The time for change

No bullet can stop the spirit of justice and democracy!!!

የደቡብ ሱዳን መሪዎች በጋምቤላው ግጭት መካሰስ ጀምረዋል

ya ya

(ሳተናው) የደቡብ ሱዳን መሪዎች በጋምቤላ ክልል በ13 መንደሮች በተፈጸመ ወረራ ለተገደሉ 208 ንጹሃንና ታፍነው ለተወሰዱ 108 ልጆች ኃላፊነት መውሰድ በሚገባው ቡድን ዙሪያ አንዳቸው ሌላኛቸውን መክሰስ ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ትናንት ረቡዕ የደቡብ ሱዳንን ድንበር በማቋረጥ ወታደሮቿ ታፍነው የተወሰዱባትን 125 ልጆች ለማስለቀቅ ጥቃት አድራሾች ናቸው ያለቻቸውን የሙርሌ ማህበረሰብ መኖሪያ ቦታ መክበቧን ማስታወቋ አይዘነጋም፡፡

የሙርሌና ሌሎች ማህበረሰቦች የሚገኙበትን ቦማ ክልል የሚያስተዳድሩት ባባ ሜዳን ጥቃቱን ያደረሱት የኮብራ ታጣቂዎች በመሆናቸው ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡የኮብራ አማጺ ሚሊሻ ከሙርሌና አኙዋክ ጎሳዎች በተውጣጡ ሰዎች የተቋቋመ ቡድን ሲሆን በ20005 ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር በስምምነት ለመስራት በመፈራረሙ የቡድኑ ታጣቂዎች ብሄራዊ በሆነው የአገሪቱ መከላከያ ኃይል ውስጥ እንዲቀላለቁ ተደርገዋል፡፡

የኮብራን አማጺ ኃይል የሚመሩት ዴቪድ ያሁ ያሁ የቀድሞው ጦራቸው እንዲህ አይነት ተግባር አለመፈጸሙን በመግለጽ ባባ ሜዳንን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ጥቃቱን ያደረሱትን ኃይሎች‹‹ወንደበዴዎች››በማለት ከመጥራት ውጪ ወንበዴዎቹ በማን እንደሚመሩ ይፋ አላደረገም፡፡

ምንጭ አሶሼትድ ፕሬስ

posted by Geremew Aragaw

Single Post Navigation

Leave a comment