበፊቷ ቀጠለች፡፡

ይህ ሃይማኖታዊ ፀብ መነሻ ያለው ክስተት፣ በሰሜን ናይጄሪያ አሊያም በኮንጎ ተከስቶ ፣ የሟቾች ቁጥር ምንም ያክል ይሁን ፣ የአንድ ወገን ሃይማኖተኞች በሌሎቹ ወገን ሀይማኖተኞች ተገድለው ቢሆን ኖሮ ?፣ መጨረሻው ምን ይሆን እንደነበር መተንበይ ከባድ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ ይህ ፅሁፍም ሆነ የሃረር ከተማ የቅርብ ጊዜ ታሪክ በሌላ አስቀያሚ ቃላት ይፅፍ ነበር፡፡ ግና አገሩ ኢትዮጵያ ሆነና፣ ከተማዋም ሀረር ሆነችና፣ አገር የማጥፋት አቅም ያለውን የእሳት ብልጭታ በእንጭጩ እዛው አዳፍነው፣ ምንም አይነት ሌላ ድራማ ከተማዋ ሳታስተናግድ የሃረር ነዋሪዎች ህይወትን ቀድሞም እንደነበረችው አስቀጠሉ፡፡

ይህ በምን ምክንያት ሊሆን ቻለ? ምንድነው የቺ በአራተኛ የተነሳጭውን የእሳት ብልጭታ፣ ወደ ሙሉ እሳትነት፣ ብሎም ከተማ ሊያወድም ወደ ሚችል ነበልባልነት ሳይቀየር እዛው እርጥብ ብርድልብስ ጥሎበት ባጭር የቀጨው? ይህ ነበር የፍሬፅዮን ሳህለሰላሴ ጥናት ዋና ትኩረት! ጥናቱን ሲያጠናቅቅ ታድያ ያገኘው መልስ አስገራሚ ነበር፡፡

በእዚሁ በምስራቅ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ እና በተለይ ሃረር ከተማ ውስጥ አንጋፋነቱ ሺህ የደረሰ፣ በትክክል ለማስቀመጥ፣ የፍሬፅዮንን ጥናት አገላለፅ “ከጠንካራ ጅማት ተሰፍቶ የተሰራ እድሜጠገብ ብርድልብስ” ዋነኛ አስተዋፅኦ እንደተዳፈነ፣ በሃረር ከተማ ሺህ አመት በኖረው በዚህ ውበት ምክንያት ሆኖ አገኘው! በቀላል አማርኛ ለማጠቃለል፡ በሃረር ከተማ ባለው “ልዩ ማህበራዊ እሴት” ምክንያት ነበር፣ ህዝብ ያልተጫረሰው፡፡

ስለዚህ ይህ የፍሬፅዮን የመመረቂያ ፅሁፍ ጥናት ብዙ ሰዎችን፣ ብዙ መዛግብቶችን አሳትፎ የተደረገበት ምክንያት፣ በተሰማራበት የትምህርት ዘርፍ (International peace, conflict and Justice Management) ፣ አለም ከአፍሪካ በተለይ ደግሞ ከኢትዮጵያ ፣ በዚህ ረገድ መማር እንዲችል፣ ይህንን እልቂትን ፣ እንደዋዛ ጭጭ አድርጎ ያስቀረን ጥብቅ ማህበራዊ እሴት፣ ከሃረር ከተማ ጋር እንደ ባሏ ተቆራኝቷት፣ ሃረር ውቧም አቅፋው ተጋብታው ሺህ አመት አብራ የኖረችው፣ ይህ ልዩ የማህበራዊ እሴት ጉልቻ ፣ ምን ላይ ነው የተመሰረተው? የፀኑት እና እንደ ጠንካራ ጅማት እርስ በእርስ ተሳፍተው እንዲኖሩ ያገዙት ብልቶቹ ምን ምን ናቸው? በሚሉ ጥያቄዎች ጠቃሚ ቁምነገሩን መርምሮ ለማወቅ እና ከትቦ መረጃ ለማስቀረት የተደረገ ስለነበር፣ እንደ በረከት የሚያዙትም፣ ወደፊት ይህንን የማህበራዊ እሴት ሁለንተናዊ ህልውና ፀንቶ መቀጠል እንዳይችል ሊያደርጉ የሚችሉ እና የሚያሰጉ ግልፅ በአመክንዮ የተደገፉ ድምዳሜዎች ካሉም እንደ አደጋ ተመድበው፣ የሚያሳይ ሰነድ ለማጠናቀቅ፣ በዚህም አለማቀፋዊ መማሪያ የሚሆን ጭብጥ ማስገኘት፣ ሃረርንም ከውቡ የሺህ አመት ባሏ-“መቻል” ጋር ሌላ ሺህ አመት እንድትኖር አቻ ፋይዳ የሚሰጥ ትልም ይዞ የተፈፀመ ልዩ ፅሁፍ ነበረ፡፡

ይህ ጥናት በውል ያስቀመጣቸው እና ሃረር ለነዋሪዎቿ በሃይማኖታዊ እንዲሁም በማህበራዊ መስተጋብራቸው ውስጥ የፈጠረችላቸውን ልዩ የኑሮ ድባብ በዝርዝር ሲመለከት ካገኛቸው እጅግ ብዙ ፣ እንዲህ አይነት ብጣሽ ፅሁፍ ዳስሶ ሲጨርሳቸው ከማይችላቸው ፣ ሃረር ከተማ ነዋሪዎች መካከል በዘመን ብዛት ከጎለበቱት የማህበራዊ እሴቶች አንዱን ብቻ ነጥለን ብንመለከት የምናገኘው፣ በሃረሪ ቋንቋ “አፎቻ” -(የጓዳ እድር አይነት ህብረት) ወይም “መሪኛች” -(ጓደኛሞች) የሚል ተለዋዋጭ መጠሪያ ያለው እጅግ የሚያስገርም ፣ ከዚያም ከዚህም የተውጣጣን የማህበረሰብ ክፍል ፣ በአንድ ጠንካራ ጅማት አስተሳስሮ የሚያቆራኝ “እሴትን!” ነው፡፡

በአንድ “አፎቻ” ውስጥ የሚጠቃለሉ የህብረተሰብ ክፍል አሊያም ሰፈርተኞች  እራሳቸውን ሲጠሩ ወይ ሰው ሲጠይቁ፣ “እገሌ የነማን አፎቻ ውስጥ ያለ ነው ? ፣ የነማን እድርተኛ ነው ብለው ነው፡፡ እንደ ሃረር ያንዱ ሰፈር ነዋሪ የአንዱ አፎቻ አባል ለመሆን ያለው መስፈርት ሁለት ብቻ ነው፣ እድሜና ፆታ!፡፡ ከዚያ ውጪ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የዘፈን ምርጫ እና የሚደግፉትም ሆነ የማይደግፉት የእግርካስ ክለብ አሊያም ሌላ ማህበር ለአፎቻ አባልነት አሉታዊም አዎንታዊም ተፅእኖ የላቸውም፡፡

በነዚህ የአንድ አፎቻ አባሎች መካከል ባለው የእድሜ ልክ ማህበራዊ አብሮነት፣ ማለትም በሃዘንም በደስታም እያንዳንዳቸውን የህይወታቸውን ምእራፎች፣ ከሁሉ በፊት ቀድመው እየተደራረሱ፣ ሌላውንም አስተባብረው ከአፎቻቸው አባል ባንዱ ቤት ስላለው በረከት ሳቃቸውን አብረው ሲያስካኩና ሲያስተጋቡ፣ ባንፃሩ ደግሞ በአፎቻቸው አባል ባንዱ ቤት ለሚደርሰው ሃዘንም ከልብ ፣ ለልብ ቀድመው እየተደራረሱ፣ ነው ፣ “መሪኛች” ፍሬፅዮን በ“ልዩ ማህበራዊ እሴትነት” ደምድሞ የመደበውን ውቡን የሃረርን የሺህ አመት ፀጋ -“መቻቻልን” የገነቡት፡፡

በዚህም ትስስር ምክንያት እነ ናይጀሪያ ፣ ማይናማር እንዲሁም ኮንጎ ላይ አንድ የአራተኛውን የሚመስል ክስተት በተፈፀመ በቀናት ጊዜ ውስጥ ሲፈፀም አለም ከሰማው በተቃራኒ ፣ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይጫረስ የምታደርገውን ልዩ ሞራላዊ ስብእና አማርኛ ባንድ ቃል ጠቅልሎ “ይሉኝታ!!!” በሚላት መፍቻ ቃል (Keyword) የሃረር ከተማ ነዋሪዎች እርስ ባንድ ጅማት ታስረዋል፣ ማህበራዊ እሴት ባዳበረው ይሉኝታ፡፡ ስለዚህ እንደተፈራው የአራተኛው የጥምቀት ጣጣ ሌላ የኢድ ቀን መአት ሳያመጣ ባጭሩ፣ ተቀጨ፡፡

ታዲያ በዛው ጥናት ላይ ፍሬፅዮን ፣ ወደፊት ይህ አስገራሚ የማህበራዊ እሴት ጅማት ሳይበጠስ እንዳይቀጥል ሊያደርጉ የሚችሉ፣ አሉታዊ እውነታዎችንም ለማየት ሞክሯል፡፡ እነዚህን የሃረር ከተማ ውስጥ በሚገርም ልዩ ቅመማ የዳበሩና የበለፀጉ ማህበራዊ ትስስሮችን ምን ሊያላላ እና ሊበጥስ የሚችል ግብአት አለ ብሎ ካጠናቸው ነገሮች ውስጥም እንዲሁ በጣት የሚቆጠሩ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ተጨባጭ አቅሞችን ጠቅሶ ነው ያለፈው ጥናቱ፡፡ ታዲያ እነዚህ በጣት ከሚቆጠሩቱ የፍሬፅዮን ጥናት ከለያቸውና ፣ ውቡን የሃረርን ማህበራዊ እሴት ሊበጣጥሱ አቅም አላቸው ፣ ብሎ ካረጋገጣቸው ምክንያቶች አንደኛው በተለየ አይን መታየት እንዳለበት መክሮ ያጠቃልላል፡፡ ይህ በተለየ አይን መታየት ያለበት የሃረር ነዋሪ መፃኢ ጠላት፣ “በታሪክ ውስጥ ያለን ቂም በሃረሪ ቋንቋ ውስጥ እንዲካተት የተደረገበት ልማድ እና ለዚህ ልማድ “ከክልልም ሆነ ከፌደራል መንግስት” የተቸረው ፣ “ ታሪካዊ ቂም በቀልን የማበረታታት” ተልእኮ እና ትኩረት ነው!፡፡

ከዘጠኝ አመት በፊት ፣ የሀረር ከተማ ተወላጅ ገጣሚያንና በደራሲያን ማህበር አባሎች አነሳሽነት፣ ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም ቀድሞ የጠባውን የሀረር ከተtማን የሺህ አመት በአል በልዩ ሁኔታ ለማክበር ቅን ልቡ እና ፍቅር ሰንቀው ለሄዱ ካዲስ አበባ የተነሱ በጎፈቃደኞች ላይ ከደረሰው አሳፋሪ ከታሪክ የሚነሳ ቂም መርዝ የመጀመሪያ ቡኮ፣ አንደኛ መንገድ፣ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት እስከ ተተከለው የቂም ሃውልት ድረስ ሀረር፣ ሺህ አመት ተቆራኝታ አቅፋ ያኖረችውን ከልዩነት ይልቅ በፍቅር ላይ የተመሰረተውን መገለጫዋን፣ ልዩነትን በሚያበረታታው፣ አዲስ እና መጤ የሃሳብ ውሽማ ለመቀየር የፈጀባት ጊዜ አጭርነት አስገራሚ ነው፡፡

አንድ ወዳጄ የዛሬ አራ አመት ገደማ፣ በተለያየ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎችን የሆኑ ሰዎች መሃል ሆኖ ሃረርን ተዘዋውረው ሲመለከቱ ያጀበ ወዳጄ በዚህ ሃረር ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፣ እንደ ኩታ ተሰፍቶላት የለበሰችውን መጤ ቂመኝነት፣ በምሬት ሰነግረኝ እንዲህ ነበር ያለኝ፡፡ ለፍቅር ሲል ታላቋን ሃገሩን ፈረንሳይን ከድቶ ፣ አልፈልግሺም ብሎ የከተመባትን የባለቅኔውን አርተር (ራምባዱ) ራምቦ  መኖሪያ ቤት በአንድ ጎኑ ቀይ ምንጣፍ ተሰቅሎ የቂም ታሪክ የሚነገርበት ስፍራ እስኪሆን ድረስ የሃረር ተጨባጭ ሁኔታ እንዲቀየር ከተማዋ በማይበጅ እና ጠንቅ በሆነ መንገድ ፣ ሆን ተብሎ እየተመራች ነው ፡፡

ለዚህ ማሳያ እንዲሆን የነገረኝ ነገረ በተለይ ልብ የሚሰብር ነበር፡፡ የአርተር ራምቦ መኖሪያ ቤትን ሊጎበኝ ከነበረው ትልቅ የመንግስት ሰው ጋር ሆነው በአጀብ እየጎበኙ፣ የሚያስጎበኘው ሰው በአደሬ ባህል፣ “ነደባ” የሚባል ቤት ውስጥ ስለሚነጠፍ፣ “ከሊም” (ቀይ ምንጣፍ) እና ከሱ ጋር ስለሚያያዘው ከሚኒሊክ ጦር ጋር ስለተደረገው የጨለንቆው ጦርነት ይናገር ነበር አስጎብኚው፡፡ “ይህ ቀይ ምንጣፍ ምንም ያክል ደሃ ብትሆን የአደሬ ቤት ሰው በዘካ ገንዘብ ሳይቀር እንድትገዛው አዋጥቶ፣ ይሰጥህና ትገዛለህ ምክንያቱም፣ ፋይዳው ለህዝባችን ወሳኝ ስለሆነ” አለ ጋይዱ፣ ቀጠለና ፣ ይህ ምንጣፍ በጨለንቆው የአሚረ አብዱላሂ ጦር እና በምኒሊክ ጦር መካከል በተደረገ ጊዜ፣ ህይወታቸው ያለፈውን ሰባት መቶ ሙሽሮች ፣ ቀዩን ምንጣፍ እያዩ ልጆች እንዲያድጉ የምናስታውስበት ነው”- እነዛ ሙሽሮች በዛ ጦርነት በማለቃቸው ምክንያት- “ነመ ሰበ ቢጩ” (አናሳ ህዝብ ) ያለው ብሄር ሆነናል፡፡ “አሁንማ ለስራ ጉዳይ የመጣ ቻይና እንኳን በቁጥር ከአደሬ ይበልጠናል!- ለዚህ ተጠያቂው ምኒሊክ ስለሆነ ቀዩ ምንጣፍ ወሳኝ ነው” አለ ጋይዱ ሳቅ ተከተለው የጋይዱን ንግግር አለኝ ወዳጄ!

ይህንን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወደ ሃረር የሚመጣ ጎብኚ ሳይቀር እንዲሰማ የሚነገረውን ታሪክ ሲናገር ጋይዱ ፣ ደጋግሞ “አህ-መራ- አህ-መራ” እያለ ይጠራ ነበር፣ በዚህ ጊዜ ለጉብኝት የመጣው ሰው ምን ማለት ነው “አህ-መራ” ብሎ ሲጠይቅ፣ የሃረሪ ቋንቋ ተናጋሪ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ለመጥራት “አማሮችን” የሚጠራበት ስም አጠራር እንደሆነ፣ እና ትርጓሜ እንዳለው ተነገረው፡፡ “አህ-መራ” የሚለው ቀጥተኛ ትርጉምም፣ “ቁጭት ሳይ” የሚል ትርጉም እንዳለው አስጎብኚው ሲናገር፣ ስፍራው በብዙ ሰው ሳቅ የአርተር ራምባዱ ግቢ ተናጋ፡፡

እውነት ይህ የሚያስለቅስ እንጂ የሚያስቅ እውነት ሆኖ ነው! ወዳጄ እንደዛን ቀን ሃረር ላይ እየተዘራ ያለውን ፣ የቂም እና በቀል አስተምህሮት፣ ለአንድም ደቂቃ አስቦት ስለማያውቅ እንዴት እንዳዘነ ያስዳኝ፣ ልብ በሚነካ መልኩ ነበር፡፡ ጎብኚ ሳይቀር እንዲረዳው በኩራት የሚነገር ሰሞኑን ሃረር የገባው አዲስ የቂም ትምህርት ማለተ ይሄ ነው፡፡ መድሃኒአለም ፊት ለፊት ካለው ሃውልት እኩል በክፉ መረጃ ትውልድን መመረዝ ማለት እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡ ዩኔስኮ የመቻቻል መዲና ብሎ እውቅና የሰጣት ሃረር፣ ያቺኛዋ ነበረች፡፡ ያቺ ሺ አመት ከጥላቻ እና ልዩነት ይልቅ የፍቅር ቋንቋ ለመላው ኢትየጵያ በተጨባጭ ስታሳይ የኖረችው፣ ሆደ ሰፊዋ ሀረር ነበረች፣ የሺህ አመት ውቢቷ!

ዛሬ ግን ሃረር ያ እውቅናውን ያገኘችበትን ውቡን ማህበራዊ እሴቶቿ በሚያሳዝን ክፋት በሚመሩ ፊት አውራሪዎች እንድትጥል ተገዳ ፣ ከዛ ተምሳሌትነት ከተገባው፣ የከተማ ባህሪዋ ጎድላለች፣ ለብዙዎች ሳይሆን ለጥቂቶች ብቻ እንድትሆን፣ ልዩነትን ረስታ፣ ፍቅርን እያስቀደመች ትሄድበት ከነበረው ስሪቷ በተቃራኒ፣ ቂም እና ክፉ ታሪክን አነፍንፋ የምታፋፋ ፣ የሺህ አመት ባሏን በሃያ አመት ውሽማ የለወጠች ከተማ ሆናለች!

ልብ ያለው ልብ ይበል-ቂም በቀል ክፉ ነውና ሁላችንም ልናወግዘው ይገባል፣ ለኢትዮጵያ አይበጃትምና!!!

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!

ያሬድ ይልማ

posted by Gheremew Araghaw

“አዎ… የትግራይ/ሕወሃት የበላይነት አለ!”

ከስዩም ተሾመ

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል “የትግራይ የበላይነት አለ ወይ?” ለሚለው ጥያቄ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል። “የትግራይ የበላይነት የለም” በሚል ካቀረቧቸው ማስረጃዎች ውስጥ ሁለት ነጥቦች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። የመጀመሪያው የፌዴራሊዝም ስርዓቱ የአንድ ብሔር (ክልል) የበላይነትን አያስተናግድም የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የሕወሃት አባላት በኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሆነ ካቢኔ ውስጥ የስልጣን የበላይነት የላቸውም የሚል ነው። ነገር ግን፣ የአንድ ብሄር (ቡድን) የበላይነት መኖር-አለመኖር የሚለካው በመንግስታዊ ስርዓቱ ወይም በባለስልጣናት ብዛት አይደለም። በዚህ ፅሁፍ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ያቀረቧቸውን ሁለት መሰረታዊ የመከራከሪያ ሃሳቦችን ውድቅ በማድረግ “የትግራይ የበላይነት መኖሩን” በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፌ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

ስዩም ተሾመ

1ኛ) “የትግራይ የበላይነት” የሚረጋገጠው የስርዓቱ መስራች በመሆን ነው! 
በእርግጥ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በፌዴራሊዝም ስርዓቱ መሰረት እያንዳንዱ ክልል ራሱን-በራሱ የማስተዳደር ስልጣን ስላለው የትግራይም ሆነ የሌላ ብሔር የበላይነት ሊኖር እንደማይችል ገልፀዋል፡-

“/የትግራይ የበላይነት/ የሚባለው አንዳንዱ የተዛባ አመለካከት ነው፣ አንዳንዱ ደግሞ ፈጠራ ነው። ከፌዴራል ጀምረህ የስርአቱን አወቃቀር ነው የምታየው፡፡ /አወቃቀሩ ካልፈቀደ/ “የበላይነት“ የሚፈልግም ካለ ስሜት ብቻ ፤ “የበላይነት አለ“ የሚልም የራሱ ግምት ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ …/በኢህአዴግ/ አንዱ በደንብ የገምገምነው እሱን ነው፤ “የትግራይ የበላይነት“ የሚባል የለም ነው፡፡ …ሄደን ሄደን ስርእቱን እንየው ነው፡፡ ስርአቱ “የበላይነት“ እንዲኖር ይፈቅዳል ወይ? የምንፈቅድ አለን ወይ? የትግራይ ብቻ ሳይሆን የሌሎችም፡፡ ይሄ ስርአት ካልፈረሰ በስተቀር ሊኖር አይችልም፡፡ ይሄ ስርአት የትግራይንም የሌላንም የበላይነት አያስተናግድም፡፡ …ሁሉም ድርጅት የራሱን ነው የሚያስተዳድረው፡፡ ህወሓት ኦሮሚያን ወይም አማራ ክልልን ሊያስተዳድር አይችልም፡፡ ስርአቱ አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ በክልል የበላይነት የሚባለው የሌለ አምጥቶ የመለጠፍ ፈጠራ ነው፡፡ ስርእቱ በዚህ መሰረት አልተገነባም አይሰራም፡፡” ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል 

በእርግጥ በፌደራሊዝም ስርዓቱ መሰረት “የትግራይ የበላይነት አለ” ማለት አይቻልም። ነገር ግን፣ በኢትዮጲያ “የትግራይ የበላይነት” መኖርና አለመኖር የሚለካው የሕወሃት ፓርቲ በአማራ ወይም በኦሮሚያ ክልል ላይ ባለው የመቆጣጠር ወይም የማስተዳደር ስልጣን አይደለም። ምክንያቱም፣ በፖለቲካ ውስጥ “የአንድ መደብ/ቡድን/ብሔር የበላይነት” መኖሩና አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል የራሱ የሆነ መመዘኛ መስፈርት አለው።

የአንድ መደብ/ቡድን/ብሔር የበላይነት ራሱን የቻለ ፅንሰ-ሃሳብ ሲሆን እሱም “The Class Domination Theory of Power” ይባላል። በዚህ ፅንሰ-ሃሳብ መሰረት የአንድ መደብ/ቡድን/ብሔር የበላይነት መኖርና አለመኖር የሚረጋገጠው ሌሎች የሚተዳደሩበትን ስርዓትና ደንብ ከመወሰን አንፃር ባለው ችሎታ ነው። “Vergara L.G.” (2013) የተባለው ምሁር የአንድ መደብ/ቡድን/ብሔር የበላይነትን፤ “Domination by the few does not mean complete control, but rather the ability to set the terms under which other groups and classes must operate” በማለት ይገልፀዋል።

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ “የትግራይ የበላይነት” መኖሩና አለመኖሩን ማረጋገጥ የሚቻለው መንግስታዊ ስርዓቱ “የአንድ ብሔር/ክልል የበላይነትን ይፈቅዳል ወይስ አይፈቅድም” በሚለው እሳቤ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ሌሎች ብሔሮችና ክልሎች የሚተዳደሩበትን ስርዓትና ደንብ ከመወሰን አንፃር ትልቁ ድርሻ የማን ነው በሚለው ነው። የአማራ እና ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች የሚተዳደሩበትን በብሔር ላይ የተመሰረተ መንግስታዊ ስርዓት ከንድፈ-ሃሳብ እስከ ትግበራ ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ሕወሃት ነው።

በእርግጥ ዶ/ር ደብረፅዮን እንዳሉት፣ መንግስታዊ ስርዓቱ ሕወሃት የአማራና ኦሮሚያ ክልልን እንዲያስተዳድር አይፈቅድም። ነገር ግን፣ የአማራ ሆነ የኦሮሚያ ክልል የሚተዳደሩበትን መንግስታዊ ስርዓት እና ደንብ የቀረፀው ሕውሃት ነው። ስለዚህ፣ የአማራ ክልል እና የኦሮሚያ ክልል የሚመሩበትን ስርዓትና ደንብ በመወሰኑ ረገድ ካለው ችሎታ አንፃር “የትግራይ የበላይነት” ስለ መኖሩ ምንም ጥርጥር የለውም።

2ኛ) የስልጣን የበላይነት የሚረጋገጠው በፖለቲካ ልሂቃን ነው!
ዶ/ር ደብረፅዮን “የትግራይ የበላይነት” አለመኖሩን ለማሳየት ያቀረቡት ሌላኛው የመከራከሪያ ሃሳብ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ብዛት ነው። ከዚህ አንፃር፣ በኢህአዴግ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ የመወሰን ስልጣን ባላቸው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ የሕወሃት አባል የሆኑ ባለስልጣናት ብዛት ትንሽ መሆኑ ነው፡-

“በፖለቲካ ሃላፊነትም እኩልነት ነው የሚታየው፡፡ በኢህአዴግ ምክር ቤትም ሆነ ስራ አስፈፃሚ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች እኩል ውክልና ያላቸው፡፡ ለምሳሌ አንጋፋው ህወሓት ነው በሚል የተለየ ተጨማሪ ቁጥር አይሰጠውም፡፡ ብዙ ውሳኔ በሚወሰንበት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ከ36ቱ ከሁላችንም እኩል ዘጠኝ ነው የተወከለው፡፡ አብዛኛው ያልተስማማበት ስለማያልፍ ማንም ድርጅት ዘጠኝ ሰው ይዞ የበላይነት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ….ለምሳሌ በካቢኔ አሁን 30 ነን፡፡ ድሮም ዛሬም ህወሓት ሶስት ሚኒስትር ብቻ እኮ ነው ያለው፤ ሶስት ይዘህ ደግሞ እንዴት ነው የተለየ ልታስወስን የምትችለው?” ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

ነገር ግን፣ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና በጠ/ሚኒስትሩ ካቢኔ ውስጥ ያሉት የሕወሃት አባል የሆኑ ባለስልጣናት ብዛት አነስተኛ መሆኑ የስልጣን የበላይነት አለመኖሩን አያሳይም። ምክንያቱም፣ የአንድ ቡድን/ብሔር የስልጣን የበላይነት የሚረጋገጠው በባለስልጣናት ብዛት ሳይሆን በፖለቲካ ልሂቃን (political elites) አማካኝነት ነው። በዚህ መሰረት፣ የሕወሃት የስልጣን የበላይነት የሚረጋገጠው የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ ልሂቃን ከባለስልጣናት በሚያገኙትን አድሏዊ ድጋፍና ትብብር መንግስታዊ ስርዓቱ እና የባለስልጣናቱ ውሳኔ በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማስቻል ነው። ፅንሰ-ሃሳቡን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ያግዘን ዘንድ በድጋሜ ከ“Vergara L.G.” (2013) ፅኁፍ ውስጥ የሚከተለውን እንመልከት፡-

“…political elites are defined as persons who, by virtue of their strategic locations in large or otherwise pivotal organizations and movements, are able to affect political outcomes regularly and substantially. The elites have power over the state, the civil organization of political power. Even though they could have conflicts with the mass, which certainly can affect political decisions from “top down” to “bottom up” the possession of multiples forms of capital (social, cultural, economic, politic, or any other social benefits derived from the preferential treatment and cooperation between individuals and groups) allows [them] to ensure their social reproduction as well as the cultural reproduction of the ruling class.” Elites, political elites and social change in modern societies; REVISTA DE SOCIOLOGÍA, Nº 28 (2013) pp. 31-49.

የፖለቲካ ልሂቃን በመንግስታዊ ስርዓቱ፣ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱና በሲቭል ድርጅቶች ሥራና አሰራር ላይ ተጽዕኖ ማሳረፍ፣ በዚህም የአንድ ብሔር/ፓርቲ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችሉት ሃሳብና አመለካከታቸውን በነፃነት የሚገልፁበት መድረክ ሲኖር ነው። በዚህ መሰረት፣ የስልጣን የበላይነት ባለው የፖለቲካ ቡድን የተለየ አድሏዊ ድጋፍና ትብብር የሚደረግላቸው ልሂቃን የፖለቲካ አጀንዳን በመቅረፅና በብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል የፖለቲካ አመለካከት ላይ ተፅዕኖ እንዲያሳርፉ ምቹ ሁኔታ ይፈጠርላቸዋል።

ከዚህ አንፃር፣ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅን መሰረት በማድረግና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ለማስከበር በሚል ሰበብ ለእስርና ስደት ከተዳረጉት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የመብት ተሟጋቾች ምን ያህሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው? ተቃዋሚ ይቅርና፣ በ2007 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በተካሄደው የኢህአዴግ 10ኛ ጉባዔ ላይ በቀረበው ሪፖርት ላይ የጠባብነትና ትምክህተኝነት አመለካከት አንፀባርቀዋል በሚል ከስልጠና በኋላ የመስክ ክትትልከተደረገባቸው ጀማሪና መካከለኛ የኢህአዴግ አመራሮች ውስጥ ምን ያህሉ የሕወሃት አባላት ናቸው? ከምርጫ 2002 – 2006 ዓ.ም በኋላ ባሉት አራት አመታት ብቻ፤ 19 ጋዜጠኞችን ለእስር፣ 60 ጋዜጠኞች ደግሞ ለስደት ሲዳርጉ ከእነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ የትግራይ ብሔር ተወላጅ ናቸው? ሦስቱም ጥያቄዎች መልሱ ከሞላ-ጎደል “ዜሮ፥ ምንም” የሚል ነው።

ታዲያ የሕወሃት አባላት “በጠባብነት” እና “ትምክህተኝነት” በማይፈረጁበት፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ ልሂቃን “ከግንቦት7 ወይም ኦነግ” ጋር በማገናኘት በፀረ-ሽብር ሕጉ በማይከሰሱበት፣ ያለ ፍርሃትና ስጋት ሃሳብና አመለካከታቸውን በነፃነት በሚገልፁበት፣ የፖለቲካ አጀንዳውን በበላይነት በሚወስኑበት፣ …ወዘተ “የትግራይ የበላይነት የለም” ሊባል ነው። በአጠቃላይ፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ያቀረቧቸው ሁለት የመከራከሪያ ሃሳቦች ምክንያታዊና አሳማኝ አይደሉም። “የትግራይ የበላይነት አለ ወይ?” ለሚለው መልሱ “አዎ…አለ!” ነው። እውነታው ይሄ ነው፡፡

posted by Gheremew Araghaw

እኔ የምለው ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው? (ዲያቆን ዳንኤል ከብረት)

እኔ የምለው ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው? (ዲያቆን ዳንኤል ከብረት)

♦♦የግሪክ፣ የካቶሊክ፣ የሶርያ፣ የሕንድ፣ የሩሲያ፣ የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን ስንክሳሮች ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ በእነዚህ ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ለቅድስና የበቁ አባቶች እና እናቶች ታሪክ ጾም፣ ጸሎት፣ ትምህርት፣ ሱባኤ፣ ትኅርምት፣ ተጋድሎ፣ ሰማዕትነት፣ በድፍረት መመስከር፣ ንጽሕና፣ ተባሕትዎ፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድረግ፣ ለሌሎች መሠዋት አና ሌሎችንም የእምነት እሴቶችን እናያለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡
የሂንዱይዝምን፣ የኮንፊሺየዝምን፣ የዞራስተሪዝምን እና የሌሎችንም የቀደምት ሰዎች እምነቶችንም እንይ፡፡ ጾም እና ጸሎት፣ ምናኔ እና ተጋድሎ፣ ራስን መግዛት እና ይህንን ዓለም መናቅ፣ ማስተማር እና መማር፣ ለሰዎች በጎ ነገር ማድርግ እና ለሌሎች መሥዋዕት መሆን የእምነቶቹ መሠረታውያን እሴቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ማጭበርበርን፣ ማታለልን፣ ስለላን፣ ዘረፋን እና ጥፋትን በቅድስና መንገዳቸው ውስጥ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡

♦♦ነዚህ ነገሮች እንድ ነገር ያመለክቱናል፡፡ ሃይማኖት ስሙ እና ሕግጋቱ ቢለያዩም ከመማር እና ከማስተማር፣ ለራስ የእምነቱን ሕግጋት ከመጠበቅ፣ ከውሳጣዊ ንጽሕና እና ለሌሎች በጎ ነገር ከማድረግ ጋር ፍጹም የተገናኘ መሆኑን፡፡

♦♦የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሳስታለች፤ መሥመርዋን ለቅቃለች ልናስተካክላት ይገባል ብለው የሚያምኑ ሰዎች መነሣታቸውን ከልዩ ልዩ ምንጮች ስንሰማ ከረምን፡፡ እኔ በሃሳባቸው መቶ በመቶ ባልስማማም፤ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ማሰቡ ግን መብቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የሚከራከርበትን ሃሳብ በግልጽ አውጥቶ፤ የማምነው እንደዚህ ነው ብሎ፣ የማይቀበለውን ኮንኖ በሠለጠነ መንገድ ሃሳቡን ካቀረበ ይኼ ሰው ጤነኛ ሰው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
እንዲህ ካለው ጤነኛ ሰው ጋር መከራከር፣ ሃሳቡን በሃሳብ፣ መጣፉን በመጣፍ፣ አባባሉን በአባባል፣ ነቀሳውን በነቀሳ መሟገት እና ቢቻል መግባባት ባይቻል ደግሞ ከነ ልዩነት መኖር ይቻላል፡፡

♦♦በቅርብ አመታት የምንሰማው ግን ከዚህ የከፋውን ነው፡፡ ይህንን ዓይነት አመለካከት የያዙ ሰዎች በመማር እና በማስተማር፣ በመከራከር እና በማስረዳት፣ በግልጽ አውጥተው በማሳየት እና በማሳመን ሳይሆን በማጭበርበር እና በስለላ፣ በማጥፋት እና በማውደም መንገድ እምነታቸውን ለማሥረጽ መሞከራቸውን አየን፡፡
ይኼ ከጤነኛነት ያለፈ መንገድ ስለሆነ እንቃወመው ዘንድ ግድ ነው፡፡

♦♦አንድ ሰው በታቦት ክብር እና ሃይማኖታዊ ዋጋ አላምንም ብሎ የሚያምነውን ማስተማር ይችላል፡፡ ከፈቀድን እንቀበለዋለን፤ ካልፈቀድን በጨዋ ደንብ አንቀበልህም እንለዋለን፡፡ እርሱ በታቦት ሥርዓት ስላላመነ የኢትዮጰያ ቤተ ክርስቲያን ታቦታትን ለማጥፋት፣ ለማስሰረቅ፣ አስሰርቆም ለመሸጥ ከተነሣ ግን ስለ እምነትም ስለ ሀገርም፣ ስለ መብትም ብለን ሰው የተባልን ሁሉ እንቃወመዋለን፡፡
አንድ ሰው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት ላይ ጥያቄ በመጠየቁ ጠላት ነው ብለን አናምንም፡፡ ምናልባት የተለየ አመለካከት ያለው ሰው እንለዋለን እንጂ፡፡ ከራሱ እይታ እና መረጃ ተነሥቶ «ስሕተት ናቸው» ብሎ ማስተማሩንም ባንወድድለትም እናከብርለታለን፡፡ ምናልባት ማስረጃውን በማስረጃ፣ ሃሳቡን በሃሳብ እየተነተንን መልስ እንሰጠው ይሆናል፡፡ ጠላታችን ነው ብለን ግን አንነሣበትም፡፡

♦♦ከዚህ ድንበር ተሻግሮ እርሱ የማይፈልጋቸውን አዋልድ መጻሕፍት ለማቃጠል፣ ለመቆንጸል፣ ከየዕቃ ቤቱ ወጥተው ወደ ባዕድ እጅ እንዲገቡ ለማድረግ፣ ብራናውን ለማበላሸት፣ ቀለሙን ለማጥፋት፣ ዕቃ ቤታቸውን ለማቃጠል ከተነሣ ግን ይህ በእምነት ብቻ ሳይሆን በሀገርም ላይ የተነሣ የታሪክ እና የቅርስ፣ የመብት እና የጤነኛ አስተሳሰብ ጠላት ነውና እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡

♦♦ገዳማዊ ሕይወትን የተቃወሙትን ሁሉ አንጠላቸውም፤ ስላልገባቸው ነው፤ የዕውቀት ማነስ ነው ብለን እንገምታለን፤ ያለበለዚያም ደግሞ ጫፋችንን እስካልነኩን ድረስ በዚህ መንገድ ማመን መብታቸው ነው ብለን እንተዋቸዋለን፡፡ ከዚህ አልፈው ወደ ገዳማት እየገቡ ቅርስ የሚዘርፉ፣ ሴት ገዳማውያንን የሚደፍሩ፣ የተሣሣተ መረጃ በገዳማት ውስጥ የሚነዙ ከሆነ ግን እምነታችንን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ እና ሕጋዊ መብታችንን ተዳፍረዋልና እናጋልጣቸዋለን፤ በሕግ መንሽም ለፍርድ ነፋስ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡

♦♦አንድ ክርስቲያን እስልምና የተሳሳተ እምነት ነው ብሎ ሊያምን ይችላል፡፡ ይህንን አመለካከቱንም ማስተማር እና የተቀበሉትን ማሳመን ይችላል፡፡ የራሱ እምነት ከእስ ልምና የተሻለ ነው የሚልበትን ምክንያት እና ማስረጃ እያቀረበ መከራከር እና መሟገት መብቱ ነው፡፡
ከዚህ አልፎ መስጊድ ውስጥ ገብቶ የጸሎት ሥርዓትን መበጥበጥ፣ የመድረሳ ት/ቤቶችን ማፍረስ፣ የሙስሊም ልብስ ለብሶ ተመሳስሎ በመግባት የእስልምና እምነት አማኞችን ሰላም መንሣት፣ ቁርዓን ማቃጠል፣ የእስልምናን ጥንታውያን ቅርሶች ማጥፋት፣ በእስል ምና ጉዳዮች ምክር ቤት የአሠራር ሥርዓት ውስጥ ሠርጎ የአሠራር ሥርዓቱን መበጥበጥ ከጀመረ ግን ከጤነኛ እና ከሕጋዊ መንገድ አልፏልና ከሙስሊሞቹ ጋር አንድ ሆነን እንቃወመዋለን፤ እንታገለዋለንም፡፡

♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥

♦♦ማንኛውም እምነት ሰይጣናዊነትን ይቃወማል፡፡ በራሱ በሰይጣን የሚያምን ካልሆነ በቀር፡፡ የሰይጣናዊነት ሁለቱ ዋና ዋና መገለጫዎች ደግሞ ክፋት እና ተንኮል ናቸው፡፡ በእምነት ስም ወንጀል ለመሥራት ካልታሰበ በቀር ከእምነት ጋር ክፋትን እና ተንኮልን አሥተሣሥሮ መጓዝ ወተት እና ኮምጣጤን አብሮ ከማኖር በላይ የማይቻል ነው፡፡

♦♦አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እናድሳለን ብለው በተነሡ አካላት ዘንድ የምናየው እና የምንሰማው ነገር የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በመቃወም የተነሣ ሌላ ንቅናቄ አይደለም፡፡ክፋትን እና ተንኮልን አንግቦ የተነሣ አለም አቀፍ ምስጥራዊ ማህበረስ ሰይጣናዊ ንቅናቄ እንጂ፡፡ ዓላማውም ማደስ አይደለም፡፡ኦርቶዶክስን ማፍረስ እንጂ፡፡

♦♦እስካሁን ድረስ በየትኛውም የእምነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለላን፣ ሤራን፣ ማፍረስን፣ ስርቆትን፣ ዘረፋን እና ማታለልን የእምነቱ ማራመጃ መንገዶች ያደረገ ብቸኛ የእምነት ንቅናቄ አለ ከተባለ እርሱ ዛሬ ዛሬ የምንሰማው «የተሐድሶዎች ንቅናቀ» ብቻ ነው፡፡

♦♦ትክክለኛ ነገር አለኝ፤ በያዝኩት ነገር አምንበታለሁ፤ ለያዝኩት ነገርም እከራከርበታለሁ፤ ማስረጃ እና መረጃም አለኝ፤ የኔ መንገድም የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ የሚል አካል ራሱን በይፋ ገልጦ፣ ፊት ለፊት ወጥቶ፣ ሃሳቡን አንጥፎ፣ ማስረጃውን አሰልፎ በብርሃን ይጓዛል እንጂ በጠላት ከተማ እንደ ገባ ሰላይ የድብቅ መንገድ አይጓዝም፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊም መንፈሳዊም ተቋም ናት፡፡ መብቶቿ እና ጥቅሞቿ በሕግ ልዕልና ያላቸው ናቸው፡፡ ተቋሞቿ፣ ንብረቶቿ፣ ት/ቤቶቿ እና ቅርሶቿን የመጠቀም፣ የመጠበቅ፣ የመከባከብ እና ለትውልድ የማስተላለፍ መብት አላት፡፡ በእነዚህ ክልሎች ገብቶ ማንም ሌላ ወገን ያልፈቀደችውን ተግባር በድብቅ እንዳይፈጽም ሕግም ሞራልም ይከለክለዋል፡፡

♦♦አሁን እያየነው ያለነው ተግባር ግን የሃይማኖት አስተምሮን ተቃውሞ ሌላ የተሻለ አስተምህሮ የማምጣት ተግባር ሳይሆን ክፋት እና ተንኮልን ገንዘብ ያደረገ የሤራ ተግባር ነው፡፡ በገዳማት ገብቶ ብራና መፋቅ፣ የአብነት ት/ቤቶችን መበተን፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ገብቶ በርዳታ ስም ሀብቷን መበከል፤ ቅርሶቿን መዝረፍ እና መሸጥ፣ ጥንታውያን ተቋማቷን ማውደም፤ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ንዋያተ ቅድሳትን እና መጻሕፍትን ማበላሸት በምን መመዘኛ ነው የሃይማኖት ሥራ የሚሆነው?

♦♦የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጥንታዊ የክርስትና ትምህርት ጠባቂ፣ የጥንታዊ እና ታሪካዊ የክርስትና ሀብቶች ባለቤት፣ የጥንታዊ መጻሕፍት ግምጃ ቤት፣ የቀደምት ኢትዮጰያዊ ባህሎች እና ትምህርቶች መገኛ፣ የሀገራዊ የአስተምህሮ ጥበብ ማዕከል፣ የቀዳሚ ክርስቲያናዊ ዜማ መፍለቂያ፣ በብዙዎች ዘንድ የጠፉ የአበው ድርሳናት ማከማቻ፣ ልዩ ክርስቲያናዊ ማዕከል ናት፡፡

♦♦በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በሤራ የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በሦስት ነገሮች ላይ የሚሠራ ወንጀል ነው፡፡ በክርስትና ላይ፣ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ እና በሀገር ላይ፡፡
በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ተጀምሮ ምዕራቡን ዓለም መንፈሳዊነት ወደ ተለየው ክርስትና የከተተው የተሐድሶ ነፋስ በክርስትና እና በክርስቲያናዊ ሀብቶች ላይ የማይተካ ጥፋት አድርሷል፡፡ በወቅቱ በተቀሰቀሰው ስሜታዊነት በተሞላው ነውጥ ምክንያት አያሌ ክርስቲያናዊ ትምህርቶች እና ቅርሶች ላይመለሱ ጠፍተዋል፡፡ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ብዙ ሀገሮች ከቀበሩበት ሊያወጧቸው እንደ ዔሳው በዕንባ ቢፈልጓቸው ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡

♦♦በዚህ የተነሣ ታላላቅ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ማኅበራትን አቋቁመው በሌሎች ሀገሮች ያሉ ቅርሶች ተመሳሳይ ውድመት እንዳይደርስባቸው የቻሉትን ሁሉ በፀፀት ሠርተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ከደረሰው ጥፋት በእግዚአብሔር ቸርነት ከተጠበቁት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለዚህ ነበር አያሌ ሚሲዮናውያን እና አሳሾች ቅርሶቻችንን ሲዘርፉ እና ሲተረጉሙ የኖሩት፡፡

♦♦አውሮፓውያን በክርስትና ላይ የሠሩት የማይካስ ወንጀል አምላክ የለሽ ትውልድ እንጂ ጻድቃንን አላፈራላቸውም፡፡ ይህንን ወንጀል ኢትዮጵያ ላይ ለመድገም መነሣት ክርስትናን ያለ ጥግ ማስቀረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ኦርጅናሌው ክርስትና ምን እንደሚመስል በትክክል ማሳየት ከሚችሉ ጥቂት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለዚህ ነው በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በክፋት የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በክርስትና ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against Christianity) ነው የምንለው፡፡

♦♦በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ለውጦች ካመጡት ታሪኮች ዋነኛው ክርስትና ያመጣው ለውጥ ነው፡፡ ለዚህም ነው የክርስትና ታሪክ ከሰው ልጆች ታሪኮች መካከል ዋነኛው ታሪክ የሚሆነው፡፡ ክርስትና ትምህርት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብ፣ የትምህርት መንገድ፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የሥነ መንግሥት ምንጭ፣ ፍልስፍና፣ የሥልጣኔ መዘውር፣ የዓለምን መልክዐ ምድር ቀያሪ፣ የሥነ ጽሑፍ መንገድ፣ የሥነ ሥዕል መርሕ፣ የሥነ ጥበብ ትልም፣ የሥነ ዜማ ስልት፣ የሕዝቦች መገናኛ ድልድይም ሆኗል፡፡ በመሆኑም የክርስትና ሀብቶች እና ቅርሶች የአንድ እምነት ሀብቶች እና ቅርሶች ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሀብቶች እና ቅርሶች ሆነዋል፡፡ በእነዚህ ሀብቶች እና ቅርሶች ላይ እናድሳለን በሚሉ አካላት የሚሠነዘረው ጥፋት በሰው ዘር ሀብት ላይ የሚሠነዘር ጥፋት (crime against human heritage) የሚሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡

♦♦ጥፋቱ ከዚህም አልፎ ሀገራዊ መልክም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን አብዛኛውን ሕዝብ የምትወክል፣ አስተሳሰቡን እና ርዕዮቱን የምትቀርጽ ተቋም ናት፡፡ ታሪኳ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ባህልዋ የሀገሪቱ ባህል፣ ቅርሷ፣ የሀገሪቱ ቅርስ፣ ጥበቧ የሀገሪቱ ጥበብ፣ ዘመን መቁጠርያዋ የሀገሪቱ ዘመን መቁጠርያ ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀሪቱ አንዷ እና ዋነኛዋ መገለጫ ናት፡፡ እናም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሀብቶች ላይ የሚሠነዘር ጥፋት ሁሉ በሀገር ላይ የሚቃጣ ወንጀል (crime against the mother land) ነው፡፡ የሚመለከተውም የቤተ ክርስቲያኒቱን አማንያን ብቻ ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያዊ፣ የሀገሪቱን መንግሥት እና የኢትዮጵያን ወዳጆች ሁሉ ነው

♦♦ኢየሱስና ሐዋሪያት በግልጽ እንጂ እንደ ማፊያ እና ሴጣን በስውር በጓሮ በር አልገቡም ፤ክርስትና ስለላ፣ ሤራ፣ ዝርፊያ፣ውድመት እና ደባ አይደለም። የክርስትናም መንገድ ቀና እና ግልጥ እንጂ ተንኮል እና ክፋት አይደለም።ይህ የክርስትና ሃይማኖትን፤ሊያፈርስ፣ክርስትያኖች ፤ሊያርድ፣ ሊዘርፍ፣በተሃድሶ ስም የተደራጀ አለም አቀፍ የኢሊሙናንት ምስጥራዊ ቡድንን ኢትዮጲያዊ ሁሉ አንድ ሆነን ልንቃወመውና፤ ልናስቆመውምና በትልቅ ቁጣ ልንጋደለው ይገባል፡፡

♦♦ልዑል እግዚአብሔር አለም ሁሉ ውበት የሆነችሁን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከእነዚህ ሴጣናዊ ምስጥራዊ ማህበረሰቦች ይጠብቅልን፡፡

posted by Gheremew Araghaw

ከእርጅናና ከሞት ማን ያመልጣል? ነፃነት ዘለቀ

ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደንበር ገተር፤

እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር፡፡

xxx

“ወያኔ አልጋ ላይ” (የፎቶው ምንጭ – ኢንተርኔት)

መውደቄ ነው ብለህ ልብህ አይበል ፈራ፤

አፄውና ደርጉም ሄደዋል በተራ፤

ደጅህ ደርሶልሃል ያኖርከው መከራ፤

መሰብሰቡ አይቀርም የዘሩት አዝመራ፡፡

በሠራኸው ሥራ ወያኔ ተጀነን! ለፈጸምከው ጀብዱ ምንጊዜም ኮራ በል፤

ኦሽትውዊዝን በሚያስንቅ፣ ሦርያን በሚያስንቅ፣ የመንን በሚያስንቅ

የዘመናት ልፋት ዘር የማጽዳት ግብርህ ዓለም አድንቆሃል፡፡

ትናንት ማታ አንዱ እንዲህ ሲል አወጋን፡፡ ባካፍላችሁ እንደምትዝናኑበት በማመን ይሄውና ከኔ እንዳይቀር አደረግሁ፡፡

በዚያን ሰሞን በአዲስ አበባ ከተማ የጦፈ የመንገድ ላይ ፍተሻ ነበረ አሉ፤ ይህ ነገር አልፎ አልፎ እንደሚከሰት አውቃለሁ፡፡ ወያኔዎች በተሸበሩና በደነበሩ ቁጥር በየመንዱና በየሰፈሩ ሰውንና መኪናን እያስቆሙ ይፈትሻሉ – ከዱሮም፡፡

አንድ አካባቢ በተደረገ የቅርብ ጊዜ ፍተሻ ሁለት ሽማግሌዎች እንዲፈተሹ ሦስት የወያኔ ፌዴራል ፖሊሶች ያስቆሟቸዋል አሉ፡፡ እዚያው በፍተሻው የነበረ ሰው ነው የሚነግረን፡፡ መገናኛ ሬዲዮ የያዘው ከሦስቱ ፈታሾች አንዱ የመሀል አገር ሰው ይመስላል፡፡ ሌሎቹ ደቡብ ናቸው – የወያኔ ልክፍት ተጋብቶብን ሰውንና ንብረትን ሳይቀር በዘውግና በአቅጣጫ ስም መጥራትን አሁን አሁን በሚገባ ተለማምደናል፡፡ የወያኔ የጦርና የፀጥታ ሰዎች በአብዛኛው ከደቡብና ከጋምቤላ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ ከሕዝብ ጋር እንዳይመሳሰሉና የሕዝብን ባህልና ወግ፣ ቋንቋና እምነት እንዳይጋሩ በወያኔ የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ነው፡፡ ለማንኛውም  እነዚያ ሽማግሌዎች ተፈተሹ ሲባሉ አሻፈረን አሉ፡፡ “በገዛ ሀገራችን ለምንድን ነው የምንፈተሸው?” ብለው አካኪ ዘራፍ ይላሉ፡፡ ሰዎቹ ለመፈተሽ ፈቃደኛ ካልሆኑ ውስጣቸውን ገልቦ አብጠርጥሮ እንደሚፈትሻቸው አንዱ ደቡቤ ፌዴራል በራሱ አማርኛ እያስፈራራ ይገስጻቸዋል፤ በወያኔ ቤት መደዴነት ትልቁ ጨዋነት ነውና ትልቅ ሰውን ማክበር እንደወንጀል ይቆጠራል – አቤት ሰውን በማዋረድና በመሳደብ እንዴት እንደሚደሰቱ ብታዩዋቸው! … ሰዎቹ በእምቢታቸው ጸኑ – ለጽናታቸውም አንዱ ቀጭን ሰበብ ውኃ ቢጤ ቀምሰው ለብ ያላቸው መሆኑ ነው ተብሏል፡፡ አጠገብ በነበሩ ሰዎች ተማጽኖ ፍተሻውን እንደነገሩ ዳበስ ተደርገው እንዲያልፉ ተደረገ፡፡ ሰዎቹ ካለፉና ራቅ ካሉ በኋላ አንደኛው ሽማግሌ ፌዴራሎቹን ይጣራና “ስማ አንት ወታደር፤ አታውቅም እንጂ ጡትና መንግሥት ዱሮውንም ቀስ ብሎ መውደቁ አይቀርም! አትጃጃሉ!” ያኔ የመሀል አገር ሰው የሚመስለው ሰልጠን ያለው ፌዴራል በጁ የያዘውን ሬዲዮ መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ በሣቅ ሞተ፡፡ ሰው የሆዱን ሲነግሩት ከልቡ ይስቃል ይባላል አይደል? ሌሎቹ ግን ፊታቸው እንደሳት ግሞ የሚያደርጉትን አጡ፡፡  በሰዎቹ ላይ ግን እርምጃ አልወሰዱባቸውም፡፡ የወያኔ ቅልብ ጦር እኮ እንደሚታወቀው ግደል እስኪባልም አይጠብቅም – ግደል ሲሉት “ለምን?” ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ “ስንት ልግደል?” ማለቱ እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ደነዝ ፌዴራሎች ትኩር ብለህ ካየሃቸው እንኳን ራሱ ሊገድሉህ ይችላሉ፡፡ ሰው ናፈቀን፤ እውነተኛ ሀገር ጠባቂ የሕዝብ ሠራዊት ናፈቀን፤ ሃቀኛ ዳኛ ናፈቀን፤ መምጣቱ መቼም ቢሆን የማይቀረው ቀን ራቀብን፡፡…

posted by Gheremew Araghaw

ከፍሬያቸው አወቅናቸው!!!

K. Teshome

ሰኔ 2009

ዛፍ፣ እጽዋት እና አዝእርት ፍሬ እንደሚያፈሩ ሁሉ ድርጅትም ፍሬን ያፈራል:: የድርጅት መልካም ፍሬዎች የሚባሉትም ማልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ ወዘተ ናቸው:: የዛፍ፣ እጸዋት፣ አዝእርት ፍሬዎች ሁኔታ የሚወሰነው በአፈሩ ንጥረ ነገር ፣ የአየር ንብረቱ ሁኔታ ፣ ሙቀትና የጸሀይ ብርሀን እና በሚያገኘው ውሃ እንደሆነ ሁሉ የአንድ ድርጅት ፍሬ የሚወሰነውም ድረጅቱ ውስጥ ባለው የሰው ሁኔታ፣ ፖሊሲ፣ ገንዘብ እና ቁሳቁስ ነው:: የዛፍ መልካምነቱ  በፍሬው ይታወቃል የሰውም መልካምነት በንግግሩ እና በምግባሩ ይገለጣል እንደሚባለው ሁሉ የአንድ ድርጅትም መልካምነት በግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ህይዎት ላይ በሚያደርገው ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ ግንባታ ነው:: በዚህች አጭር ጽሁፌ አሁን ሃገራችንን እያስተዳደረ ያለው ወያኔ/ኢሃደግ የተባለው ድርጅት  ካፈራቸው ፍሬዎች አንዱ የሆነውን  ዘረኝነት ነው::

የሀገሬ ሰው ደርግ ተብሎ  የሚጠራው ድርጅት ፍሬው መራራ ስለሆነበት ያለ የሌለ አቅሙን አሰባስቦ በገዘገዘው እና  ባዳከመበት ወቅት ወያኔ የተባለው ታጣቂ ድርጅት ከበረሀ ወጥቶ አጋጣሚውን በመጠቀም በትረ ስልጣኑን በሃይል ነጥቆ ወሰደ:: ሁላችሁም እንደምታውቁት ወያኔ በተረ ስልጣኑን ሲይዝ ምን አልባት መከላከያ  በሚባለው ቀንዱ የመዋጋት አቅም ካልሆነ በስተቀር ታላቁን የኢትዮጵያን ህዝብ የማስተዳደር አቅምም አልነበረውም:: በሰው ኋይሉም፣ ባስተዳደር እውቀቱም ሆነ ልምዱ፣ በፖሊሲውም ፣ በፖለቲካውም  ያልበሰል እና እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም:: ዘረ ከልጓም ይጠቅሳል እንደሚባለው አዲስ አበባ ቤተ መንግስት ላይ ተቀምጦ ህዝብ አስተዳድራለሁ እያለ ሃሳቡ እና ምግባሩ ግን ያው የበረሀ ማንነቱን የሚያንጸባርቅ ነበር:: በዚህም የተነሳ ሃገሪቱ በግምት ስትመራ ቆይታለች::

በወያኔ ዙሪያ እና ላይ ተንጠላጥለው ያሉ ሰዎችም አይዞዋችሁ ወያኔን በትዕግስት ጠበቁ ሲጠነክር የዲሞክራሲ ካባ ትለብሳላችሁ፣ የዲሞክራሲ ጫማ ትጫማላችሁ፣ በብሄርተኛ ዲሞክራሲ ልጥ አንድ ትሆናላችሁ፣ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ትተነፍሱ የነበራችሁ ኦክስጅን ትተነፍሳላችሁ፣ ራባችሁ በጥጋብ፣ ጥማችሁ በርካታ ይሻራል እያሉ ለህዝቡ ተስፋ ሲሰጡ ዘመናት አለፉ :: የሃገሬም ሰው በዚህ የተስፋ ቃል አምኖ እና ተስፋ ሰንቆ “ በለስዋን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል” የሚባለውን ተረት እየተረተ የወያኔን መልካም ፈሬዎች ይጠባበቀ ነበር:: ከጊዜ ጊዜ ህዝቡ ወያኔ ወደፊት የሚያፈራቸው ፍሬዎች መልካም አለመሆናቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ቢያይም እና ስድስተኛው የስሜት ህዋስ ጥርጣሬ ቢፈጥርበትም የሀገሬ  ሰው ግን ለማመን የማይቸገር ስለሆነ የወያኔን የተስፋ ፍሬዎች ትእግስትን ገንዘብ በማድረግ ለብዙ አመታት ሲጠብቅ ቆይቷል:: ወያኔ ግን አድሮ ቃሪያ መሆኑ በተደጋጋሚ ይታይ ነበር::

ከብዙ አመታትም በኋላ ወያኔ የተባለው ድርጅት ሌሎችን ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተቋማት በማንቋሸሽ እና ሽባ ካደረዳቸው በኋላ እራሱን በፖለቲካ፣ በአደረጃጀት፣ ኢኮኖሚ እያጠነከረ መጣ:: መከላከያ የተባለ ቀንዱም ጠነከር፤ እንዳውም ፊደራል ፖሊስ የተባል እሾህ አወጣ:: ወያኔም የማይታዘዙትን እና የሚቃወሙትን ሁሉ በእሾሁና እና በቀንዱ እያስፈራራ እና እየተዋጋ አፍ ማስያዝ ጀመረ::

ቆይቶም ወያኔ የተባልው ድርጅት ብዙ ክፉ ፍሬዎችን አፈራ፦ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ሙስና፣ ትዕቢት፣ ውሸት ወዘተ የሚባሉ ፍሬዎችን::  የወያኔ አባዋራዎችም የዘረኝነት ፍሬን ከበሉ በኋላ ለኦህደድ፣ ብአዴን ወዘተ ሰዎች አበሉዋቸው:: እነርሱም በተዋረዳቸው በቴሌቪዠን፣ ሬድዮ፣ ጋዜጦች እና ስብሰባ መድረኮች ላይ ደግሰው ለካድሬዎቻቸው እና ለህዝቡ መገቡት:: የወያኔ ሰዎችም የዘረኝነትን ፍሬ ሲመግቡን መብታችሁ ይከበራል፣ ዲሞክራሲያዊ ትሆናላችሁ፣ የራሳችሁንህዝብ ትመራላችሁ፣ የራሳችሁን  እጣ ፈንታ  ትወስናላችሁ በሚል መሸንገያ እና ማታለያ ቃል በመጠቀም ነበር::አይጥ መብላት በምትፈለገው ምግብ እንደምትጠመድ ሁሉ እኛንም  የወያኔ ሰዎች በምንፈልገው ዲሞክራሲ ስም አጠመዱን::

መራራ የሆነው የዘረኝነት ፍሬም በዲሞክራሲ ተለውሶ የተሰጠን ስለነበር አፍ ላይ ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር:: ቀስ በቀስ ግን የሚያሰክር፣ ማስተዋልን የሚነጥቅ፣ አእምሮን የሚያሳጣ እርስ በእርሳችንም እስከ አለመተዋወቅ ያደረሰ፣ እኛ የመባባል ባህላችንን ደፍጥጦ አንቺ፣ አንተ፣ እናንተ መባባልን የፈጥረ ሁኑዋል:: እኛም የዘረኝነትን ፍሬ ከበላን ጊዜ ጀመሮ አያቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን ካቆዩልን የአንድነት ትልቅ ክብር ተለየን፣ እርስ በእርሳችንም እስከ አለመተዋወቅ ደረስን:: የስካር ደረጃው የተለያየ አይደል! አንዳንዶቻችን እማ በዘረኝነት ፈሬው በጣም ሰለ ሰከርን በእማማ ኢትዮጵያ ስም መጠራትን አንፈለግም::

ሰው የዋጠውን ይተፋል፤ ያነበበውን ይናገራል እንደሚባለው ሁሉ እኛም አሁን የዋጥናትን የዘረኝነት ፍሬ በንግግር እና በትግበራ እየተፋናት በአለንጋዋም  እየተገረፍን  እንገኛለ:: እነሆ ዘረኝነት ለወያኔዎች  ስልጣን ማራዘሚያ ለእኛ ግን የድህነት፣ የጭቆና፣ አለመግባባት፣ እርስ በእርስ መለያያት እና ለተለያዩ መከራዎች አጋልጦናል:: እንዳውም አሁን አሁን እማ በዘረኝነት የመረዙን ወያኔዎች ሁቱ እና ቱሲ የበሉትን የዘረኝነት ፍሬ ካበሉን በኋላ በሁቱ እና ቱሲ መልሰው ያስፈራሩናል:: ለህጻን ልጅ የሚያስፈራራ መጫዎቻ ገዝቶ ሲጫዎት እንደገና በመጫዎቻው ማስፈራራት እንደ ማለት ነው:: አማራ እና ኦሮሞ  እሳት እና ጭድ ናቸው እስከ ማለት ያደረሳቸው የዘረኝነት እጀንዳቸው ነው:: እስቲ ዘረኝነት በተግባር ያመጣብንን የተወሰኑ አመላካች ጣጣዎች እናንሳ::

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ጉራፈርዳ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ በሚባሉ አካባቢዎች የተሰማው የአደጋ ደወል ድምጽ የዘረንነት ፍሬ አይደለም?

ብዙ ቁጥር ያላቸው በጉራፈርዳ ይኖሩ የነበሩ ግብር ከፋይ አማርኛ ተናጋሪዎች በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሚመራው የክልል መንግስት ጫካ አቃጠላችሁ በሚል ሰበብ አገራችሁ ተመለሱ የሚል ዘር–የማጥራት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል :: ከጉራፈርዳው ዘር– ማጥራት ወንጀል በተጨማሪ  በመጠኑ የላቀ እና በአይነቱምየከፋ ብዙ ሺ አማርኛ ተናጋሪዎችን ያፈናቀለ ዘር–ማጥራት በቤንሻንጉል–ጉምዝ ተደገመ። በዚኽን ጊዜ የፌደራሉ መንግስት ምንም እርምጃ ሲወሰድ አላየንም:: ይህ የሚያሳየው የመንግስት አጀንዳ ዘረኝነት መሆኑን ነው::

በኦሮምያ እና አማራ ክልል ያሉ ህዝቦች መብታችን ይከበር፣ በዘራችን ምክንያት የምንናቅ እና የምንሰደብ መሆን የለብንም፣በሃገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ ልንቆጠር አይገባንም፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን አለብን ብለው ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መልኩ ሰላማዊ ተቃውም በማሰማታቸው ብቻ ወያኔዎች ጦርነት አውጀው ብዙዎቹ በአደባባይ በጥይት ተገድለዋል፣ በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ ታስረዋል፣ ድብደባ እና ሌሎች ሰቆቃዎች ደርሰውባቸዋል:: ለኦሮምያ እና አማራ ህዝብ መብት መከበር በሰላማዊ እና ህገ መንገስቱ በሚፈቅደው መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች እና አባሎቻቸው በወያኔ ካድሬዎች እየተያዙ በአሸባሪነት፣ አመጽን በማነሳሳት፣ መንግስትን በሃይል በመገልበጥ ወንጀል ተከሰዋል:: የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ አመራር የሆኑት እነ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እና በቀለ ገርባ አሁን እስር ቤት ያሉት ወንጀል ሰርተው ሳይሆን በዘራቸው እና በፖለቲካ አመለካከታቸው ነው:: ታዲያ ይህ የዘረኝነት አይደለም?

የምናየው በአንድም ሆነ በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ውስጥ ያለው ፍጥጫ፣ መቃቃር፣ መገዳደል፣ ጥላቻ የወያኔ የዘረኝነት ሴራ ውጤት ነው:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሁለት ሲኖዶሶች እየተመራች ትገኛለች:: አንዱ የሃገር ቤት ሌላው የውጩ ሲኖዶስ እየተባል:: ይህ የሆነው የቤተክርስቲያኒቱ ስርአት በማይፈቅደው ሁኔታ አሁን ከሃገር ውጪ ያሉት ፓትሪያሪክ ከመንበራቸው በወያኔ መሪዎች በግዳጅ እንዲለቁ ከተደረገ በኋላ ከራሳቸው ወገን የሆነውን  ፓትሪያሪክ በመሾማቸው ነው::  በጅማ፣ በአርሲ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ግጭትን በመፍጠር ብዙ ህይዎት እና ንብረት የወደመው በወያኔ የዘረኝነት ሴራ ነው::

በታሪክ አይተነው ሰምተነው በማናውቀው ሁኔታ በካርታ ላይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና ራስ ደጀን ተራራ ወደ ትግራይ የገቡት፣ የትግራይ ክልል የጎንደርንና ጎጃምን መሬት ቆርጦ ቤኒሻንጉል ክልል ጋር ድንበርተኛ የሆነው በወያኔ የዘረኝነት ተንኮል ነው::

በየቢሮዎቻችን አዳዲዲስ አለቆች ተሹመው ሲመጡ ሰለ እነርሱ መጀመሪያ ማዎቅ የምንፈልገው ስለ ምናቸው ነው? የአመራር ብቃታቸውን? የትምህርት ደረጃቸውን እና ልምዳቸውን ? ወይንስ ዘራቸውን? ብዙዎቻችንን  የሚያስማማን አንድ መልስ ይመስለኛል እርሱውም ዘራቸውን የሚለው ነው:: ይህ ታዲያ ዘረኝነት አይደለምን? እንዲህ እንድናስብ ያደረገን የወያኔ የዘረኝነት ፍሬ ነው::

ከደርግ ዘመን በእጅጉ በተቃረነ ሁኔታ ሀገራችን ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰባቸው ሃገሮች ተርታ ናት:: በወያኔ  የአገዛዝ ዘመን እስካሁን ከ30 ቢሊዮን ዶላር ባላይ ከሀገር ወጥቷል:: በ 2009 ዓም እንኳን  በ3 ወራት ውስጥ ከ 3 ቢሊዮን ዶላሮች ባላይ ከሀገራችን ወጥቷል:: ማነው ኦሮሞ ባለስልጣን  ከትግሬው ጋር ሙስና የሚሰራ፣ ማነው አማራ ባለስልጣን ከኦሮሞው ጋር የሚሰርቀ:: የወያኔ ባለስልጣናት በዘር፣ በጎጥ፣ በአካባቢ ልጅነት እየተሸፋኑ እና እየተደባበቁ ነው የህዝብን ንብረት የሚዘርፉት::

በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የተሰሩ ህንጻዎች ባለቤትነታቸው የማን ነው? የትግራይ ተውላጆች እንደምትሉኝ አልጠራጠርም:: ትክክልም ናችሁ፤ ይህ የአደባባይ ሚስጢር ስለሆነ:: ይህ የሆነው አማራው፣ ኦሮሞው ወይንም የሌላው ብሄር ተውላጆች ህንጻ መገንባት ስለማይችሉ ሳይሆን እነዚህ አይነገብ የሆኑ ቦታዎች ለእነርሱ ስለማይሰጣቸው ነው:: እነዚህ ቦታዎቸ በአብዛኛው ለትግራይ ተወላጆች ብቻ መባዎች ናቸው:: ታዲያ ይህ የዘረኝነት ፍሬ አይደላም?

ይህ የዘረኝነት መንፈስ እና መለያየታችን በዚሁ ከቀጠለ የወያኔ መንግስት አብዝቶ በጂራፍ እየገረፈን፣ በጥይት እየቆላን ግዛቱን ያጸናብናል፣ በብራት አለንጋም ይገርፈናል::

ስለዚህ ህዝባችን እንደ እኔ ሁለት አማራጭ አለው ብየ አምናለሁ::  ህይውት ምርጫ ስለሆነ ከሁለት አንዱን መርጦ መኖር ያስፈልጋል:: አንደኛው በሃገራችን ባእድ እና ባሪያዎች ሁነን መኖር:: ምርጫችን ይሄ ከሆን ደግሞ አፋችንን ሸብበን፣ ሲያስሩንም፣ ሲገድሉንም እንደሚታረድ በግ ሁነን መኖር:: እነርሱም እርስ በእርሳችንን እያናከሱን፣ እያጋጩን እና እያጋደሉን ይኖራሉ:: እኛን በዘረኝነት ማህረብ ጨፍነው ያለንን ሁሉ ከወሰዱ በኋላ ሃገራችንን በታትነዋት በስልጣንም ማርጀት ስለማይቀር ሲያረጁ ስልጣን ለቀው ይሄዳሉ::

ሁለተኛው ደግሞ እስካሁን እሺ ብለናቸው ለውጥ ስላልመጣ ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈሳችንን ይዘን ለውጥ ለማምጣት  መጣር:: ከወያኔ ካደሬዎች ውጪ ያላችሁ ሰዎች ይህን አማራጭ እንደምትመርጡ አያጠራጥርም:: ምርጫችን ይህ ከሆነ ደግሞ ምንም እንኩዋን የዘረኝነት እና መለያየት ዋና ምክንያት ወያኔ ቢሆንም ሰው የችግሩ ፈጣሪ ነው እንደሚባለው ሁላችንም በተለያዩ ደረጃዎች አሁን ላለንበት ችግር ድርሻ አላለን ማለትም በግለሰብ፣ በቡድን፣ በማህበረሰብ እና  በተቋም ደረጃ ለችግሩ አስተዋጾ ያደረግን ስለሆነ ሁላችንም የችግሩ አካል ሁነን ልንሰራ ይገባል:: ስለሆነም በተለያዩ ደረጃዎች ምን ምን ስራዎች ሊከወኑ እንደሚገባ የማምንበትን ነገረ እንደሚከተለው አስቀምጫሁ::

በግለሰብ ደረጃ ፦ ብዙዎቻችን ሳናውቀው የወያኔ ተልዕኮ ማስፈሚያ ሁነናል ብየ አምናለሁ:: እንደ ግል እያንዳንዱ በዘረኝነት መርዝ ሃሳቤ፣ ንግግሬ እና ምግባሬ ተበክሉዋል ወይ በሎ መጠየቅና እራስን ማስተካከል፣ በዘረኝነት አስተሳሰብ ፋንታ አእምሮዋችን ጸረ ዘረኝነት አስተሳሰብ እንዳስብ ማስለማድ፣ ምላሳችን አንድነትነን እና ፍቅርን የሚሰብክ፣ምግባራችንም አንድነትን የሚገልጥ ሊሆን ይገባል:: እያንዳንዱ ግለሰብ ከተስተካከለ ቤተሰብ፣ ማህበረሰብ፣ ነገድ ፣ ጎሳ እና ሀገር ይስተካከላል:: ሌላው እራሳችንን የዘረኝነት ቫይረስ ከለከፋችው እና ዘረኝነትን ከሚያራምዱ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ሚዲያዎች  ማራቅ ይገባል:: ቢቻል እነዚህ አካላትን ማንቃት ሳያውቁት ለወያኔ የከፋፍለህ ገዛው ፖሊሲ ባንዳ ሁነዋልና:: እነዚህ አካላት ለወያኔ አገዛዝ ህልውና በመሆን የህዝብን መከራ ያራዝማሉ እንጂ መለያየትን እየሰበኩ ለውጥ አያመጡም:: “አንድነት ሀይል ነው” እና “እርስ በእርስዋ የተለያየች መንግስት አትጸናም” የሚለው መልእክት አልገባቸውምና::

ሁለተኛ ከወያኔ የአገዛዝ ቀንበር ውጪ የሆኑ የህዝብ ልሳንናት ሚዲያዎች እንደ ኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ፣ የአሜሪካ ድምጽ  የአማረኛ ሬድዮ፣ የጀርመን ድምጽ የአማረኛ ሬድዮ፣ ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ እና ሌሎችም የወያኔ ልሳናት የሆኑ ሚዲያዎች የሚዘሩትን የዘረኝነት እና የመለያየት አስተምህሮ ሊመክቱ ይገባል:: አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መተሳሰብን ሊሰበኩ እና ሊያስተምሩ ይገባል::

ሶስትኛ ከክፉ ዛፍ ስር ምሳር አለ ዛፉም ይቆረጣል ፍሬው መራራ ነውና  እንደሚባለው  በዋናነት ዕፀ ዲሞከራሲ፣ ዕፀ ነጻነት፣ ዕፀ አንድነት ፍሬ ይሰጠናል ብለን ከካጫካ መጥቶ ቤተ መንግስት ሲገባ ዝም ያልነው ወያኔ በዲሞክራሲ ሲያጭበረብር ቆይቶ ወደለየለት ዘኝነት፣ ኢ-ዲሞከራሲያዊነት እና ጭቆና ስለተቀየረ፣ ህዝቡን ቀንድ እና እሾህ በሆኑ መካላከያ እና ፖሊሶቹ እያስፈራራ እና እየገደለ ስለሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ በፊት በደርግ እንዳደረገው ሁሉ የወያኔን አገዛዝ ተባብሮ መጣል ነው:: ይህ ከሆነ እኛ ከዘረኝነት መርዝ የምንፈወሰ እና የምንነጻ መልሰን አንበከልም ፤ የወደፊቱንም ትውልድ ከዘረኝነት አባዜ ታድገን ሀገራችን ወደፊት እንድትራመድ ማድረግ እንችላለን::

በአራተኛ ደረጃ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጎጠኝነትን ማራመድ ትተው ህብረ ብሄራዊነትን ገንዘብ ቢያደርጉ:: በ1997 ዓም  በተደረገው ምርጫ ቅንጂት ምርጫ አሸንፎ የነበረው ብሄረተኛ ሳይሆን ብሄራዊ ፓርቲ ስለሆነ ነው ብየ አምናልሁ:: የፖለቲካ ፓረቲዎች ህዝቡን አንድነት ሊሰብኩ ቢችሉ:: እኔ ይገርመኛል አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች እንኳን ሀገራዊ ራዕይ ጠንከር ያለ እንኳን አካባቢያዊ ራዕይ የላቸውም:: አንዳንዶቹ ፖለቲካን ድህረ ጡረታ ስራ አድረገው ስለቆጠሩት ሳይለወጡም ፣ ሳይለውጡም የለውጥ እንቅፋት እና አሰተጓጓይ ሁነው ይታያሉ:: ወያኔም እንደ ባንዳነት የሚጠቀምባቸው እነዚህን ነው:: እንደዚህ አይነት የፖለቲካ ድርጅቶች ሊጠፉ ይገባል:: በምትኩ ብሄራዊ ራዕይ ያላቸውን ድርጆቶችን መደገፍና ማጠናከር መልካም ነው በዬ አምናለሁ::

በአምስተኛ ደረጃ የሃይማኖት ተቋማት ከፖለቲካ ገለልተኛ ሁነው ከህዝቡ ጋር ቅርበት እና ተቀባይነት ስላላቸው የእምነቱ  ተከታዮችን ስለ አንድነት፣ ፍቅር እና  ሰላም አጠናክረው መስብክ ቢችሉ:: ከዚህም አልፎ ዘረኝነት እንደ አንድ የመወያያ አጀንዳ ተይዞ መድረክ ተዘጋጅቶለት ውይይት ማድርግ ተገቢ ነው:: ቤተ እምነቶችም መንግስት የሀይማኖት ተቋማትን እየተጠቀመ የሚዘራውን የዘረኝነት ጥፋት ስራ እምቢ ሊሉ ይገባል:: እንድዚህ ሲሆን ነው ወያኔ የኢኮኖሚ፣ ፍትህ፣ ትምህርት፣ማህበራዊ፣ የፖለቲካ እና የባህል ተቋማትን እየተጠቀም የሚዘራውን ዘረኝነት መቋቋም የሚቻለው::

posted by Gheremew Argahw

Travel Warnings in the Land of 13-Months of Sunshine By Prof. Al Mariam

U.S and U.K. issue warning to their citizens planning travel in  Ethiopia

Time was tourists flocked to Ethiopia in search of the “Land of 13-Months of Sunshine” and adventure. Ziggy Marley, son of the late great reggae king Bob Marley, even wrote a song about it:

13 Months of Sunshine/Is what we got/Take us to, take us to, take us to that land/Who shall ascend the hill/Stand in that holy place/Lift up your heads/

O ancient gates/13 Months of Sunshine/Is what she got/Forward to , Forward to , Forward to that land/Where the water run (free)/We want to be

In 2017, the song heard from the U.S. of A and the U.K. is, “Get away, begone from that Land!”

For the past quarter of a century, Ethiopia has become “Land of 13-Months of Darkness” under the corrupt tyrannical rule of the Thugtatorship of the Tigrean People’s Liberation Front (T-TPLF). Some 400 thousand Ethiopians have fled to Saudi Arabia alone, the vast majority are “undocumented”. Millions of others scattered throughout the world. Ethiopians are leaving their country by sea, land and air to escape oppression, injustice, brutality, abuse, persecution and the indignity of second class citizenship under T-TPLF rule. They cry out, “Take us out of the Land of 13-Months of Darkness because we can’t breathe with T-TPLF boots on our necks”.

Now the Governments of the U.S. and U.K. are advising their citizens, in no uncertain terms but with diplomatic delicacy, “Avoid Ethiopia like the plague! If you travel to  Ethiopia and get in a jam, and the likelihood of getting jammed is high, you are on your own. Don’t call us because you can’t. Normal communications are shut down. We can’t help you.”

On June 13, the U.S. State Department issued a “Travel Warning” advising

U.S. citizens of the risks of travel to Ethiopia due to the potential for civil unrest and arbitrary detention since a state of emergency was imposed in October 2016. The Government of Ethiopia extended the state of emergency on March 15, 2017, and there continue to be reports of unrest, particularly in Gondar and Bahir Dar in Amhara State. This replaces the Travel Warning of December 6, 2016…

The Government of Ethiopia routinely restricts or shuts downs internet, cellular data, and phone services, impeding the U.S. Embassy’s ability to communicate with U.S. citizens in Ethiopia and limiting the Embassy’s ability to provide consular services. Additionally, the Government of Ethiopia does not inform the U.S. Embassy of detentions or arrests of U.S. citizens in Ethiopia… (Emphasis added.)

What exactly does this travel warning mean?

The U.S. issues two types of travel notices. A “travel warning” is issued when U.S. officials recognize the existence of a high risk situation to personal safety and seek to urge U.S. citizens “to consider very carefully whether they should go to a country at all.” Such a warning is issued when there is “unstable government, civil war, ongoing intense crime or violence, or frequent terrorist attacks”; and “remains in place until the situation changes; some have been in effect for years.”

A “Travel Alert” is issued “for short-term events we think you should know about when planning travel to a country”, often because the destination country is experiencing “strikes, demonstrations, disturbances, health issues or  an elevated risk of terrorist attacks.”

On June 13, the U.K. Foreign and Commonwealth Office also issued a travel warning advising its citizens to prepare their own “alternative communication plans when travelling in Ethiopia”. The warning strongly advises against travel to a number of locations in the country, including the “Bole area (in the capital) at night and in more secluded areas, such as the Entoto Hills” because of “incidents of violent assaults”. The warning urges against any travel in the “Amhara”, “Somali”, “Gambella” and other regions.

On June 13, the T-TPLF announced  the launch of its “e-visa service” (electronic travel authorization for international visitors) for travelers to Ethiopia effective June 12, 2017.”  The service is alleged to be “part of a new national initiative to transform the tourism sector in the country.”

How cleverly convenient?! Vintage T-TPLF. They love one-upmanship, trying to stay one step ahead in the game and do an end run to score a touchdown.

Of course, the T-TPLF was notified in advance of the travel warning by the U.S and the U.K. officials. The T-TPLF guys just could not resist the opportunity to stick it in the face of Uncle Sam and John Bull by announcing that visitors can just cyber-walk (cakewalk) their way into Ethiopia, travel warning or no.

There have been previous U.S. travel warnings in Ethiopia.

In December 2016, the State Department issued  a “Travel Alert”, set to expire in February 2017, informing “U.S. citizens of the risks of traveling in certain regions of Ethiopia due to anti-government protests, some of which have involved violence.”

In May 2015, the State Department issued a “Travel Alert”, with an expiration date of June 30, notifying “U.S. citizens residing in or traveling to Ethiopia of the upcoming elections scheduled for May 24, 2015.”

In April 2010, the State Department issued a “Travel Alert”, set to expire in July 2010, informing “U.S. citizens of the risks of travel to Ethiopia before and after national parliamentary elections scheduled for May 23, 2010.”

For the first time, the U.S. issued a “Travel Warning” in June 2017.

Tourism in Ethiopia went to the dogs after the T-TPLF declared a state of emergency in October 2016

According to data cooked  in the kitchens of T-TPLF tourism office, statistical agency and central banks and smoothly massaged and craftily laundered through the World Bank, (I did not say Bankrupt), the International Monetary Fund, tour operators, travel agents and others, Ethiopia has been on a steep trajectory of massive increases in tourism.

2006     330,000                                           2007     358,000
2008     383,000                                           2009    427,000
2010     468,000                                           2011      523,000
2012     597,000                                           2013      681,000
2014     770,000                                           2015      864,000

The T-TPLF allegesEthiopia earned over $5.6 billion from tourism activities in 2016 with over 800, 000 tourists. By November 2016, tourism had dropped by 100,000. Yet, the “Ministry of Culture and Tourism hopes to increase the number of tourists to one million and the revenue to well over $29.8 billion in 2017.”

From $5.6 billion to $29.8 billion in one year! Such a thing can only happen on Planet T-TPLF (nom de terre Thugistan).

Over the past year, tourism in Ethiopia has nosedived.

Estimates vary but tourists are staying away from that country in droves, possibly by the hundreds of thousands. Travel alerts and warnings issued by the State Department are making Americans planning to travel in Ethiopia skittish. There is substantial anecdotal evidence of trip cancellations, changes in travel plans, re-routings to other African destinations and travel postponements by American citizens. Informed American travelers believe it is too dangerous and highly risky to travel to Ethiopia and check out the usual historic tourist spots. To complicate things and make matters even worse, the T-TPLF has turned back upon arrival at Bole airport a number of Ethiopian Americans whom it suspects or believes are its opponents.

The impact of a dried up tourism industry on the local services economy has been devastating.

A story in Addis Standard in March stated that tour businesses were reporting cancellations of “more than 95% of the bookings for the high season.” One tour operator complained, “But there are no tourists now and we can’t even rent the cars to business tourists coming to Addis Abeba. We don’t know what to do. We are just paying rent, maintaining a small staff and hoping for the best at the moment.” most of their clients come from abroad after communicating with them via the internet, guide, says he is now considering a change in career.” The operator added, “Last year at this time, I worked at least 4 days a week. Now getting tourism work has become very difficult. Some of my friends have started working as taxi drivers. At this point, we don’t know what is going to happen next and that is scary.” Many tour guides are also changing professions and looking for other non-tourism related work.

The T-TPLF has sought to drum up tourism by participating in tourism fairs and exhibitions and conducting “workshops” for travel agents and tour operators in Los Angeles, New York, Toronto and other cities. They have also launched tourism web-marketing under the tagline “Land of Origins” in apparent reference to Ethiopia as the “origin of mankind” and of the “Blue Nile”. None of the public relations efforts have worked. Tourists are staying away.

The collapse of tourism appears to have been blamed on the former chief executive officer (CEO) of  “Ethiopian Tourism Organization” (ETO) who has been in office since 2014. According to a recent report in the Ethiopian Observer, the CEO was appointed to “to promote the country’s tourist destinations and to restore the country’s bad image in the western media.” But, “Last year after a wave of anti-government protests in Oromia and Amhara regions, and the government’s move in declaring state of emergency,… the number of foreign tourists visiting the country has fallen by half. The inflow of European tourists fell dramatically due to travel restrictions and sales of travel packages.” Leo Tolstoy observed, “It’s too easy to criticize a man when he’s out of favor, and to make him shoulder the blame for everybody else’s mistakes.”

The decline in tourism has also impacted the availability of foreign currency. Tourism contributes significantly to the country’s foreign currency supply which is used to finance imports (I did not say imports of luxury cars, designer clothes and fancy construction supplies for T-TPLF bosses and cronies). The black market for greenbacks and Euros is said to be sizzling hot. Word on the street is that one U.S. dollars could  fetch up to 31 T-TPLF birr, especially if the conversion amount is over USD$1 thousand.

The IMF says the birr is overvalued, which among other things, makes exports relatively more expensive, dampen domestic demand and increase spending on imports. With declining exports (in 2011, Ethiopia allegedly exported nearly $870 million worth of commodities compared to barely $600 million in 2016), chronic shortages of hard currency, an insatiable demand for imports (imports in Ethiopia increased to $4.2 billion in the third quarter of 2016 and averaged $2.7 billion from 2006 until 2016), widening trade deficit ($3.2 billion in 2016), crushing foreign debt (nearly $40 billion in 2016 representing 54.8 percent of GDP), the Ethiopian economy is spiraling downward as average Ethiopians drown in a morass of a mismanaged economy.

Two weeks ago, “the Auditor General’s latest report” to the “Parliament” “revealed illegitimate transactions close to 20 billion Br in 158 federal institutions during the past fiscal year.

A pariah among nations?

What exactly is the message the U.S. and the U.K. governments are communicating by issuing travel warnings in Ethiopia?

On the surface, a travel warning is just that, but does it signify something deeper about U.S./UK perceptions of the political situation in the country? Is there a hidden message buried in the warnings?

Reading between the lines, there is little question that the U.S. and U.K. governments have concluded there will be no end to the political turmoil in Ethiopia which remains barely contained by a state of emergency decree which authorizes illegal mass arrests and incarcerations and use of live fire on protests including peaceful ones. It is clear to both the U.S. and the U.K. that T-TPLF has no legitimacy whatsoever in the eyes of the vast majority of the Ethiopian population. They know the T-TPLF is sitting atop an ethnic powder keg connected to a slow burning fuse fast approaching the loaded barrel. The T-TPLF barely hangs on to power because it has minimal control over the military. However, the military is highly fragmented along ethnic lines. Nearly all of the military brass are ethnically affiliated with T-TPLF regime leaders. The vast majority of the rank and file are members of other ethnic groups.

The U.S. warning speaks about the “unpredictability” and state of “unrest” “particularly in Gondar and Bahir Dar in Amhara State”. The U.K. warning concurs. That fact is corroborated by substantial anecdotal evidence of individuals who have visited those areas in the recent past.  The areas mentioned in “Amhara State” are now self-administering. There is little doubt that the T-TPLF has lost complete political and military control in a number of areas throughout the country. Just a few days ago, the T-TPLF sent a contingent of troops to suppress resistance in the Arba Minch and Gamu Gofa areas some 500 km south of the Ethiopian capital.

The U.S. perceives a direct relationship between the “state of emergency and the unpredictable security situation” in Ethiopia in urging its citizens to avoid travel to Ethiopia. The U.S. understands that the T-TPLF would not have resorted to a “state of emergency” unless it believed it was facing a clear and imminent existential threat. There is little question that there currently exists a vast groundswell of opposition to T-TPLF rule. The T-TPLF claims “protests and demonstrations” against its rule are limited to a few isolated areas remotely managed by overseas opposition groups. That is inconsistent with the fact that the T-TPLF issued a nationwide state of emergency. For the T-TPLF to impose a nationwide state of emergency decree, it must necessarily believe there is broad and deep  resistance to its tyrannical rule throughout the nation.

The U.S. is manifestly disapproving of the means the T-TPLF is using to impose its will on the vast majority of the Ethiopian population and its excessive and indiscriminate use of violence on peaceful protesters. The U.S. is communicating its disapproval in its advisory language underscoring the fact that there is “widespread arbitrary arrests and detentions throughout the country” and the intentional failure of the T-TPLF to “notify the U.S. Embassy of detentions or arrests of U.S. citizens in Ethiopia.”

The U.S. expects notification of arrest of its citizens abroad within 24-72 hours. But the T-TPLF does not honor such diplomatic courtesy. There was a time when such reporting was required (Treaty of Amity and Economic Relations between the United States of America and Ethiopia, Sept. 7, 1951, art. 6(2) (entered into force Oct. 8, 1953). Art. 36 of the Vienna Convention on Consular Relations (1963) also provides for consular communication and contact with nationals of a foreign state when arrested in the host country.

Of course, legal obligations mean nothing to the T-TPLF ignoramuses who have absolutely no regard for the rule of constitutional and international law. As I have often remarked, preaching the rule of (international) law to the T-TPLF is like sermonizing  Scripture to Heathen or pouring water over a slab of granite. It is a complete and total exercise in futility!!!

The U.S. Congress is righteously indignant about the T-TPLF’s “use of force and live fire in response to demonstrations” and on “peaceful gatherings”. In February, Representative Christopher Smith introduced H.R. 128 condemning the use of excessive violence and to “support respect for human rights and encourage inclusive governance” in Ethiopia. In May, Senators Ben Cardin (D-Md.) and Marco Rubio (R-Fla.) introduced S.R. 168, co-sponsored by 14 senators, which mirrors the House version. I discussed these bills in my May 29 op-ed piece in The Hill.

The T-TPLF’s “disruptions” of communication throughout the country by “routinely restricting or shutting down internet, cellular data, and phone services” are a sore point for the U.S. and the U.K. In its annual human rights report for 2016, the State department expressed its disapproval of the “Ethiopian government’s shut down of mobile access to the internet, wired access to several social media and communication sites including Facebook, Twitter, Instagram, YouTube, Skype, WhatsApp, and Viber, news websites such as the Washington Post and the New York Times, and many other sites, including foreign university homepages and online shopping sites such as Amazon.”

My informed conclusion is that it is highly unlikely that the T-TPLF will make a monkey out of the Trump Administration. I cannot imagine the T-TPLF wrapping the Trump Administration around its little fingers as they did the Obama Administration.

I do not doubt that the T-TPLF leaders believe they are so crafty and clever that they could outfox, outmaneuver and outsmart Trump and his administration any day of the week. Why else would they take hire a $2 million dollars from the mouths of starving Ethiopian babies and feed the voracious appetite of a Washington lobby firm in January unless they believed they can make a patsy of the Trump Administration?

I believe the Trump Administration has given some consideration to the points I raised in my letter to Trump dated February 3, 2017 and other follow-up communications.

President Trump is the object of savage criticism for his “America First” foreign policy”. During the presidential campaign, I was one of his harshest critics on a variety of issues. On the issue of human rights and cuts in U.S. aid to dictatorships, I agree with him completely.

As I defended U.S. Ambassador to the U.N. Nikki Haley in my op-ed piece in The Hill last week,  the Trump Administration is right in its decision (yet to be implemented) to quit the U.N. Human Rights Council than be part of an organization that is run by the some of the world’s notorious human rights violators, including Ethiopia. Haley was absolutely right when she declared, “Being a member of this council is a privilege, and no country who is a human rights violator should be allowed a seat at the table.” Haley had the courage to stand up and tell dictators to shape up or ship out.

I am so glad that Nikki Haley is no Susan Rice, Obama’s Ambassador to the U.N. In  2012, Rice canonized  the late Meles Zenawi, the ruthless and bloodthirsty genocider, as “brilliant and a son of Ethiopia and a father to its rebirth.”

Rice has never been able to tell the difference between the death and rebirth of a nation in Ethiopia, Rwanda or anywhere else. There has never been a murderous African dictator Susan Rice did not madly love.

The question is “not to be or not to be”. The question is who is on the wrong side of history on the issue of human rights? Obama or Trump?!

Trump’s “America First” foreign policy is “focused on American interests and American national security”, not about the feeding and care of savage African dictators or making excuses for the mess they have created. It is about “withdrawing” from messy entanglements that cost the American taxpayer billions of dollars. It is about accountability and not giving handouts and free money to African dictators who stash it in their offshore accounts.

The Obama Administration prolonged the political life of the T-TPLF with infusion of massive amounts of American tax dollars. It is unlikely that Trump will dump hard-earned American tax dollars to prop up a bloodthirsty thugtatorship; and will certainly not buy the “terrorism partnership” scam of the T-TPLF.

I believe the Trump Administration has concluded that things in Ethiopia have gone beyond a point of no return when the T-TPLF renewed its state of emergency in March. No doubt, the T-TPLF will continue to renew its emergency decree until it is removed from power.

When that time comes, que sera, sera (“what will be, will be”)!

posted by Gheremew Araghaw

Ethiopia running out of food aid money, magnifying regional threat

BY ON 15 JUNE 2017humanosphere

Food aid for millions of Ethiopians will run out by the end of June, according to the United Nations.

The UN says if nothing is done, the country’s food crisis could expand and destabilize a region with two neighboring countries already facing famine.

The Ethiopian government has spent $381 million In the past three years to help its citizens deal with the effects of the ongoing drought. This indicates the government can and does respond to domestic problems, but some say it may not have enough money and resources to keep up with the current crisis. Ethiopia’s government says it needs more than $1 billion in emergency assistance.

An estimated 8 million Ethiopian people are in need of food assistance due to drought and crop failures, the U.N.’s World Food Program says, and are at risk of losing a vital lifeline. The Ethiopian government disputes the WFP claim, saying that fewer people are in need and that it is up to the challenge.

“It’s true that in some areas food will run out by the end of the month but this will only affect around 1.7 million people,” Ethiopia’s commissioner for disaster risk management Mitiku Kassa said to the press.

“We expect the donor community to step in to fill that gap and we are hopeful. But if they fail to do that, we will have to use some of our development budget to provide emergency assistance to our people.”

The difference in scale matters because some say the country may need more foreign assistance than it is requesting. The Ethiopian government has been alleged to have covered up crises before. Humanitarian groups are right now responding to a cholera outbreak that the government claims is just acute watery diarrhea.

RELATED  Human rights deteriorating as authoritarianism rises in Eastern Africa, report says

But the dispute is not just the main problem. The fact that Ethiopia needs more foreign assistance adds stress to an already underfunded regional hunger crisis in East Africa.

WFP spokesperson John Aylieff warned the country is in a “dire situation.” Ethiopia is under increased pressure due to hosting some 730,000 refugees who have fled conflict and crisis in their nations. Poor rainfall need for agriculture, an overstretched government, the spread of the crop-destroying fall army worm and an inflow of refugees have all amplified the problem.

As a result, the number of people in need of food aid rose by 2 million within just two months. The situation in Ethiopia is critical because it “plays a major role in terms of regional stability” according to an official with the U.N. Development Program.

Millions of people in the Horn of Africa are today at risk of dying from starvation, warns the U.N.

Parts of South Sudan already experience famine, a declaration that comes after people start dying, and there are concerns Somalia will soon follow. South Sudan’s famine affects more than 100,000 people and up to 5 million are at risk of starvation. Continued fighting makes it difficult for aid groups to help people in need and for farmers to resume planting crops as the rain returns.

RELATED  Myanmar: Damning reports of Rohingya women, children raped and slaughtered

Ethiopia is frequently held up as a development success story. A 1984 drought and famine that left more than 400,000 people dead ended up galvanizing the international community, most notably with a Live Aid concert that kicked off the decades-long use of celebrities to raise money for humanitarian causes.

The country’s economy improved in the ensuing decades, helping it avert famine during the drought in 2010 that killed more than 260,000 people in neighboring Somalia.

Somalia and South Sudan lack the capability to provide the kind of support the Ethiopian government can deliver. It leaves millions of people dependent on international humanitarian support. The humanitarian appeals for both countries are not fully funded – as is often the case for emergency situations.

“Although the impressive efforts from communities, governments and international actors have so far managed to prevent the current drought escalating to famine, we are still in the midst of a major life-saving intervention and there is need for sustained funding and international support to mitigate what could still deteriorate,” Jeffrey Labovitz, the regional director for the International Organization on Migration, said.

“In the coming months, we are likely to see many more needing humanitarian aid and being displaced, due to the poor rains.”

The fact that Kenya and Ethiopia are able to help themselves takes off some of the financial pressure on the regional response. However, that appears to be changing.

posted by Gheremew Araghaw

የዘፈንና ሙዚቃ ኮታችን እንኳን አይጠበቅልንም? – ምሕረት ዘገዬ

ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

ይህ በዓል የማን እንደሆነ አሁን ገና በደምብ ገባኝ! “ኢሕአዲግ” የሚባለው የሕወሓት መሀል-አገራዊ የሠርክ መጠሪያም የለየለት ቅጥፈት መሆኑን በዛሬዋ አጋጣሚ ይበልጥ ተገነዘብኩ።

አለቃየ አንድ አጣዳፊ ሥራ አዞኝ ከጧት ጀምሬ የተደፋሁ አሁን ድረስ አለሁ –  ከቀኑ 11 ሰዓት፣ ዛሬ ግንቦት 22 ዕለተ ቅ. ዑራኤል 2009ዓ.ም ነው። ፍሪጅ ውስጥ ገብቶ እየተከበረ ያለው የግምቦት 20 የወያኔ በዓል በየቦታው ፊሪዳ እየተጣለ አንጨብጫቢዎቹንና አባላቱን ሆዳቸውን በሥጋና በአልኮል እየቀበተተ አሁን ድረስ ቀጥሏል፤ ከዘረፋና ከሰሜናዊ አቅጣጫ ጉዞ የተረፈው የሀገር ሀብት በነቀዝ የወያኔ አጋፋሪዎችና ጀሌዎች እየረተመልህ ነው ወገኔ። ይህን ማስታወሻ የምጽፍላችሁ በቅርቤ በዚህች ቅጽበት እየተከበረ ከሚገኝ የግንቦት 20 በዓል ላይ ተመርኩዤ ነው። ዘፈኑ እንደጉድ ይቀልጣል፤ ጩኸቱም እንደጅራፍ ይኖጋል። እውነትም ሶዶምና ገሞራ አዲስ አበባ ገብታለች ያስብላል፤ ሚሊዮኖች የሚልሱትን የሚቀምሱትን አጥተው በርሀብ አለንጋ ይገረፋሉ – እዚህ መቀሌ ላይ – ማለቴ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ በጮቤ ረገጣ ዓለም ታልፋለች፤ በጭቁኖች ገንዘብ ዳንኪራ ይረገጣል – ምን ለማምጣት? ብለህ ጠይቅ – መናገር ሳያስፈልግ ዕድሜ ከሰጠን  በቅርቡ አብረን የምናየው ይሆናል። ይህ ጥጋብ እነዚህን ተምቾችና አልቅቶች በቁም ሲዖል ካላወረደ ምላሴ ጥቁር አይደለም ማለት ነው። ለነገሩ ለዚህ አልተነሳሁምና….። አሃ! ሃሜታየን በብዕር እየከተብኩ መሆኔን በቴሌፓዚ የርቀት መገናኛ ተረዱ መሰለኝ ገና አሁን የይሁኔ በላይን “ነይማ ነይማ” የሚለውን ከፈቱ።…

ለዘፈን ግድ ኖሮኝ አይደለም። የማንም ይከፈት አይከፈት ግድ አይሰጠኝም፤ ጊዜውም ሆነ አጠቃላይ ዘመኑ የጸሎት፣ የምህላና የዋይታ እንጂ የዘፈንና የዳንኪራ እንዳልሆነ ጠንቅቄ የማውቅ ዜጋ ነኝ። ዕድሜየም ልምዴና ተሞክሮየም በተለይ በአሁኑ ሰዓት ለዘፈን ተጨናቂ እንድሆን አያደርጉኝም። ትዝብቴን  ለመተንፈስ ብቻ ነው። እንጂ ከስቃይ በስተቀር ጥጋብን የማይችሉት ወያኔዎች ሀገርን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ሌሊት ሌሊት ሆስፒታል አይሉ ትምህርት ቤት፣ ሠፈር ውስጥ አይሉ የአምልኮት ሥፍራ ለመዝናናትም ሆነ ለመረበሽ ምቹ በሆነው የጋራ የትግርኛ ምታችን (rythm) በአሥረሽ ምቺው ሀገር ምድሩን እንደሚረብሹ ማንም ያውቃል፤ “ችለናቸውማል”። “ወደሽን ቆማጢት” አሉ?… ሆ! ኧረ ማን ነው በማን ግዛት ተቆጭ ገልማጩ?

በአጠገቤ የሚካሄደው የወያኔ በዓል የተጀመረው ምሣ ሰዓት አካባቢ ነው። ከዚያን ሰዓት ጀምሮ የሚከፈተው ዘፈን ከ90 በመቶው በላይ ትግርኛ ነው – ሆን ብዬ እየተከታተልኩና በግብዝነታቸውም በሣቅ እየተንፈረፈርኩ ስለነበር የምለው ነገር እውነት ነው – ኩነኔውን ለኔ ጥላችሁ እንደ አንደኛ ደረጃ እውነት ውሰዱት ከፈለጋችሁ። … አሁን ደግሞ ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ አላውቅም “እምበር ተጋዳላይ” እየተዘፈነ ነው። የቀጥታ ሥርጭት ላይ ነው ያለሁት – በጽሑፍ። ዛራቸው ተነስቶ እየደለቁ ነው። ድንኳኑ የጠበባቸው ይመስላል። አጠገቤ ደግሞ አንድ የቢሮ ተጋሪ የቴዲን “ኢትዮጵያ” ከፈተብኝ። በ”እምበር ተጋዳላይ”ና በ“ኢትዮጵያ” መሀል እየተረበሽኩ ነው የምጽፍላችሁ። ለነገሩ ስበጠበጥ የኖርኩትና ብርቅዬውን ዕድሜየን ያገባደድኩትም በነዚህ የሳይቤሪያና የካልሃሪ ዓይነት ኑባሬያት ነው። መሀል ላይመጡ እኛን እንዳራራቁና እንዳፋጁ ይኖራሉ።

አልፎ አልፎ – ምናልባት ከአንድ ሰዓት በኋላ አንድ የጉራግኛ ወይም የኦሮምኛ ዘፈን ለማስመሰል ይመስለኛል ጣል ያደርጋሉ – የአማርኛ ዘፈን ሃሊዮት ኮሜት ሆናለች፤ ከስንት አንዴ አንዲት ውዳቂ ዘፈን –  ከፖለቲካዊ አንድምታዋ አንጻር ተመርጣ – ታሽታና ተፈትላ ትቀርብና ለአፍታ ትዘፈናለች – ያኔ ታዲያ ቱባዎቹ ወያኔዎች ግምባራቸውን እንዴት እንደሚኮሰኩሱት ይታየኛል – አምሃርኛን በመጠየፍ ስሜት። ያ የከፈቱት የሌላ ጎሣ ዘፈን በቅጡ ሳይጠናቀቅ ወዲያውኑ ትግርኛውን ይለጥቃሉ። በዚህች ተራ ነገር፣ በየቤታቸው ከፍተው ሊዘሉበትና ሊፈርጡበት በሚችሉበት ትንሽ ነገር እንኳን ትዝብትን አይፈሩም፤ ሀፍረትም በጭራሽ አይሰማቸውም። ዳንኪራው ላይ እንኳን በዚህን አጋጣሚ እንድንጨፍር የምንችለውን ዘፈን በጋራ መናገሻ ከተማችን ውስጥ ቢከፍቱልንስ? ማለቴ ለጋበዟቸው ሰዎች ቢከፍቱላቸውስ? ትግሬዎች በሚበዙበት ቦታ ደግሞ ትግርኛ ብቻ ይሁን። በዚህም በደል?… በየትምህርት ቤቱ ሚኒ ሚዲያ ሳይቀር ግዳጅ የተጣለባቸው ይመስል ሁሉም የሚደልቀው በአብዛኛው ትግርኛ ነው – ሰርኩላር ተላልፎ ይሆን እንዴ ግን? የወያኔ ነገር ምን ይታወቃል! የየሆቴልና የምሽት ክበቡንማ ተውት (ሰዎች እንደሚነግሩኝ ነው ታዲያ – የት አየህ እዳትሉኝ)። ሰዎች ደግሞ የጭፈራ ሥልቱን እንኳን በቅጡ ሳያውቁት ለማስመሰልና ውዳሤ ከንቱን ለማትረፍ በየዳንስ ቤቱና በየድግሱ በትግርኛ ዘፈን ወንከር ወንከር ይላሉ። በሠርጎችማ ትግርኛን ያላዘፈነ ሠርጉ በወያኔ ፌዴራል ይበተናል የተባለ ይመስል አብዛኛው ዲጄ በአማራና ኦሮሞ ሠርግ ሣይቀር ካለትግርኛ አይከፍትም – ይቅርታ – መከፈቱ አይደለም የኔ ችግር – ለማስመሰልና አጉል ተወዳጅነትን ለማግኘት የሚደረገው ሩጫ ነው የሚያስገርመኝ። ባጭሩ ሀገራችን በአስመሳዮችና በሆዳሞች ተሞልታለች። አፉና ልቡ የሚለያየው ዜጋ በዝቷል።ትግሬነት ደግሞ በምኞትም ሆነ በስለት አይገኝም።

እርግጥ ነው አዲስ አበባ መቀሌን እንደምትመስል ሳይሆን አሁን አሁን መቀሌን እንደሆነች መገንዘብ አያዳግትም፤ አብዛኛው ደህና ነዋሪ ትግራዋይ ነው። አብዛኛው ዘመናዊ ተሸከርካሪ የትግሬ ነው። አብዛኛው ሕንፃና የንግድ ተቋም የትግሬ ነው። በርግጥም በዚህ ዘመን ትግሬ መሆን እጅግ ያስቀናል። ህግን መሬት ላይ እያንደባለለ የሚረጋግጥ ሰው ብታይ ባለህ ተወራረድ – ያ ሰው ትግሬ ነው።  ትግሬ ሆንክ ማለት ኢትዮጵያን የግል ንብረትህ ለማድረግ ትልቅ ሊቼንሳ ነው ባጭሩ። ብዙው ትግሬ የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ብቻ ሣይሆን ተራ ዜጎችን – እኛን – ሳይቀር በባለቤትነት የያዘና እንዳሻው የሚያደርግ ይመስለዋል፤ የንግግሩ ቃናና አድራጎቱ ሁሉ ሲታይ ከዚህ ስሜት የመነጨና በአልጠግባይነት ሥጋዊ ፍትወትም የተቃኘ ነው። ወያኔ ሲጠግብና ሥልጣን ሲይዝ ምን ተዓምር ሊያሳይ እንደሚችል እንግዲህ ላለፉት 26 ዓመታት አየን። እውነትህን ነው ቴዴ “እጄን አላነሳም እኔስ ከቀሚሷ፤ እናት እኮ ነች ተስፋ አልቆርጥም በርሷ” ይላል አጠገቤ የተከፈተው ቴዲ። የወያኔዎች ጥጋብ ግን ሁልጊዜ ይገርመኛል። ዕድሜ ሲጨምር እየሰከነ ሳይሆን እያሸተና እየጎመራ የሚሄድ ልዩ ጥጋብና ዕብሪት።

ልብ አድርጉ! አዲስ አበባ ውስጥ መቼም በተጋባዥነትም ይሁን በሠራተኝነት ከትግሬ ቁጥር እምብዝም የማይተናነስ የሌላ ብሔርና ዘውግ ተወላጅ አይጠፋም። ለነሱ ግን ሁሉም ትግሬ ነው የሚመስላቸው። የጠገበ ሰው ሁሉም ሰው የጠገበ እንደሚመስለው።

አንድ ጨዋታ ልንገራችሁና ወደሥራየ ልግባ፤ ከኔ የትውልድ ቀየ ከቅምብቢት አንድ ልጅ ዐይኑን ይታመምና አዲስ አበባ ለህክምና ይመጣል። ዶክተሩ የልጁን ዐይኖች አወጣና አጸዳድቶ ሊያስገባ ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀመጣቸው ዕቃ ለማምጣት ዘወር ሲል የሆስፒታሉ ድመት እነዚያን ዐይኖች ቅርጥፍ አድርጎ ይበላቸዋል። ዶክተሩ ይናደዳል። የሚያደርገው ቢጠፋው የድመቱን ዐይኖች ያወጣና ለልጁ ገጥሞ ከአንድ ወር በኋላ ለ”ቼክአፕ” እንዲመለስ በማዘዝ ወደመጣበት ያሰናብተዋል።

ልጁ ቅምብቢት ይመጣል። አትታዘቡኝና እኔም ነበርኩ። ዘመድ አዝማድ ተሰብስበን “እሰይ! ድፋባቸው የኛ ልጅ!  በደምብ ታክመህ መጣህ አይደል?…” እያልን ከብበን እንጠይቀው ያዝን። ከዚያም እኔ እሆን ሌላ ሰው  – ጊዜው ራቀና ዘነጋሁት – “ለመሆኑ እዚህ አካባቢ እነማንና እነማን እንታይሃለን” ብለን ስንጠይቀው ዐይኖቹን እያጉረጠረጠ “ድመት! የሚታየኝ ሁሉ ድመት ነው!” አይል መሰላችሁ? ሁላችንም ደነገጥን። የሆነ የውስጥ አካሉን አበላሽተውበት ከሰውነት ተራም እንዳወጡት ገመትን።

አዎ፣ ወያኔዎች የሚታያቸው አንድ ነገር ብቻ ነው – ያም ትግሬና ትግሬነት ብቻ። ከመነሻው አባታቸው ሰይጣን የገጠመላቸው ሶፍትዌር ትግራይነትና ትግሬነትን ብቻ ነው – የአፍሪካ ቀንድ ጽዮናዊነት፤  እጅግ አደገኛ ዘረመላዊ ደዌ – ካላስቀበረ የማይለቅ የዘረኝነት ልክፍት። ከዚህ እልፍ ሊሉ አይችሉም – ቢያልፉ ደግሞ እውነታቸውንም ነው መዘዙ suicide የመፈጸም ያህል ነው – በየትኛው ምልዓታቸውና ደግ ሥራቸው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተወዳድረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ይታያችሁ። እናም ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በጀመሩት የሊቀ ሣጥናኤል ሰፊ መንገድ ተጉዘው የቀረቻቸውን አጭር ግን አሣር የበዛባት ዕድሜ መጨረስ ነው – የሚያሳዝነው አመክሮና የፍርድ አስተያየት በሌለው ሁኔታ ስንብታቸው እስከወዲያኛው መሆኑ ነው – የሠሩት ሥራ ሰማይና ምድር ሊታገሱት ከሚችሉት በላይ ግዙፍ ነውና የሚወርድባቸውም ታሪክ የሚያውቀው ተራ ቅጣት ሳይሆን የክቱ ስሑል ነበልባላዊ  መቅሰፍት  እንደሚሆን የታሪክን ድርሣናት ባያነብም ተንተርሶ የተኛ በቀላሉ ይረዳዋል – ባይገርማችሁ እነሱም ጭምር! በበኩሌ እኔ በሚገባ አውቃለሁ፤ የተሰወጠችብኝ (የተሰወረችብኝ) የጊዜዋ ነገር ናት። …

ኢንተርኔት በመዘጋቱ ዛሬ መላክ አልቻልኩም። በሁሉም አቅጣጫ ዘጋግተው እንደሰሜን ኮሪያ ሕዝብ ትልቅ በረት ውስጥ አጉረው ያሰቃዩናል። … እንደሰማሁት በ10ኛና 12ኛ ክፍሎች ብሔራዊ ፈተና ምክንያት ኢንተርኔት ተዘግቷል አሉ። ከዓለም የምንገናኘው ከሣምንት በኋላ መሆኑ ነው – ያውም ያኔም ከለቀቁልን። እንዲህ እየተሆነ አገርን መምራት የትም ታይቶ አያውቅም። ጋጣ ውስጥ የታሰርኩ በግ ወይ ፍየል የሆንኩ ያህል ይሰማኛል። በውጭ ሀገር ያለ እንዴት የታደለ ነው! (ከነችግሩም ቢሆን)።

posted by Gheremew Araghaw

 0  212  212

ወያኔ በውጭ ሃገር ያሰማራቸው ሰራዊቱ – ከሙሉቀን ገበያው

ሕወሃት (ወያኔ) ኢትዮጲያን ከተቆጣጠርበት ከ 1983 (እንደ አውርፓውያን አቆጣጠር 1991) ጀምሮ ልዩ በሆነው ያገዛዝ ዘዴው ተጠቅሞ እየፈለጠና እየቆረጠ ለ26 አመታት ዘልቋል። ይህ የጥቂቶች ጅምር የሆነው መሰሪ ድርጅት ከ 1967 ጀምሮ፤ በዘረኝንት መንፈስ ተጠምቆ፣ በጸረ-አማራ ጥላቻና ቅናት ስሜት ተወልዶ፣ በኤርትራ ገንጣይ ወንድሞቹ ታግዞ  ጎርመሰና በብልጣብልጥ መሪዎቹ እየተመራ ላልገመተው ነገር ግን ለሚያልመው ድል በቃ።

የደርግ መንግስት ወታደራዊ አገዛዝ ያስመረረው ህዝብና  ተፈጥሮ ና ሰው-ሰራሽ የረሃብ አደጋ ያጎሳቀለው አገር  ተጨምሮ ለወያኔ ድል ማደርግ መንገዱን አመቻቸለት። በ1977 አመተ ምህረት በትግራይና ሰሜን ኢትዮጵያ በረሃብ ለሚረግፉ ወገኖች ህይወት ማዳኛ  ከነ ቦብ ጌልዶፍ በልመና የተገኘውና ለወያኔ የተሰጠውን 100 ሚሊዮን ፓወንድ ( በዛሬ ዘመን እጅግ ትልቅ ገንዝብ) ለጦር መሳሪያና የወያኔን ደርጅት ማስፋፍያነት ተጠቀሞበት ከተራ ሽፍታ ጦር መሆን ተለወጦ፤ በአካባቢው ባሉ አገራት ሱዳን፣ሶማሌና የአረብ አገራት እርዳታ ቦኋላም በአሜሪካ ከፍተኛ እርዳታ ተጨምሮ ብዙ አስርት አምታት ታግሎ ሻቢያ እንኳን ያላገኘውን ድል ወያኔ ያለ ብዙ ድካምና እንቅፋት አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ቻለ።

የወያኔ መሪዎች መሰሪ፣ ነገር ግን ብልህነት የሞላቸው ስለነበሩ ያልጠበቁትን ትልቅ ድል በቀላሉ ላልመነጠቅ ትልቅ ስራ ሰርተዋል። ምናልባትም ከደርግ ወይም ሻቢያ በተለየ  የአገዛዝ ዘዴያቸውን በደንብ ያጠኑ ሁነው ተገኘተዋል። በዚህም መሰረት ጥቂት ሁነው 6% (የትግራይ ህዝብን ሁሉ አይወክሉም ነግር ግን ደጀኔ ነው ብለው ያምናሉ) አብዛኛውን  94% ኢትዮጲያውያንን ለመግዛት የሚያስችል ስልት መንደፍ ነበርባቸው። ተንኮልኞቹ መሪዎቻቸው ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጲያን ስትወር የተጠቀመችበትን ‘በጎሳና በሃይማኖት ለያይተህ ግዛ’የሚለውን መመርያ ከልብ በማመን ከስታሊንና ማኦ  ( ኮሚኒስቶች ነን ባዮች)  መጽሃፍት ስለ ብሄር ብሄረሰቦች የተተነተነውን በወል እንኳን ሳይሆን ቀድተው፤ ላገዛዛቸው እንዲያመቻቸው በ’ከፋፍልህ ግዛው’ ዘዴ ጥቂቶቹ ብዙሃኑን እንደልባቸው ለ26 አመታት በቀላሉ እንዲገዙ አስችሏቸውል።

ወያኔ እንደ እስስት ቆዳ በሚለዋወጥ ባህሪው ፈራንጆቹንም አደናግሮ፤ የነሱንም ጥቅም አስከባሪ ሆኖ፣  የነሱን እሺታ ከሚፈልጉ ድርጅቶች ጨምሮ  በብዙ  ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ና እርዳታ የፈጠርው መንግስታዊ እንዲሁም ወታደሪዊ አቅም ገንብቶአል። መሪዎቹ በሚያስደነቅ ሁኔታ ፈረንጆቹን ሲያታልሉ፤ በፈረንጅ አፍ (እንግሊዘኛ) ስለዲሞክራሲ ግንባታና የእድገት ሲለፍፉና ሲያሳምኗቸው፤ በዚያኑ ያህል  ደሞ  ለኛ ባገራቸን በሚገባን ቋንቋ (አማርኛ) ሲያስፈራሩና ሲቆጡን ኖረዋል። ይሄ ጸሃፊ የሚያስታወሰውን እዚህ ለምስክረነት መስጠት ይፈልጋል።

ታዋቂውን የእንግሊዝ ጋዜጠኛ ጆናታን ዲንቢልቢ ከቀዶምው የወያኔ መሪ መልስ ዜናው ጋ ተገናኛቶ  አቶ መልስ እንዴት አድርጎ “እንደ ሸወደው” ማወቅ ያስደንቃል። አቶ መለስ “የኔ ልፋትና ትግል ውጤት የሚለካውና የምርካብት እኔን እራሴን በዘርጋሁት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስሸነፍና ስልጣን ስለቅ ነው” ብሎት ጆናታን ዲቢልቢልን ሲያሰድንቀውና  “እንደዚ ያለ ታላቅ አፍሪካዊ መሪ አይቼ ሰምቼም አለወቅም” ብሎ ለአቶ መለስና ደርጅቱ ትልቅ ከበሬታ ሰጥቶ ነበር። ሁላችንም እንድምናወቀው ግን  1997 ምርጫ ና የአቶ መለስ እርምጃ እንዴት እንደነበር የምናወቀው ነው። ፈረንጆቹን የማታለል ዘዴ ወያኔ ተክኖበታል።  ምርጫ በየግዜው ማድርግ፣ ተከሳሽን ወደ “ነጻ ፍርድ ቤት” መወስድ፣ አስምሳይ ተቃዋሚ ጋዜጦችን ወይም ሬድዮኖችን መፈቀድ  የመሳስሉት ፈርንጆችን ያስታል። የውሽት ምርጫ መሆኑን፤ ፈራጁም ዳኛ የወያኔን ፍርድ አስፍጻሚ መሆኑን፣  ሚዲያውም በወያኔ መዳፍ ስር መውደቁን ግን አያወቁም።

ወደ ወያኔ አገዛዝ ዘዴ ስንመለስ በጎሳና በክልል ኢትዮጲያውያንን አጥሮ፣ አንዱን ባንዱ ላይ በጠላትነት አስተሳስሮ፣ ታላላቆቹን ነገዶችና ሃይማኖቶች  አተራምሶ፡  ራሱ ወያኔ ዳኛ፣ ፈራጅ፣ ጠብቃ፣ ፖሊስ ሆኖ ብዙዎችን አታሎ አሳምኖ አሁን ድርስ በሀይለኛነት ይገዛናል።

ወያኔ ትንሽ የለውጥ ምጥ በመጣበት ቁጥሩ ራሱን ቀለም እየቀባና እያሰምሰለ ከርሞል። ከማርክሲስት ሌኒንስት ርዮት አለም  ወደ አብዮታዊ ዲሞክራሳዊ መዝሙር፤ ከዚያም በቦናፓርቲዝም ዘፈን ወደ ልማታዊ መንግስትነት እያሰመሰለ ፈረንጆቹንም፣ የኛዎቹን የውኋችን እያታለለ ቆይቷል። መሰረታዊ ባህሪይው (ለአማራ ብሄር ያለው ጥላቻና ‘አከርካሪውን’ መስበር ድርጊት፣ የትግራይ በኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ የበላይነትን ማስቀጠል፤ ወያኔ፡ ሃገር እስከገዛ ድርስ በኢትዮጲያ ስር ለሞቆየት፤ ነገር ግን ወያኔ የማይግዛ ከሆነ የትግራይ ሪፐፕሊክን ከኢትዮጲያ ሀብት በተዘረፈ ንብረትና መሬት መምስርት) ግን የማይለውጥ የወያኔ ቃል ኪዳን ነው።

ወያኔ በፕላን ባቀደው መሰረት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ በትልቅ እጅ በመንግስትነትና በኤፈርት በሚባለው ዘራፊ ‘የልማት” ደርጅቱ ሲቆጣጠርው (እባኮውን የቀድሞው ሚንስቴር-ዴታ የነበረውን የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ልቃቂት” በእወንተኛ ማስርጃ የተሞላ መጽሃፍ ያንብቡ)፤ በወታደራዊና በደህንነት  መድሩኩ በኩል ደግሞ ፡ ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ (ከትንሽ ሌላ ጎሳ ተወላጅ፤ ታማኝ ሰዎች በቀር) ተቆጣጥሮታል።             በፖለቲካውም መድረክ የያንዳንዱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አድርጋና ፈጣሪ ወያኔዎች ሲሆኑ ለስሙ ፊት ለፊት የሚቀመጡ የሌሎች ጎሳ ተወላጅ ታማኝ አገልጋዮችን አሰቀምጠዋል። ክልል ብለው በከለሉት የሚግኙት ትናንሽ መንግስታት ከወያኔ ፈቃድ ወጪ አንዲት ወሳኔ የማይወስኑ፤ ከ ዘፈን ውጪ ሌላ የማይፈቀድልቸው፣ የወያኔን ውስኔ የሚያስፈጽሙ ሁነው ተገኘተውል።

በሀገር ቤት የወያኔን ተንኮልና አጥፊ አገዛዝ የተረዱ ደፋር ኢትዮጲያወያን ወገኖች በግል ና በመደራጀት የሚያደርጉትን ትግል፡ ወያኔ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ሲያጠፋ ይታያል። ለይስሙላ ያስቀመጠወን ህገ-መንግስት፡ መጀመርያ አፍርሽ የሆነው ራሱ ወያኔው ነው።  ደረቁ ደርግ “አታድርግ፤ ካደርክ ግን እቀጣሃለው”የሚለወን ፊት ለፊት የሚታይ አሰፈሪ ህግ፤ ዘዴኛው ወያኔ ፈርንጆች ወዳጆቹን የሚያታልልበት ዘዴው        “እንድ ልብህ አድርግ፡ ተፈቅዶልሃል፤ ግን ከኔ ቅጣት አታመልጥም” በሚለው ቀይሮ ተግብሮታል።

ጋዚጠኞችን፤ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችን፣ ሃገር ወዳድ ባለሞያዎችን፣ ሙሁራኖችንና የኪነ ጥበብ አዋቂዎችን እያሳደደ፤እያስፈራራ፤ ስም እያጠፋ፣እያሰረ፤ሲያስፈለግም እየገደለ አገዛዙን ቀጥሎአል። የውሽት ተቃዋሚ ድርጅት እየመሰርተ፤ ዲሞክራቲክ መድርክ ያለ እያስመሰለ፣ ሰላዮቹን እየገጠገጠ፡ ምርጫ ቦርዱን መደነሻ ቤት አድርጎታል።

ግፍና መከራ የበዛበትን ህዝብ ለለውጥ እንዳይነሳ ባስፈሪ የስለላ መዋቅሩ ጠላለፎ፡ ህዝቡ እንዲፈራራና እንዳይተማመን፣እንዳይነጋግር አድርጎት፤ በተለይ ገንዘብና ዳቦ ጥቅማ ጥቅም በሚወዱ ደካሞች  በወገኖቻቸው ላይ ሰላይና ጠቋሚ አደርጎ ቆልፎ ይዞታል። ለሰላሚው ትግል የተነሱ ወጣቶችን አስቀድሞ በማፈን፣ ከትምህርት፣ ከስራ በማባረር ካአገር እንዲሰደዱና ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያስደርገ፤ ሰባዊነት የጎደለው ግርፋትና ስቃዩ ፤ ጨካኝነትና አውሬ ባህሪው ሌላው የአገዛዝ ስልቱ ነው።

ወያኔ የእግር ቁስል ሆነው  ስራውንና ክፋቱን  ለአለምና ለአገሬው ሰው የሚያጋልጡትን፤  የለውጥ ተስፋን  ሃገር ውስጥ ላለው ህዝብ የሚሰጡትን እንዚህን በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጲያውያንን ለተወሰኑ አመታት እንዴት አድርጎ መቆጣጠር ተስኖት ሲበሽቅና ሲናደድ የኖረ ቢሆንም አሁን ግን በተለመደው የሽፈጥ ዘዴው፡ እሩቅ የሚደርስ የክፋት ተንኮሉን በውጭ ሀገራት ዘርገቶአለ። ከውስጡ አምልጠው የሚወጡ መርጃዎችና ስርአቱን ትተው ከሚመጡ የወያኔ መንግስት ሃላፊዎችና የመረጃ ሰራተኞች ብዙ ነገር ይሰማል። ይህን በውጭ ሃገር የሚደርገውን ወያኔዊ ትግል የሚያስፈጽሙ ሰራዊት ወያኔ  በብዙ አገራት አሰማርቷል። እነዚህም እንድሚከትሉት ናቸው።

  1. በኤምባሲ ና  ቆንስላዎች የሚመደቡ ወያኔውችና ከሌሎች ጎሳ የሚወለዱ ሆድ አደር ዜጎች። ተልኮአቸው የተቃዋሚ ግለስቦችን እና ድርጅቶችን ፣ በተለይም የብዙሀን መገናኛ (እንድ ኢሳት ያሉትን) መከታተልና መርጃና ማስረጃ መሰብሰብ። አብዝኛውን በተቀዋሚ አስተሳሰብ  ያለ ህዝብን  የመሬት ቦታ፣ የቤት፤ የቢዝንስ እንዲሁም ሌሎች ጥቅማጥቅምን የሚስገኝ አማላይ ፕሮፓጋንዳን መንዛት።
  2. በደህንነት ከፍሉ የተሰማሩ (ከሃገር እንዲወጡ ለስድተኝነት ጥያቄ የሚበጅ ማስርጃ በደህንነት ከፍሉ የተዘጋጀላቸው ) ባሉበት አገር በሃስት የስደተኛ ጥግኝነት ጥያቄ ያቀርቡና እስክ ዜግነት ድርስ የተቀበሉ የወያኔ ደጋፊዎችና የመረጃ ሰራተኞች። የነዚ ተልኮአቸው፡ በየተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ተቃዋሚ ደጋፊ መስለው የፓርቲው አመርር ወስጥ በመግባት፤ ድርጅቱን እንዳይራመድ፤እርስ በርሱ እንዲጠላለፍ፣ አባላቱ እንዳይተማምኑ ማድረግ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋ ህብረት እንዳይደርግ ማድርግ፤ የታወቁ የድርጅት መሪዎችን ስም ማጥፋት፤ እንዲሁም ከድርጅቱ የቃርሙትን ሁሉ ለ ወያኔ ደህንነት ማሳወቅ።
  3. ድምጽ አጥፈተው ሀገር ወዳድ  አትዮጲያዊ መስለው በሚዲያ ስራ በተለይ  በራድዮ፣ በቲቪ፣ በመሃበራዊ ሚዲዎች እንዲታወቁ የተደርጉና እምነት እንዲጣልባቸው ታዋቂ የተቃዋሚ አክቲቪስቶችንና መሪዎችን በሚዲያቸው የሚያቀርቡ፤ በህዝብ ዘንድ አመኔታ እንዲያግኙ የተደረጉ (እንዲይንቀላፉ የተደረጉ) ፤ የመረጃ ክፍሉ በሚሰጣቸው የሚስጥር ትዛዝ (ከተኙበት የሚነቁ) አሉ። የነዚህ ተልእኮ፡ ወያኔ የሚፈራቸውና በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተጽኖ ፈጣሪ፣ ሀገር ወዳድ ሙሁሮችን፣ የኪነጥበብ ሰዎችን ስማቸውን ና ስራቸውን ማራከሰና ማጥፋት ፤ ውጭ ሀገር የሚኖረውን ህዝብ ማደናገርና መከፋፈል።
  4. ቀድሞ በተቀዋሚ ድርጅት ታዋቂ ደጋፊነታቸውና አመራር አባልነታቸው የሚታወቁ ፡በኩርፊያ ከዚያም  በጥቅም የተደለሉ፣ ወደ ወያኔ ካንፕ  “አገሬ ስተልማ አይቻልሁ፤ አባይን የደፈረ መሪና ደርጅት አይቻልሁ” የሚል ዋሾ ዜማ እየዘፈኑ እውነቱን እያወቁ ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ መሳርያነት ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ሆድ አደሮች። ለነዚ  የተሰጣቸው ተለኮ፡ በሶሻል ሚዲያ (ፓል ቶክ፣ ፌስ ቡክ፤ ዩ ቱዩብ  እንዲሁም የኢንተርኔት ሬድዮና ቲቪ) የተቃዋሚ መሪዎችን የሚሳድቡ፣ ስም የሚጠፉ፤ አዲስ ወያኔዊ ደጋፊ የሚመለምሉ፤ ወያኔን ደግፎ ሰልፍ እንዲወጣ  የሚያስተባብሩ) እንዲሁም በሚያስተናግዱት ሚዲያ የወያኔን ቱባ ባለ ስልጣኖችን እይጠሩ ፕሮፕጋንዳ የሚሰሩ፤ እነዚህን አረመኔ ወንጅልኞች ባለ ስልጣናትን  ጀግና አድርጎ  ቀባብቶ መፍጠርን፤ ሰማይ ማደርስን  የመሳሰሉትን  እንከፍ ሚና የሚወጡ፣  በወያኔ እርጥባን የሚጣልላቸውና ደግሞም ወያኔ የሚንቃቸው ናቸው።
  5. ወያኔ ለትምህርትና ለ ስልጠና የላካቸው ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው። የነዚ ተልኮ አብዛኛእውን ግዜ በውጭ ሀገር ለሚያግኙት ጋዜጠኛ፣ ታዋቂ ሰው፣ ፕሮፌሰር፣ የሌላ አገር ተማሪዎች፣ ባልስልጣኖች፤ የተማሪና ሙያ ማህበርት ወስጥ ሰርጎ በመግባት የወያኔን ዲሞክራሳዊነት፤ የእድግት ጉዞ ፣ፕሮፕጋንዳ መንዛት ነው። ተቀዋሚ ድርጅቶችን በሚያድርጉት ስብስባ በመገኝት ሙሁር መሰል አደናጋሪ ጥያቄ መጠየቅና አድማጩን ማደናበር። በውጭ ለሚታተሙ ወያኔን የሚኮንኑ  ጽሁፎችን የፈርንጅ ጋዜጣዎችን የአምስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ሁይማን ራይትስ (Human Rights Watch) ና የመሳሰሉትን ዘገባዎች  የሚቀወም ጽሁፍ የሚያቀርቡ  ናቸው።
  6. ቀደም ብሎ ወያኔ ጫካ እያለ ሲደግፉ የነበሩ፣ ኑሮአቸውን በውጭ አገር ያደርጉ፣ የሚኖሩበትን ሃገር ዜግነት የወሰዱ፤ ነግር ግን የትግራይ ተውላጅ ብቻ በመሆናቸው በዘርኝነት የበላይንት መንፈስ የተጠናወታቸው ጭፍን  ደጋፊዎችና ሙሁር ነን  ባይ ዘርኛ ትግሬዎች። እንዚ በገንዝብ፤ በማባባል፣ በሌላም በሁሉም መስክ በተሰጣቸው ሚና የሚሳትፉ ሌላወን ኢትዮጵያዊ የሚንቁ ና የማይቀበሉ ናቸው።
  7. ብዙ በሺዎትና  ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወያኔው የሚከፍላቸው ሎቢ የሚሰኙ የፈርንጆች ድርጅቶች፤ ለሚከፍላቸው ገንዝብ የሚሰጣቸውን ስራ የሚሰሩ። እንዚህም አብዛኛውን ባአሜሪካ አገር እና ባአወሮፓ የሚገኙ፤  የአሚሪካንና አውሮፓውያን ፖለቲከኞችን፡ ወያኔን የሚጠቅም ፖለቲካዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ወሳኔ ምክር ቤታቸው ወይም ካቢኔያቸው  እንዲደግፍ የሚያባብሉ፤ወያኔ ላይ የተቃጣ ነቃፊ ህግ እንዳይጸድቅ እንዲተጉ የሚያደርጉ ናቸው።  ታዋቂ  የፈርንጅ ጋዜጠኞችን በማባባባልና በመደለል በ ጋዜጣ ወይም መጽሄታቸው ስለ ወያኔ መልካም ነገር የሚሰብኩ፤ በውሸት በዚህ አሃዝ የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ አደገች ብለው የሚያሳትሙትን የሚለማመጡ ናቸው። በተጨማሪም በገንዘብ የተገዙ የኮምፒትርና ስልክ መርጃ ጠላፊ የወጭ ሀገር ባለሞያዎችን (hacker) ይጨምራል። የተቃዋሚ መሪዎችን፣ ተጽኖ ፈጣሪ ሙሁሮችን ግልሰቦችን እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቶችን  ኮምፒተር ፋይሎችን፣ መረጃዎችን፣መልክቶችን፣ የስልክ ንግግሮችን በህገ ወጥ መንገድ ወያኔ እንዲሰርቅ የሚያስችሉ ናቸው።

ወያኔ እንዚህን ሁሉ ሰራዊቱን  በወጭ ሃገር ባለው ኢትዮጲያዊ ላይ አሰምርቶአል።

ይህ እንግዲህ  በተለይ ታላላቆቹ አገሮች አሜሪካና አወሮፓ በተለይ ዮናይትድ ኪንግድምን ጨምሮ  በይፋ ከሚሰጧቸው ገንዘብ፣ ብድርና ወታደራዊ እርዳታና ስልጠና ጨምሮ ( በነዚሁ አገራት የሚሰጡትን ግዳጅ ወያኔ በተለይ በሱማሌና በሱዳን ያለውን አከራሪ እስልምናን በወታደር በመዋጋት  ትዛዝ ስልሚፈጽም ርዳታውና ድጋፉ ይስጠዋል) የሰባዊ መብት ተከበረ አልተከበረ  አንዳች ደንታ ከሌላት፣ ባአፍሪካ አዲሲትዋ ቀኝ አዙር ኮሎኒያሊስት ከሆነችው ቻይናን ጨምሮ የአልም ባንክና፣ አይ አሜ አፌ (IMF) የሚሰጡት  ገንዘብ  የፋፋው ወያኔ  በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው የግፍ አገዛዝ ቀጥሎአል። ከኢትዮጲያውያን የሚዘርፈውና ከመኖሪያቸው እያፍናቀለ መሬት የሚሸጠው ወያኔ፡ አሁንም ከእኔ በላይ ላሳር ብሎ በተሃደሶ አዲስ ሽንገላ የተቆጣወን ህዝብ በአስቸኳይ መንግስት  (State of Emergency decree) እያስፈራራ  እድሜውን አስረዝሞአል።

ይህን ሁሉ እርዳታና የገንዝብ፣ የመሳርያ ሀይል ከታጠቀው ወያኔ ሰላማዊ፣ ፍታሃዊ  አስተዳደርና  አገር የኢትዮጲያ ህዝብ አያግኝም።  ተስፋ ሳይቆርጥ በአላማው ጸንቶ፣ ወገቡን ታጥቆ ፣ የወያኔን መከፋፋያ ዘዴ አፍርሶ፤ በመተባበርና ባንድነት በመታገል ይህን አስከፊ አገዛዝ መጣል ያስፈለገዋል። እርስ በራስ በወያኔው ወጥምድ ገብተን ከምንጣጣል፤  በህብረት ወያኔን በሚያስፈልገው የትግል ዘዴ ሁሉ ጥለን የጋራ ፍትህ የሰፍነባትን፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚታይበት፣ የሚዳኝበት ሰላማዊ ሃገር መገንባት ይገባናል።

ለሁሉም አምላክ ይርዳን።  አሜን!

posted by Gheremew Araghaw

ከፖለቲከኞቻችን ክፋትና ጥላቻ ይልቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግነት እና ጥበበኛነት እንደሚበልጥ መቼም አትርሱ | ሸንቁጥ አየለ


ደብብ አፍሪካ ንብረት አፍራህ: ደቡብ አፍሪካን ልትበዘብዝ ነዉ ተብሎ ያለችዉ ጥቂት ንብረቱ የወደመበት ኢትዮጵያዊ ሰዉ ጉዳይ ያስገርማል:: ይህ ሰዉ በአንድ ወቅት ደብዳቤ ጽፎልኝ ሳነበዉ የታሪኩ ዉስብስብነትና አሳዛኝነት አስገረመኝ:: ኢትዮጵያ ዉስጥ የደረሰበት በደልና ግፍ ከደቡብ አፍሪካዉ ግፍና በደል ጋር ተዳምሮ አጀብ ያስብላል::

ይህ ሰዉ ከዛሬ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተሰደድ:: ልጁ ጓደኛዬ ነዉ:: ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲሰደድ እንዲህ የሚል ንግግር አድርጎልን ነበር ” ደቡብ አፍሪካ ቢያንስ ያፈራሁትን ሀብቴን ማንም አይነጥቀኝም” የሚል:: ይህ ሰዉ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሰደድ የተነሳዉ በደቡብ ኢትዮጵያ በጉራፋርዳ ወረዳ ያፈራዉ ሀብት ሁሉ ባንድ ቀን ወደ አመድነት ከተለወጠ ብኋላ ነበር::

ይህ ሰዉ የቤተ ክህነት አገልጋይ ነበር:: ሶስት ልጆችም ነበሩት:: በሀገሩ በኢትዮጵያ ሲኖር በጉራፋርዳ ሲኖር እስከ 1500 ኩንታል ድረስ ሩዝ በየአመቱ ማምረትም ችሎ ነበር:: የነበረዉም እቅድ መኪና ገዝቶ በመኪናዉ ልዩ ልዩ የንግድ ስራዎችን መስራት ነበር:: በገዛ ሀገሩ የተከሰተ ክስተት ጠቅላላ ራዕይዉን ለወጠዉ:: ያፈራዉን ሀብት ባንድ ሌሊት አወደመዉ:: የሚያገለግልበትን ቤተክርስቲያን ባንድ ሌሊት አጠፋዉ:: ንብረቱም ተቃጠለ::ቤተክርስቲያኑም በዚያዉ ሌሊት ተቃጠለ:: ከዚህ ሰዉ ጋር 78 ሽህ አባወራዎች ማለትም ወደ 450 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች ባንድ ሳምንት ጉራ ፋርዳን ለቀዉ እንዲወጡ እርምጃ ተወሰደባቸዉ:: የተሰጣቸዉ ምክንያት ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያ ሀገራችሁ አይደለም የሚል ነዉ:: ለምን ብለዉ ሲጠይቁ ደግሞ እናንተ አማሮች ናችሁ የሚል ነበር::

ይህ ሰዉ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሰደድ የከፈላትን ጥቂት ገንዘብ እንድትኖረዉ የረዳዉ የጉራ ፋርዳ ተወላጅ የሆነ ኢትዮጵያዊ ነዉ:: ይህ ኢትዮጵያዊ የሚንጢ ብሄረሰብ ቢሆንም አማራ ወንድሙን ለመርዳት የቻለዉን ሁሉ አድርጎለት ነበር:: ንብረቱ: ቤቱና ሁሉ ነገሩ ሲቃጠል የተወሰኑ ከብቶቹን ያሸሸለትና የደበቀለት ይሄዉ የሚንጢ ብሄረሰብ አባል የሆነ ሰዉ ነበር:: ይሄዉ የሚንጢ ብሄረሰብ የሆነ ኢትዮጵያዊ ያደረገዉ ነገር አስገራሚ ነበር:: ከብቶቹን ሸጦ ገንዘቡን ይዞ ለተጠቃዉ አማራ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት ሰጥቶት ነበር::

ይህ ሰዉና ሌሎች ተፈናቃዮች በህግ መብታቸዉን ለመጠየቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዉ ነበር:: ሆኖም ወረዳ : ዞን : ክልል እና ፌደራል ላይ ያሉ ፍርድ ቤቶች በሙሉ የአማሮችን ጉዳይ አናይም ሲሉ እንቢ አሉ:: የህገ መንግስት ጥሰቱ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ በደንብ ለመረዳት ያን ጽሁፍ ፈልጎ አሁንም ማንበብ ይቻላል::

ስለህግ ማዉራት አይቻልም:: ህጉ ተዝግቷልና:: ፖለቲከኞች ላይ አቤት ማለት አይቻልም:: ፖለቲከኞቹ አማራ ላይ የወረደዉ ዉርጅብኝ ልክ ነዉ ብለዋልና:: አቶ በረከት ሲጠዬቁ የመለሱት መልስ እንዲህ የሚል ነበር:: “አማሮቹ ከጉራ ፋርዳ መባረራቸዉ ልክ ነዉ:: ምክንያቱም የአካባቢዉን አርሶ አደር ሄደዉ ጭሰኛ እያደረጉት ነዉና”::

አቶ መለስ ነብሳቸዉን ይማረዉና የመለሱት መልስ እስካሁን ሳስበዉ እንዴት አንድ ሀገር የሚመራ ሰዉ እንዲህ ያስባል ብዬ ጭዉ ያለ ሀሳብ ዉስጥ እገባለሁ:: አቶ መለስ ሲመልሱ “አማሮቹ የተባረሩት ደን እየጨፈፉ ስለሆነ ነዉ” አሉ:: አስከትለዉም “ጉራፋርዳ በምስራቅ ጎጃም አማሮች ስለተጥለቀለቀ የአማሮች መባረር ልክ ነዉ” ሲሉ መለሱ::

አንድ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ደፍሮ አቶ መለስን ህገመንግስታዊ የንብረት መብት ጥያቄ ጠዬቃቸዉ:: አቶ መለስም የአማሮቹ ንብረት መወሰዱ: መቃጠሉ ምንም ሳይመስላቸዉ የመለሱት መልስ አስገራሚ ነበር:: “ንብረታቸዉን ለማስመለስ ምናልባት በህግ ሊጠይቁ ይችል እንደሆን ወደፊት ይታያል” ሲሉ ነበር የመለሱት:: 106 አንቀጽ ያለዉ ህገ መንግስት የጻፉ ፖለቲከኞች: ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በህግ ፊት እኩል ነዉ: ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በፈለገዉ የሀገሪቱ ክፍል መኖር መብቱ ነዉ : ማንኛዉም ሰዉ የንብረት መብቱ የማይገፈፍ ነዉ ብለዉ ህገ መንግስት የሚባል ዶክመንት ያቀረቡ ፖለቲከኞች እንዲህ ብለዉ ሲመልሱ ጆሮ ጭዉ ያደርጋል::

በተመሳሳይ በ1994/1995 ዓም 20 ሽህ አባዎራ ኢትዮጵያዉያን ማለትም ከ100 ሽህ ሰዎች በላይ ከወለጋ ሀገራችሁ አይደለም ተብለዉ ተባረሩ:: የተሰጣቸዉ ምክንያትም አማሮች ስለሆናችሁ ወለጋ ሀገራችሁ አይደለም የሚል ነዉ:: እኔም ለስራ ጉዳይ በ1995 ዓም ወደ ወለጋ ሄጄ ነበር:: ነገሩን በቅርበት እከታተልም ስለነበር የወለጋ ነዋሪዎችን በተለይም አርሶ አደሮችን አመለካከት ለማግኘት በጉዳዩ ላይ አንዳንድ ጥያቄዎች እያነሳሁ ሀሳባቸዉን እንዲያካፍሉኝ አደርግ ነበር:: ብዙዎች ነዋሪዎች የሚመልሱት መልስ አንድ ነበር:: “ልጆቻችን በታሪክ ዉስጥ ጠላት ሆነዉ እንዲቀጥሉ: ኢትዮጵያዉያንን ደም ለማቃባት የተሸረበ ሴራ ነዉ:: ሀገሩማ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነዉ ” የሚል ነበር::

ከሁሉም በላይ ግን የሚከተለዉ ታሪክ ድንቅ ነዉና ላካፍላችሁ:: አማራ ይዉጣ እያሉ ክፉ ፖለቲከኞች ከበሮ በሚደልቁበት ወቅት በነቀምት ዙሪያ የሚኖሩ አንድ የኦሮሞ አርሶ አደር ማሳ ላይ ለጥናትና ምርምር ተገኝተን ነበር:: እኝህ አርሶ አደር ካላቸዉ ማሳ ላይ ከወሎ ለመጡ አንድ አማራ አርሶ አደር መሬታቸዉን ቆርሰዉ ሰጥተዋቸዉ ነበር:: እኔም ነገሩ በጣም ገርሞኝ የኦሮሞዉን አርሶ አደር ትክክለኛ ግንዛቤ ለማግኘት ብዬ ቀጥተኛ ጥያቄ ጠየቅኋቸዉ:: እንዲህ ስል “አማራ ከወለጋ ይዉጣ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት እርስዎ መሬት ቆርሰዉ ለአማራ አርሶ አደር መስጠትዎት ምን ቢያስቡ ነዉ? ምንስ ጫና ደረሰብዎት?”:: የኦሮሞዉ አርሶ አደር እንዲህ ሲሉ መለሱ ” አማራ የኦሮሞ አንዱ ጎሳ ነዉ እንጅ የተለዬ ሰዉ አይደለም::” አሉ ቁርጥ ባለ ሀሳብ:: ነገሩ አልገባኝም:: እናም ደግሜ ጠዬቅሁ:: “የኦሮሞ አንዱ ጎሳ ነው ማለት ምን ማለት ነዉ?” ስል:: ” እሳቸዉም በእርግጠኝነት መለሱልኝ “ያዉ እንደኛ ሰዉ ነዉ ማለቴ ነዋ:: ኦሮሞና አማራ የሚለያያቸዉ ምንም ነገር የለም:: ወንድማማች ናቸዉ”::

እርግጥ ነዉ ይሄን ወርቃማ የኢትዮጵያ ህዝብ አስተሳሰብ በመላ ሀገሪቱ ለስራና ለትምህርት ስዞር አስተዉያለሁ:: በጥልቀት በመረመርሁት የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክም ዉስጥ ይሄን መሰል አስገራም ወርቃማ ታሪኮችን አንብቤአለሁ:: ለምሳሌ ፕሮፌሰር ሰባስኪ የሚባለዉ የጣሊያን ፕሮፌሰርና ታሪክ ጸሃፊ “የኢትዮጵያ ታሪክ:-በፋሽት ጣሊያን ወረራ ወቅት” ብሎ በሰዬመዉ መጽሀፉና እምሻዉ አለማዬሁ ወደ አማርኛ በመለሰዉ መጽሀፍ ዉስጥ የሚገርም ታሪክ ሰፍሮ ይገኛል::

ታሪኩን ባጭሩ ስንጨምቀዉ የሚከተለዉ ነዉ:: ጣሊያን ዋና ግቡ የኢትዮጵያን ብሄረሰቦች አብረዉ እንዳይቆሙ መበታተን ነበር:: በተለይም ጣሊያን የአማራ ህዝብን ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ብሄረሰቦች ነጥሎ ማጥፋት ይፈልግ ነበር:: እናም ሁሉንም የኢትዮጵያዉያን ብሄረሰቦች ጸረ አማራ አድርጎ አስነስቷቸዉ ነበር:: ሆኖም በመጨረሻዉ ሰዓት ጣሊያን የተረዳዉ የኢትዮጵያን ህዝብ መለያዬት እንዳልቻለና አማሮችን ከሌሎች ብሄሮች ለመነጠል ያደረገዉ ሙከራ ሁሉ እንደከሸፈበት ተረድቶ ነበር:: ለዚህም ማረጋገጫዉ በርካታ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች አስተዳዳሪያቸዉን ሲመርጡ ችሎታ እስካለዉ ድረሰ በርካታ አማሮችን አስተዳዳሪዎቻቸዉ አድርገዉ እየመረጡ የኢትዮጵያዉያንን ህብረት ሲያጠነክሩት ነበር:: የኢትዮጵያ ህዝብ ህብረትም ጠንክሮ ለነጻነት በጋራ ጣሊያንን በህብረት ሲወጉት ነበር::

እናም በምሬት ከደቡብ አፍሪካ ደብዳቤ ለጻፈልኝ ጓደኛዬ ይሄን የትዮጵያ ህዝብ ደግነትና ጥበበኝነት ካካፈልኩት ብኋላ አሁን በደቡብ አፍሪካም የተከሰተዉ ክፉ ስራ የጥቂት እብሪተኛና መጥፎ ፖለቲከኞች ስራ እንጅ የህዝቡ እንዳልሆነ እንዲገነዘበዉ የሚረዳ ደብዳቤ ጻፍኩለት:: ከፖለቲከኞቻችን ክፋትና ጥላቻ ይልቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግነት እና ጥበበኛነት እንደሚበልጥ መቼም አትርሳ የሚል ደብዳቤ ሰደድኩለት:: እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ በበታችነት : በጥላቻ እና በአላዋቂነት የተያዙ ፖለቲከኞች ባህሪ የደቡብ አፍሪካን ህዝብ ባህሪ ሊወክል የሚችል አይመስለኝም የሚል ነጥብ አካትቼ ሰደድኩለት::

እሱም በተራዉ የሚከተለዉን ጥያቄ ለእኔ አቀረበልኝ:: እኔም የእርሱን ጥያቄ ለእናንተ አቀረብኩላችሁ::

“የወለጋዉና የጉራፋርዳዉ አርሶ አደሮች ህገ መንግስት አርቅቀን በህጉ እንመራበታለን ከሚሉት ፖለቲከኞች ለምን ተሻሉ? ልባቸዉ ነዉ የተሻለው ወይስ እዉቀታቸዉ? ወይስ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ መኖር ጣዕም በተግባር የቀሰሙ ሰዎች በመሆናቸዉ ይሆን እንዲህ ከፍ ያለ የሰበዓዊነት ታሳቢ ሊኖራቸዉ የቻለዉ?”

በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት እመለስበት ይሆናል::እርሱ የጠየቀዉን ጥያቄ ግን እናንተም እኔም እያንሰላሰልን እንቆይ::

———–

ማስታወሻ:-

———–

ይሄ ጽሁፍ ከሁለት አመት በፊት ተጽፎ ለህዝብ እንዲደርስ የተደረገ ጽሁፍ ነዉ::የጽሁፍ ይዘት ጥልቅ ቁም ነገሮችን ለህዝብ ስለሚያስተምር በደንብ ወደ ህዝባችን እንዲደርስ በስፋት ቢሰራጭ መልካም ነዉ::

posted by Gheremew Araghaw

ይህቺ አገር የማናት?

ይህቺ አገር የማናት? Biniam Hirut

ኢትዮጲያ ውስጥ ካለኝ የስራ እና የንግድ ልምድ በመነሳት….ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ወደጎን በመተው በአገሪቱ ውስጥ እጅግ እየተስፋፋ የመጣውና መመለሻ የሌለውን የሙስና ባህልን ሳስብ በጣም አዝናለሁ፣ እሰጋለሁም፡፡ በግሌ ፈጽሞ ሊደረጉ የችላሉ ብዬ ያላሰብኳቸው ነገሮች ደርሰውብኛል፡፡ በኢትዮጲያ ውስጥ በአንድ አመት ብቻ በሙስና የሚጠፋው ገንዘብ አባይን ለመገደብ ከሚወጣው ይተናነሳል ብላችሁ ነው ?
እጅግ የሙስና ስር የሆኑ ድርጅቶች በርካታ ናቸው

በጣም ትልቁን ቦታ የሚይዙት ግን
የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

—የሀገሪቱ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የውጪ እዳ የተበደረ ድርጅት ነገር ግን እሰራለው ካላቸው ስራዎች እሩቡን እንኳን መስራት የማይችል፡፡ በጄኔራል የሚመራ እና በርካታ የህወሃት የቁርጥ ቀን ልጆችን በዙሪያው አቅፎ የሚንቀሳቀስ፡፡ ድርጀቱ ውስጥ ያለው የሙስና ሰንሰለት እጅግ የተወሳሰበ እና ከአንድ መንደር የመጡ ሰዎች ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ ድርጅት ጋር ምንም አይነት ስራ ለመስራት ፓስወርዱ የሰፈር ስም ነው፡፡ ከሰሩ ግን በአንድ ጀምበር ሚሊዮነር ይሆናሉ፡፡ እዳውን ግን ትውልድ ይገፈግፋል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ግን መቼም የዚህ ድርጅት ሃላፊዎች ሹመት በሹመት ይሆናሉ እንጂ ምንም ቢያጠፉ የሚነካቸው የለም፡፡
የኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን

—ስለዚህ እንኳን መናገር የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ከጽዳት ሰራተኛ እስከ ሀላፊዎች ድረስ አሁንም በሰፈር ልጆች የተሞላ ድርጅት ነው፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ ከአንድ መንደር ብቻ ለመቅጠር የተቋቋመ እስኪመስል ድረስ፡፡ በተለይ ቁልፍ የሆኑ የጉምሩክ ቦታዎች ላይ የሚሰሩቱ፡፡ በጣም የማዝነው… በአረብ ሀገር ስንት ስቃይ አይተው የሚመጡ እህቶቻችንን እና ተራ መንገደኞችን ካልሲና ቀሚስ እየቆጠሩ ያለምንም ምህረት ፍትሃዊ ያልሆነ ታክስ የሚያስከፍሉ ሰዎች በቢሊዮን የሚቆጠር ታክስን ግን በትንንሽ ፍርፋሪ የሚያጭበረብሩ ሰይጣኖች የሞሉበት ድርጅት ነው፡፡
የኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

—በኢንቨስትመንት ስም በርካታ ጥቅማጥቅሞች የሚገኝበት ይህ ቤት ሀገሪቷ የምትዘረፍበት ቤት ነው፡፡ በኢትዮጲያዊያኖችም በውጭ ሀገር ዜጎችም፡፡ በተለይ ቻይናውያን እድሜ ለዚህ ድርጅት እና ይህ ድርጅት ለሚሰጣቸው የተለያዩ ድጋፍ፣ ከለላ፣ እና ጥቅማጥቅሞች፡፡ የሀገር ውስጥ ነጋዴዎችን ህገወጥ በሆነ መልኩ በከፍተኛ ሙስና ሽባ እያደረጉ ከሌሎች ሀገር ሰዎች ጋር ስንት ብር ሰሩ.?..በየመንደሩ በትንንሽ ኩሽናዎች በቻይናዎች የሚሰሩ ስንት ጉዶችን ያስፋፋዉ ይሄ ድርጅት ነው፡፡ ቆዳዎት እስከነጣ ድረስ ለአበሻ የማይቻል ነገር ሁሉ ይቻላል፡፡ አሁንም በሚገርም ሁኔታ ሃላፊዎችን የሚነካ ማንም የለም፡፡

ይቀጥላል ..በየ መስሪያ ቤቶቹ… ክ/ከተማ..ቀበሌ/… እያለ፡፡ ይህ ሁሉ ገንዘብ ግን የት ነው የሚገባው ? ይህንን ማስተዳደር ያልቻለ መንግስትስ ምን ማስተዳደር ይችላል?

posted by Gheremew Araghaw

በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ (አያሌው መንበር)

በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ
(አያሌው መንበር)

ህወሃቶች አጀንዳ መዘዝ ሲያደርጉ መቸም የሚያክላቸው የለም።ዛሬ ደግሞ በVOA ጋዜጠኛዋ አዳነች ፍሰሃየ በኩል መቀሌን ከሁለቱ የአማራ ከተሞች (ከባህር ዳርና ደብረ ብርሃን)፣ከአዋሳ፣…ወዘተ እያወዳደሩ፣ ሁለት ትግሬዎችን ለምስክርነት በመጥራት <<እኛ እኮ ነን በድህነት ውስጥ ያለን፣የተረሳን ነን>> የሚልን አስቂኝ ዘገባ በመስራት አጀንዳ ሰጥተውናል።ይህ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት አባይ ወልዱ የትግራይ ኪራይሰብሳቢዎች “በህዝቡ ስም አትነግዱ” በማለት ከገለፀው ጋር ተቀራራቢ ይሁን ተቃራኒ አንባቢ የሚፈርደው ሆኖ እውነታው ግን የሚከተለው ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ነገር ለማሰስሰብ አስቤ በይደር ይዠው የነበረውን እቅድ ይህንን እንዳየው ግን ወቅቱ አሁን ነው መሰለኝ ብየ የመንግስትና የNGO መረጃዎችን ለማገላበጥ ሞከርኩ።ከዚያም አሸማቃቂ ሀገራዊ መረጃዎችን ተመለከትኩ።በእርግጥ በመረጃው መሰረት ከሆነ ለውጦችም ይታያሉ።
እንዲያው የሆነው ሆኖ እ.ኤ.አ በ1995 46 የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶው ህዝብ ከዓለማቀፉ የድህነት መስመር በታች እንደሚኖር ይህ አሃዝ በ2004/5 እንደቀነሰ ያሳያል።ሌላ የመንግስት የGTP II አሃዝ የድህነት መጠኑ በ2014 ወደ 23 በመቶ እንደወረደ ያመላክታል።
በመጀመሪያው ጊዜ (ከ95 እስከ 2004) በዚህ ዳታ ላይ የድህነት መጠኑ በትግራይ ሰፋ ብሎ 48.5 በመቶ በአማራ ደግሞ 40 በመቶ ነበር ይላል Poverty and Inequality in Ethiopia 1995 to 2004 በሚል በአ.አ.ዩኒቨርሲቲው ጣሰው ወልደ ሀና፣ በዓለማቀፉ የምግብ ፖሊሲ የጥናት ተቋሙ John Hoddinott እና Stefan Dercon በተባሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አማካኝነት የተጠናቀረውና መነሻውን መንግስታዊ ዳታ ያደረገው መረጃ።
ይህንን መረጃ ከ1995 እስከ 2011 ስንመለከት የትግራይ የድህነት ቅነሳ አሃዝ ከ48 በመቶ ወደ 30 (የ18 በመቶ ልዩነት አሳይቴ) ሲወርድ የአማራው ግን ከ40 በመቶ ወደ 30 በመቶ (10 በመቶ ብቻ ነው) ቅናሽ ያሳየው።
ይህ እንግዲህ ባለው የሀገር ውስጥ የምጣኔ ሀብታዊ እድገት እንኳን እንደሌላው እኩል መጠቀም ያለመቻሉ አንዱና ዋናው ማሳያ ነው።በ2014 በተደረሰበት የ23 በመቶ የድህነት ቅነሳ (ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ህዝብን) ክልላዊ ንፅፅር ለጊዜው ባለገኘውም ከዚህ የተለየ አሃዝ እንደማይኖር ግን ነባራዊ ሁኔታው ይነግረናል።
አንዳንድ ተጨማሪ ሰነዶችን ለማገላበጥ ያህል እስኪ የኢህአዴግን “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ትንሽ እንቃኘው።በዚህ እቅድ ውስጥ የተለያዩ ሀገራዉፕ ዳታዎች ታጭቀዋል።ክልላዊ የአፈፃፀም ንፅፅር አለመሰራቱ ሆን ተብሎ ለትችት እንዳይጋለጥ ቢመስልም ያለው ላይ ተንተርሶ ግን አስተያየት መስጠት ይቻላል።ለአሁኑ የቁጠባና እና ኢንቨስትመምት እንዲሁም ወጭ ንግድን (Export) እንመልከት።
ቁጠባ በየትኛውም ሀገር ተርፎህ ሳይሆን አብቃቅተህ ለተሻለ ነገር ስትል የምታስቀምጠው ሀብት ነው።በዚህ መለኪያ ስናየው ኢትዮጵያውያን አብቃቅተው ብቻ ሳይሆን ተቸጋግረውም ቢሆን ይቆጥባሉ።በተለይም የቁጠባና ብድር ተቋማት እንደ አስገዳጅ ህግ እያደረጉ አርሶ አደሩን እየቀፈደዱ ያስቆጥባሉ።የቀበሌ አመራርም መገምገሚያው እንደነበር እኔ ራሴ አረጋግጫለው።የሆነው ሁኖ ቁጠባ ብዙ ክፋት የለውም።ክፋቱ ግን የቆጠብከው ለራስህና ለአካባቢህ ሳይውል ሲቀር ነው።
በኢትዮጵያ ያለው የቁጠባ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ይባልበት ከነበረው ከ10 በመቶ በታች ቁጠባ በጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ አሃዝ ተምዘግዝጎ ወደ 25 በመቶ እየተጠጋ ነው።ከዚህ ውስጥ የአማራ ክልል ትልቅ ድርሻ አለው።
ቁጠባ ብዙ ጊዜ የሚውለው ለሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ነው።የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ደግሞ አማራን ተጠቃሚ ያላደረገ እንደሆነ አንድ ዳታ ልጨምር።
አንድ የመንግስት መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው ዓመት ወደ 2ሺህ የሚጠጋ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲሰጥ ለትግራይ 6 ሚሊዮን ህዝብ 187 ፕሮጀክት፣ ለ30 ሚሊዮን አማራ ህዝብ ግን 159 ፕሮጀክት (ለዚያውም ሊሰራ የማይችል) ነው የተሰጠው።በቀላል ሂሳብ ስሌት ስንመለከት ትግራይ 187 ሲደርሳት አማራ 159 ሳይሆን 935 ፕሮጀክቶች ሊደርሱት ይገባ ነበር።
በገቢ ደረጃም ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በገለፁት መሰረት ከ2006 እስከ 2009 ወደ ትግራይ በኢንቨስትመምት ስም 12.6 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ሲደረግ ወደ አማራ የሄደው 2.8 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው።የአማራው ከትግራዩ በ4 እጥፍ ያንሳል፤ አማራው ከትግራይ ህዝብ ደግሞ በትንሹ በ6 እጥፍ ይበልጣል።
ወደ ምሳሌ ብንገባ እንኳን ባለፉው ዓመት 2008 ዓ.ም እኮ የ5 ቢሊዮን ብር ግዙፍ (በሀገር ደረጃ ምናልባት ግዙፍ ይመስለኛል) ፋብሪካ የተመረቀው፣ በዚህ ወር እኮ ነው የመጀመሪያው #ሞተር ፋብሪካ እዛው መቀሌው የተመረቀው፤በዓመት 18 ቢሊዮን ብር ገቢ ያስገኛል የሚባለው 120 ፋብሪካን በአንድ ላይ ያቅፋል የተባለው በ2.3 ቢሊዮን ብር የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተገነባ ያለው መቀሌ አይደለም እንዴ?፣90 አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ባለሀብቶችን ያሳተፈው የትግራዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤግዚቪሽን እኮ እየተካሄደ ያለውና የእናንተን ተጠቃሚነት ያሳየን ትናንት ግንቦት 19 ነው….የኬሚካል፣የጨርቃጨርቅ፣ የብረታብረት ፋብሪካዎች ትግራይ አይደሉምን? ይህ እኮ ሀቅን መካድ ነው።
የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንትን ስናይ ደግሞ ለአማራ የተመደበው 4.5 ቢሊዮን ብር በሲስተም ለትግራይ መሰጠቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ስለሆነም አማራ የሚቆጥበው የቁጠባ ገንዘብ ለትግራይ ኢንቨስትመንት እየዋለ ነው ማለት አይደለምን?
ሌላው ጉዳይ የገቢ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ሁኔታን ስንመለከት እ.ኤ.አ በ2009 ከነበረበት 54 ቢሊዮን ገደማ በ2016 ወደ 170 ቢሊዮን ብር አድጓል።ከዚህ ውስጥ የአማራ ግብር ከፋይነት ድርሻ በሀገሪቱን ከፍተኛ ነው።
የክልሉ ገቢ አሰባሰብ በ2012 ዓ.ም (ከሶስት ዓመት በኋላ) የክልሉ ወደ 18 ቢሊዮን ያድጋል ይላል እቅዱ።የሚሰበሰበው ገንዘብ በቀጥታ ወደፌደራል ገቢ ሆኖ ነው የበጀት ድልድል የሚደረገው።
ይህ የታክስ ገቢ አሰባሰብ የሚያደገው እንግዲህ የህዝቡ የገቢ መጠን ሳያድግ፣ ብዙም Value add ባልተደረገበት፣ የክልሉ ህዝብም ግብርና ላይ በተንጠለጠለበት ነው።
ሰብስቦ ለራሱ እንዳይጠቀም እንኳን የሚልከው ወደ ፌደራል መንግስት ነው።ከዚያም አጠቃላይ የሀገሪቱ አቅም ታይቶ ነው የሚከፋፈለው።የሀገሪቱ ከፍተኛ በጀት ለካፒታል ፕሮጅፕክቶች ማስፈፀሚያ ሲበጀትም አማራ ተጠቃሚ አይሆንም።ምክንያቱም ባለፈው እንደጠቀስነው ለአማራ ህዝብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይገነባሉ ተብለው ከተያዙት ፕሮጀክቶች ከሀምሳ በላይ ሳይፈፀሙ ሲቀሩ በትግራይ ግን በየጊዜው ነው የምረቃ ሪቫን የሚቆረጠው።ስለዚህ አማራ ሁለት ጊዜ ይበደላል ማለት ነው።
የወደፊቱን የሀገሩቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ስንመለከት ደግሞ የበለጠ ያሳስበናል።አብዛኛው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለው ትግራይና አዲስ አበባ ዙሪያ ነው።የግብርናን ጉዳይም በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ እናውቀዋለን። የግብርና ውጤቶች ወጭ ንግድ ድርሻ 3.6፣ በመቶ የአምራች ኢንዱስትሪው ደግሞ 12.5 በመቶ ነው።
በ2020 በአብዛኛው አማራ የሚያመርተውና የሚተዳደርበት የግብርና ምርቶች ወጭ ንግድ ድርሻ በ6.5 በመቶ እንዲታድግ እቅድ ሲያዝ ትግራይንል አ.አ ዙሪያን ያማከለው አምራች ኢንዱስትሪ ግን ወደ 26 በመቶ እንዲያድግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራበት ነው።ይህንን ስንመለከት ኢንዱስትሪ ወደ አማራ እንዲስፋፋና ፍትሃዊ እንዲሆን የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር ወይም 1/3ኛ የሀገሪቱ የግብርና ምርት አምራቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የግብርና ምርት ወጭ ንግድ እድገትን የሚያሳይ እቅድ ሳይነደፍ ለቀጣዩ ዘመንም አማራ ዛሬ ቆም ብሎ እምቢ ካላለ የበለጠ ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።በደላችን በሁሉም ዘርፍ ነውና ትግላችንም ሁሉን ዓቀፍ መሆን አለበት።..
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ
አዳነች ፍሳሀየ ትግራይ ከእነ “ባህር ዳር፣ደብረ ብርሃን፣አዋሳ፣አዲስ አበባ” ስትነፃፀር ችላ ተብላ በድህነት አረንቋ እየማቀቀች ነው የምትለን ሁለት ትግሬዎችን ለስምክርነት ጠርታ እንግዲህ አይኗን በጨው ቀብታ ነው።ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ ነውና ነገሩ።
ሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት ውስጥ ውስጥ ሆና በተከታታይ እድገት ውጥ ማለፏ እኮ ወደነጋቲቭ የገባውን የኦሮሚያና አማራ የምጣኔ ሀብት መነቃቃት ትግራይ በእጇ ስላስገባች እንጅ ሌላ ምንም ሎጅክ የለውም።ለአንድ ሀገር እድገት እንቅፋት ከሚባሉት አንዱ የሰላምና መረጋጋት አለመኖር ነው።ኦሮሚያም አማራም ባልተረጋጋ ህይወት ውስጥ ናቸው።
የሀገሪቱ እድገት ግን ቀጥሏል እያሉን ነው።ይህ ለምን ሆነ ሲባል ምንም እንኳን ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም መገመት ግን አያዳግትም። የአምራች ኢንዱስትሪው ትግራይ ላይ በመገንባቱ የአለመረጋጋቱ ሰለባ አለመሆኑ ትልቅ ድርሻ ይይዛል።የአገልግሎት ዘርፉ (ባህር ዳርና ጎንደር ብዙ ሆቴሎች ከ90 በመቶ በላይ ሰራተኛ ቀንሰዋል) ሽባ ሁኗል።4ቱም የትግራይ አየር ማረፊያዎች እና ሆቴሎች ግን ስራ ላይ ናቸው።አሁንም የአገልግሎት ዘርፉ አልቆመም።የግብርና ምርት ላይ መሰረት ያደረገው አማራው ደግሞ ገበሬው ወቅቱን ጠብቆ ባያዘምርም ቢያንስ ስራ አላቆመምና ራሱን መመገብ ችሏል።
በጥቅሉ “የሀገሪቱ” (የትግራይና የትግራይ ባለሀብቶች) እድገት ያላቆመው የምጣኔ ሀብት ክምችቱ ወደ ትግራይ መዞሩ መሆኑን ልብ ይሏል።የክልሉን የኢንዱስትሪ ዝርዝር ማውጣት የሚቻል ከሆነ እንጨምራለን።የአዲስ አበባን ካነሳንም የምጣኔ ሀብት ዘረፋው የተያዘው በጥቂት የትግራይ ተውላጅ ፊውዳሎች ነው።
ታድያ በየትኛው መስፈርት ነው ዛሬ መቀሌ በተፈጥሮ ብቻ እያደጉ ካሉት ከአዋሳ ወይም ከባህር ዳር ጋር የምትነፃፀረው?
መቀሌ ማለት እኮ ልክ ምዕራባውያኑ አልሸባብን እየደገፉ እንውጋው እንደሚባለው ሁሉን ቅልጭም አድርጋ ውጣ አላየውም አልሰማሁም እያለች ሰጭውንም ሌላውን በነገር የምትጎሽም አጋሰስ ከሆነች ሰነባብታለች።ይህች ጩኸት የመጣችው የሌላው አካባቢ ጩኸት ስለበረከተ አፍ ለማዘጋት ነው።
ለማንኛውም አዳነች ፍሳሃየ የተባለች ጋዜጠኛ የምትሄድበት መንገድ አሳፋሪነት ዛሬም ቀጥሏል፤ የህወሃት አጀንዳ ሰጭነት ወደ ውጭም ተሸጋግሮ ይኸው በመጨረሻ “ትግራይ በድህነት አረንቋ” በማለት ይሳለቁብናል።
ከድህነትም ከህወሃት ስናይፐር ጋርም ስቃዩን እያየ ያለው አማራውና ኦሮሞው ግን ዛሬም ስለሰብአዊነት ይጮሃል።የመኖር መብቴ ይከበርልኝ እያለ ይጠይቃል።ህወሃት ደግሞ እኔ እኮ አንተን አላውቅህም፤ላንተ አልታገልኩም እያለ መግደሉን ቀጥሏል።

posted by Gheremew Araghaw

Post Navigation

%d bloggers like this: