The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

ኃይለማርያም ደሳለኝ በቴሌቭዥን ቀርቦ በሕዝቡ ላይ ዛተ – ግርማ ካሳ

ሕዝቡ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ነው ያቀረበው። ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ ህዝቡ በሰላም ድምጹን አሰማ። ዜጎች ባነሱት ጥያቄ ልንስማማ፣ ላንስማማ እንችላለን ። ሆኖም ማንም ዜጋ የመሰለውን መናገርና መቃወም ይችላል። ህዝቡ ያደረገውም ይሄንኑ ነው።

ሆኖም የአጋዚ ጦር ሕዝቡን ጨፈጨፈ። ሕጻናት፣ አረጋዉያን ሴቶች፣ ወንዶች፣ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች ሁሉም እንደ ቅጠል በጥይት ረገፉ።

አጋዚ የፈጸመው ወንጀል የተደበቀ አይደለም። ፎቶዎችንና ቪዲዮዎች እያየን ነው። የሟች ቤተሰቦችን ድምጽ እየሰማን ነው። መረጃው፣ ሁሉም ነገር አለ።

ሆኖም ሃይለማርያም ደሳለኝ የሕዝቡን ጥያቄ አራክሶ፣ “የማይደገም ትምህርት እንሰጣለን” እያለ በመዛት ለሕዝብ ያለውን እጅግ በጣም ትልቅ ንቀት ማሳየቱን መርጧል። ከሕዝቡ ጎን ከመቆም፣ለህዝብ ከመቆርቆር፣ እነ ሳሞራን አሁን በቃቹህ ከማለት፣ እነ ሳሞራ ለፈጸሙት ወንጀል የክብር ሜዳሊያ እያጠለቀላቸው ነው። “ጎሽ ጥሩ አደረጋችሁ” እያላቸው ነው።

ኃይለማሪያም አይኖቹ የሚያዩ፣ አይምሮ የሚያስብ ከሆነ ፣ ትንሽ በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ ይመረመር ዘንድ፣ ተቃዉሞ የተነሳባቸውን ቦታዎች እንደሚከተለው ላቀርብለት ወደድኩ። እንቅስቃሴ የተደረገባቸው ቦታዎችን በቀይ ተከበዋል። (ካገኘሁት መጠነኛ መረጃ በመነሳር)

በኦሮሚያ ወደ 20 ዞኖች አሉ። የጂማ ልዩ ዞን፣ የጂማ ዞን፣ የኢሊባቡር ዞን፣ የቀለም ወለጋ ዞን፣ የምእራብ ወለጋ ዞን፣ የምስራቅ ወለጋ ዞን፣ የሁሩ ጉዱሩ ዞን፣ የአዳማ ልዩ ዞን፣ የቡራዪ ልዩ ዞን፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ ዞን፣ የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የምእራብ ሸዋ ዞን፣ የአርሲ ዞን፣ የምእራብ አርሲ ዞን፣ የምስራቅ ሃረርጌ ዞን፣ የምእራብ ሃረርጌ ዞን፣ የባሌ ዞን፣ የጉጂ ዞንን የቦረና ዞን ናቸው።

• በጉጂ ፣ በምእራብ ሃረርጌ ፣ በምእራብ አርሲ፣ በምእራብ ወለጋ፣ በምስራቅ ወለጋ ፣ በቀለም ወለጋ ፣ በአጠቃላይ በስድስት ዞኖች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ተቃዉሞ ተነስቷል።

• በምስራቅ ሃረርጌ፣ ከሃረር በስተምእራብ ባለው ቦታ፣ በአርሲ ወደ ታች ወረድ ብሎ፣ በጂማ ዞን በስተምእራብ ደቡብ በሸቤ ሳምቦ፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን ወደ ታች ወርዶ ምእራብ አርሲ ዞን አዋሳኝ ላይ በሚገኙት በቡልቡላና አዳሚ ቱሉ አካባቢ፣ ምእራብ ሸዋ ዞንን በሚያዋስኑ የሰሜን ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች፣ ወሊሶን ጨምሮ ግማሽ በሚሆነው የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ባጠቃላይ በጥቂት ይሁን በከፊል በሌሎች አራት ዞኖች ተቃውሞ ተነስቷል።

• እርግጥ ነው ከቡልቡላ፣ አዳሜ ቱሉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ አሉ ከሚባሉት ትላልቅ ከተሞች ከአንድ እስከ አምስት ከሚጠቀሱት ዉስጥ ( አዳማና ቢሾፍቱ) በሚገኙባቸው የአዳማ ልዩ ዛን እና በምስራቅ ሸዋ ዞን ብዙ እንቅስቃሴ አልታየም። እንደ ጂማ፣ አሰላ ባሉ ከተሞችም እንደዚሁ። በኢሊባቡር ዞን እንደ ሌሎች ዞኖች ብዙ የሚታይ እንቅስቃሴ የለም። ሆኖም እንቅስቃሴው የመዛመት ባህሪ ስላለው ተቃዉሞ በሌለባቸው ቦታዎች ያለው ህዝብም መብቱን ነጻነቱ የተነፈገ በመሆኑ፣ በማንኛውም ጊዜ ሊንቀሳቀስም ይችላል። ይንቀሳቀሳልም።

እንግዲህ ኃይለማሪያም ይሄንን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅን የሕዝብን እምቢተኝነት ነው፣ በሚቆጣጠረው ሜዲያ እያሳነሰ ያቀረበው።

የሚያዙት ሕወሃቶች ነገ ያስጡልኛል፣ ወይንም ሸሽተው ወደ ትግራይ ሲሄዱ እዚያ ያስጠልሉኛል ብሎ አስቦ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። ተጠቅመዉበት እንደ ታኘከ ማስቲካ ነው የሚተፉት። በአደባባይ ለተናገራቸውም ነዋራ ንግግሮች ምላሽ በሕዝብ ፊት ይሰጣል።

ያመረረና በቃኝ ያለ ህዝብ የሚፈለገውን ካለገኘ ወደኋላ አይልም። እነ ኃይለማርያም የሚበጃቸው ሰላምን መፈለግ ነበር። የሚበጃቸው የሕዝብን ጥያቄ አክብሮ ብሄራው እርቅ እንዲመጣ ነገሮች ማመቻቸት ነበር። እንግዲህ እንደ እንስሳ ማሰብ ከፈለጉና ከሕዝብ ጋር መላተም ከመረጡ መንገዱን ጭርቅ ያድርግላችው ከማለት ውጭ የምንለው የለንም። እኛ መክረናል። አስጠንቅቀናል። እንደ ጲላጦስ እጆቻችንንም ታጥበናል።

0208446236664

020844624

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: